ይህ ከዚህ በታች ያለው ማስታወቂያ በጽ/ቤቱ መግቢያ ላይ የተለጠፈ ማስታወቂያ ሲሆን፤ ሌሎች የአካባቢው ምንጮች ቀደም ብለው እንደገለጹት ከሆነ፤ “የቆንስላ ጽ/ቤቱ ስራውን ካቆመ ቆይቷል። በተለይም አንዳንዶቹ ሰራተኞች፤ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት ሰዎች ጋር አብረው ሄደዋል” ሲሉ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ነበር የሰነበቱት። አሁን ዛሬ የተደረገውን የስራ ማቆም ማስታወቂያም፤ አብዛኞቹ ሰራተኞቹ ወደ አዲስ አበባ ተደባልቀው በመመለሳቸው የሚለውን አባባል ያጠናክረዋል።
ከዛሬ ጀምሮ፤ አገልግሎት መስጠት አቁመናል!!
ነዋሪነቱ በጅዳ፣ ሳኡዲ አረቢያ የሆነው ነብዩ ሲራክም እንዲህ ብሏል። “በጅዳና አካባቢ እየሆነ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ከመንግስታችን ተወካዮች መረጃ ማግኘት አልችል ያለው ነዋሪ ተረባብሿል … ህገ ወጥ ነዋሪዎች ወደ ሃገር ቤት መግባት የሚችሉበትን ቀዳዳ ሁሉ ቢያነፈንፉ የመረጃ ፍንጭ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ይናገራሉ! አንዳንደዶች ደግሞ እየተቆጡ ነው! ህጋዊው ነዋሪ ዜጎቹን መደገፍ የሚችልበት መንገድ ጠፍቶት እየዋለለ ነው! ከትናንት ጀምሮ ከአንዳንድ ወዳጆቸ ጋር ጉዳዩን በዋናነት የሚያንቀሳቅሱትን የመንግስት ተወካዮች ድጋፍ ማድረግ ባለብን እርዳታና ድጋፍ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ ይዘናል! ረፋዱ ላይ ደግሞ የጅዳ ቆንስል ስራ በውል ላልተጠቀሰ ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዳቆመ በማስታወቂያ አስታውቋል ! ግራ ግብት ያለ ነገር ሆኖብናል!” በማለት አስተያይውቱን ሰጥቷል።
No comments:
Post a Comment