Monday, November 11, 2013

ለጉዳዬ መነሻ የሆነኝ በ (facebook) የዉስጥ መስመሬ ከሳዉዲ አንዲት እህት የፃፈችልኝ አሳዛኙን በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ ያለዉን ሰቆቃ ሊረዳቸዉ የሚችል አካል ካለ የበኩሌን እንዳደርግር የሚማፀን መልክት ነዉ፡፡ የመልክቱ ይዘት አንዲህ ይነበባል፡- በፖሊሶች የሚደርስባቸዉ እንግልት፤ድብደባ እና ግድያ በተጨማሪ ተፈጥሮም እየተፈታተናቸዉ አንደሆነ ትናገራለች፡፡ እስር ቤት ዉስጥ ሰዉ በሰዉ ለይ ተደራርቦ ሞልቶ አሰፓልት ላይ ብርድ እና ፀሀይ አያሰቀያቸዉ ነዉ ትላለች፡፡ በተለይ ሴቶች እህቶቻችን ያሉበት ሁኔታ በጣም አንደሚያሳዝን እና ሊደርስላቸዉ የሚችል ወገን እንደሚፈልጉ መልእክት እንዳስተላልፍ ወይም የበኩሌን እንዳደርግ የሚማፀን ነዉ፡፡

ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ በ(facebook)የዉስጥ መስመሬ ከሳዉዲ አንዲት እህት የፃፈችልኝ አሳዛኙን በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ ያለዉን ሰቆቃ የበኩሌን እንዳደርግር የሚማፀን መልክት ነዉ፡፡


 BY:Mesfin Habtemariam (11.11.2013)
ለጉዳዬ መነሻ የሆነኝ በ (facebook የዉስጥ መስመሬ  ከሳዉዲ አንዲት እህት የፃፈችልኝ አሳዛኙን  በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ  ያለዉን ሰቆቃ ሊረዳቸዉ የሚችል አካል ካለ  የበኩሌን እንዳደርግር የሚማፀን  መልክት ነዉ፡፡
የመልክቱ ይዘት አንዲህ ይነበባል፡- በፖሊሶች  የሚደርስባቸዉ እንግልት፤ድብደባ እና ግድያ በተጨማሪ ተፈጥሮም እየተፈታተናቸዉ አንደሆነ ትናገራለች፡፡ እስር ቤት ዉስጥ ሰዉ በሰዉ ለይ ተደራርቦ ሞልቶ  አሰፓልት ላይ ብርድ እና ፀሀይ አያሰቀያቸዉ ነዉ ትላለች፡፡  በተለይ ሴቶች እህቶቻችን ያሉበት ሁኔታ  በጣም አንደሚያሳዝን እና ሊደርስላቸዉ የሚችል  ወገን  እንደሚፈልጉ መልእክት እንዳስተላልፍ ወይም የበኩሌን እንዳደርግ የሚማፀን ነዉ፡፡
ግን ምን ማድረግ እችላለሁ፤ ማድረግ ብችል ጥሩ ነበር፤ ዉስጤ በሀዘን እያነባ እህህ እንጂ ልደርስላቸዉ አልቻለኩም፡፡ አዝናለሁ ማድረግ የምችለዉ መረጃዉን ለሚችሉ ማስተላለፍ ብቻ፡፡
ዘም ብዬ በዚህ ጉዳይ ሰብከነከን የሀገራት የዲፐሎማሲ ግኑኝነቶች  (Diplomatic  Relations)ማለተ ምነ ማለት ነዉ አልኩ፡፡ ምክንያቱም ይህ ወዳጅነት ሀገራት እርስ በርስ በመከባበር በፖለቲካ፤በኢኮኖሚ፤በባህል እና በመሳሰሉት ለሀገራቸዉ ለወገኖቻቸዉ  በሚጠቅም መንገድ በጋራ በትብብር ሊሰሩ ወዳጅነት ይመሰርታሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒዉ አሁን የኢትዮጲያ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ እንዳለዉ አይነት  ወንጀል ሲፈፀም የክብር የሉአላዊነት ጉዳይ ስለሆነ መንግስታት ለሀገራቸዉም ለወገኖቻቸዉ ክብር ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ ወይም በአለም አቀፍ የህግ  አግባብ  እርምጃ ይወስዳሉ፡፡  
ለነገሩ ኢትዮጲያ  ክብራን የሚያስጠብቅላት መንግሰት ሲኖራት አይደል ዜጎች መብታቸዉ ሚጠበቀዉ፡፡ አበዉ ሲተርቱ ባለቤቱ ያቃለለዉን አሞሌ ጨዉ....አንዳሉት፤ ወያኔ በአለም ፊት  ሰዉ የመሆን ክብራችንን አዋርዶት ሌሎች በስደት ሄደነባቸዉ እንዴት ሊየከብሩን  ይችላሉ?
ህዝባችን እረኛ እንደሌለዉ መንጋ ተበትኖ፤ ተዋርዶና ክብሩን ጥሎ  መኖር ከጀመረ እነሆ 23 አመታትን  አስቆጠረ፡፡ ዜጎቻችን  በቄያቸዉ በሰላም ሰርተዉ እንዳይኖሩ በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ  ተማረዉ በስደት የበረሀ፤ የባህር ሲሳይ እየሆኑ ከዛም የተረፉት ይኸዉ አሁን እንደምናየዉ ለጨካኝ አዉሬዎች እንደሰዉ ተፈጥረዉ አንደአዉሬ የሚንቀሳቀሱ ሰዉ በላ የአረብ ፖሊሶች እንግልት እና ሞት ተዳርገዋል፡፡
ዛሬ ዉሸት በማይታክተዉ ኢትዮጲያ ቴሌቪዥን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ቀርበዉ ስለ አረብ ሀገር ስደተኞች ተጠይቀዉ ሲመልሱ፤ በሳዉዲ ሀገር ያለዉን አምባሳደር አስጠርተዉ ስለጉዳዩ ሊጠይቁ እደሆነ ተናግረዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ መጠየቃቸዉ ባያስከፋም ወገኖቻችን አሁን የሚያስፈልጋቸዉ አፋጣኝ ነፍስ የማዳን ምላሽ ነዉ፡፡ አሁን የሚያሰፈልገዉ በየትኛዉም መንገድ እንደ መንግስት ዜጎቻችን  ከእስር፤ ከድብደባ እና  ከግድያ  አንዲያመልጡ የሳዉዲን መንግስት ማስቆም ነዉ፡፡
ባለቤቱን ካልደፈሩ አጥሩን አይነቀንቁም አለ የሀገሬ ሰዉ፡ ሀላፊንት የሚሰማቸዉ ቢሆን  ወያኔዋች ዜጎች በየሀገሩ  በሄዱበት ሁሉ ሲዋረዱ የእነሱም ዉርደት አንደሆነ የገባቸዉ አይመስልም ወይም ጆሮ ዳባ ብለዋል፡፡ ለንገሩ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር 
Dr. ቴዎድሮስ አድሃኖም  ሳዉዲን በጎበኙበት ወቅት ከሳዉዲ ባለ ስልጣናት ጋር ህገወጥ የሚባሉትን ስደተኞች እንዲያሶጡና በምትኩ 40፣000 ህጋዊ ዜጎችን አንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ እንደ ያዙ ባለስልጣናቱ ይናገራሉ›› ይህ በጣም ሀላፊነት የጎደለዉ ጊዜዉ ሲደርስ ከተጠያቂነት ማምለጥ አንደማይቻል ሊያዉቁት ይገባል፡፡
በሰለጠነ ዘመን ወደላ እንደ ጋርዮሽ የጨለማ ዘመን ሰዉ በሚመስሉ  በሰዉ በላ አዉሬዎች በወገኖቻችን ላይ በአረብ ሀገር መንግስታት የሚደርሰዉን እንግልት የአለም አይን እና ጆሮ እንዲያይ እና እንዲሰማዉ የምንችል ሁሉ የበኩላችንን እናድርግ ጥሪዬ ነዉ፡፡
ፍትህ ፍትህን ለተጠሙ ይሁን!!
Via:-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9220

No comments:

Post a Comment