በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያ አራት ነው፡፡ አሁን የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲኾን የመጣው ግን ከአማራ ክልል አካባቢ መኾኑን የቅጥር መዝገቡ ያሳያል፡፡ በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ፡፡ ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱ ፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ(እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ በመተኮስ በግምት ወደ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል፡፡ የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል፡፡ የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል፡፡ በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል፡፡አሁን በተገኘ መረጃ ‹‹ኑሮ መኖኛል›› ሲል ተሰምቷል፡፡ እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል፡፡አሁን አስክሬኑኑን የፖሊስ መኪና አንስቶታል፡፡
ምንጭ፦ ጽዮን ግርማ
http://www.ethiotube.net/