Wednesday, April 22, 2015

Addis Ababa: Scuffles erupted moments after Hailemariam Desalegn spoke

April 22, 2015
ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopian demonstrators hurled stones and scuffled with police during a rally byScuffles erupted moments after Prime Minister Hailemariam Desalegn spoke. thousands in the capital on Wednesday after a video showed dozens of compatriots being shot and beheaded by Islamic State militants in Libya, witnesses said.
The rally was to show solidarity with families of those killed. Scuffles erupted moments after Prime Minister Hailemariam Desalegn spoke. Witnesses saw several people being detained by police.
Ethiopia has confirmed that those killed in the video, posted at the weekend, were its citizens. Family members have so far named two of them.
Read more below the video…
Demonstrators hurled stones and police fired teargas as emotions ran high at a mass rally in Ethiopia’s capital on Wednesday commemorating 30 compatriots shot and beheaded by Islamic State militants in Libya, witnesses said.
Protesters started gathering at Addis Ababa’s Meskel Square at dawn to denounce Islamic State. “We will not bow down to terrorism!” one placard carried by a young boy said. Another read: “The world must be united against terrorism.”
One man at the government-organized rally, who said he was a university professor, said many in the crowd were angry that jobless Ethiopians still felt they had to travel to places like Libya in the hope of crossing over to a better life in Europe.
He also accused the authorities of clamping down on free speech. “Even the chanting (at the rally) was led by the government,” he said. “We do not have the power to speak.”
Ethiopia’s government dismisses accusations from rights groups that it stifles critics and opponents.
The rally was called to show solidarity with families of those killed and to mark the start of three days of national morning. Scuffles erupted moments after Prime Minister Hailemariam Desalegn spoke.
When some in the crowd hurled stones, police fired a teargas canister, witnesses said. Several people were detained and at least four police officers were seen being driven away, they added.
The prime minister urged Ethiopians not to travel across the Sahara to reach Europe. “We should strengthen our resolve against any form of terrorism and extremism,” he added in his speech.
Although Ethiopia’s economy is growing fast, unemployment remains high. Many opt to trek across the Sahara in a bid to reach Europe via Libya, where Islamic State militants have gained a toehold after seizing large parts of Syria and Iraq.
Ethiopia has confirmed that those killed in the video, posted at the weekend, were its citizens. Family members have so far named two of them.
“I am in pain. The innocent son of a poor mother butchered like he was,” said Ahaza Kasaye, the mother of one of those identified, said, propping herself up with a walking stick. “But I am heartened to see so many Ethiopians mourn him.”
The killings have stunned a nation where relations between Ethiopia’s Christians and Muslims have long been relatively peaceful. Muslim lawmakers in parliament on Tuesday read out verses in the Koran preaching tolerance.
http://ecadforum.com/News/addis-ababa-scuffles-erupted-moments-after-hailemariam-desalegn-spoke

Wednesday, April 15, 2015

በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው


ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ የቱሪስት ከተማ የደርባን ተወላጆች_የውጭ አገር ዜጎች ከአገራቸው እንዲወጡ ለማስገደድ በወሰዱት ጥቃት 3 ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አጇንስፍራንስፕሬስዘግቧል።
ኢትዮጵያዊያኑ ሱቆቻቸው ውስጥ እንዳለ በጋስ በተሞላ ቦንብ መቃጠላቸውን አንዳንዶች ተደብድበው መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በደርባንና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጭንቅ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ደግሞ አንድ ኢትዮጵያዊ አገራችን ችግር ላይ ነች፣ አገር የለንም የት እንደምሄድም አላውቅም ብሎአል።
የአሁኑ ተቃውሞ የዙሉ ባህላዊ ንጉስ ጎድ ዊል ዝዌልቲኒ የውጭ አገር ዜጎች ሻንጣዎቻቸውን ሸከፍው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ነው። የፕሬዚዳንት ዙማ ልጅ በበኩሉ ” የውጭ አገር ዜጎች አገሪቱን በረጅም ጊዜ ሊቆጣጠሩዋት ይችላሉ” በሚል የሰጠው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል። ማላዊ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ በማውጣት የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።

Tuesday, April 14, 2015

ሞያሌ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ እኩለቀን ድረስ በተኩስ ተናጠች

 የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ከትናንት ሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ እኩለቀን ድረስ ከተማዋ በተኩስ ስትናወጥ ውላለች።አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት የተኩሱ ልውውጡ የተካሄደው በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያዎች መካከል ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንድ የክልል 5 ጠባቂ መግደላቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ልዩ  ሃይል ሚሊሺያዎች በየሰዎች ቤት እየገቡ እቃዎችን ከመሰባበርና ከመዝረፍ በተጨማሪ ከተማዋን በተኩስ ሲበጠብጡዋት አድረዋል።
ጧት አካባቢ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛና በሶማሊኛ የተጻፉ ወረቀቶች መበተናቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ጽሁፎቹ በከተማው ያሉትን ባንዶች ለመቅጣት መጥተናል የሚል ይዘት እንዳለው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በማግስቱ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አላቸው የሚባሉ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል።
አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት የሶማሊ ክልል ተጣቂዎች ምሽት ላይ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አስቁመው በሚፈትሹበት ጊዜ፣ አንደኛው ለምን ትፈትሹታላችሁ በማለት ፈታሹን የገደለው ሲሆን፣ መረጃው በሶማሊ ክልል  ታጣቂዎች  ዘንድ በመድረሱ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ መነሳሳታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የክልሉ ታጣቂዎች ሌሊት ላይ በወሰዱት እርምጃ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ  የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የከተማዋ የሶማሊ ተወላጆች የመከላከያን ድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ በመኪኖች እና በተለያዩ ድርጅቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአል። የፌደራል ፖሊሶች ተከታታይ ጥይቶችንና አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ቢችልም፣ ውጥረቱ እስከ ምሽት ዘልቋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ውለዋል።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ከረብሻው ጋር እጃቸው አለበት ብለው የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ ናቸው።

We Say the Land is Not Yours: Breaking the Silence Against Forced Displacement in Ethiopia

April 14, 2015
Oakland, CA – We Say the Land is Not Yours: Breaking the Silence against Forced Displacement in Ethiopia, aWe Say the Land is Not Yourslandmark report from the Oakland Institute documents testimony from members of several ethnic groups from different areas of the country,1 bringing forward the voices of those most directly impacted by land grabs and villagization. The Ethiopian government’s villagization program aims to resettle up to 1.5 million Ethiopians, mainly pastoralist and indigenous communities, from areas targeted for industrial plantations. These resettlements have happened without free, prior and informed consent, and when communities resist, they have been forcibly removed by means of violence, imprisonment, intimidation, political coercion, and the denial of humanitarian assistance.
“The Oakland Institute has released reports based on meticulous fieldwork and years of research, exposing the human rights abuses against indigenous and pastoralist communities in Ethiopia,” said Anuradha Mittal, the Oakland Institute’s Executive Director. “As the country now prepares for the national election in May 2015, it is important for communities that have been shut out and locked up, to tell their stories in their own words.”
Over the past few years, free speech in Ethiopia has been systemically withdrawn. International media and NGOs have documented the threats, arrests, and disappearances of those critical of government’s policies. To add to this is the lack of media freedom: Ethiopia is the second biggest jailer of journalists after its neighbor, Eritrea. Its broadcasting and telecommunications sectors are controlled by the state, and the minimal private media sector is heavily regulated and frequently censored.
“The context in which we release this report is one of torture, oppression, and silencing,” said Mittal. “A development strategy without ensuring its citizens freedom of speech and expression is not a development strategy but a scheme to benefit the ruling elites. Those basic human rights are not being upheld in Ethiopia. It is therefore urgent to make voices of those impacted heard.”
The report includes the voices of Ethiopians, some who remain in Ethiopia, and others who have fled to neighboring countries and have sought political asylum.
With the impending national elections, the government has escalated its crackdown on political opposition and dissent. This report brings forth the voices that are being silenced, to bring this oppressive situation to the attention of the members of the African Union, international community, and donor countries. The time is now to take decisive action.
To download a copy of the report, click HERE.
For more information on Ethiopia, click HERE.
1 Representatives of affected communities from Gambella, Benishangul, Hammer and Nyangatom in the Omo Valley, and refugees in Kenya, came forward to share their experiences.

Thursday, April 9, 2015

” ምስክር ፈላጊው ችሎት ” – 27ተኛ የፍርድ ቤት ውሎ

ሚኒስቴር ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳይቶ ቢሮ ሲፈተሽ ታዘብ ተብዬ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሲ.ዲ እና ዲክሜንት ሲወሰድ አይቻለሁ፡፡ ከዚያ ፖሊስ በ9/2006 ዓ.ም ሄጄ በሶፍት ኮፒ የነበሩት ሰነዶች ፕሪንት ተደርገው ማህሌት የፈረመችባቸው ላይ ፈርሜያለሁ፡፡ በእንግሊዝኛና አማርኛ የተጻፉ ናቸው፡፡ በግምት ወደ 40 ገጽ ይሆናል፡፡ አብዛኛው የፖለቲካ ነክ ጽሑፎች ናቸው፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጽሑፎች አሉበት፡፡ ያየናቸው መረጃዎች ከእሷ ኮምፒውተር ላይ ስለመገኘታቸው አይተን ፈርመናል፡፡››
ለእኒህ ምስክር መስቀለኛ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር፡፡
የጠበቆቹ መስቀለኛ ጥያቄ፡- ሲዲውን ማን እንዳመጣው
ታውቃለህ…ውስጡ ምን ነበረበት…
የምስክሩ መልስ፡- እኛ ራሳችን ቼክ አድርገናል፤ ባዶ ሲ.ዲ ነው፡፡በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል ያሉ አምስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡። የምስክሮቸን ቁጥርም 35 ነው በማለት ቀይሮታል፡፡
ባለፈው የተሰሙት 13 ምስክሮች ሲሆኑ በዛሬው ችሎት ባልተካደ ነገር ላይ ሲመሰክሩ የዋሉት የደረጃ ምስክሮች
14ተኛ ምስክር ተወዳጅ ኃ/ማርያም ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 34 ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹የመጣሁበት ኬዝ ግንቦት 7/2006 ዓ.ም በምኖርበት ልደታ 5ኛ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ጠይቆኝ በታዛቢነት ያየሁትን ለመመስከር ነው፡፡ ማህሌት ጤና ጥበቃ ሚ/ር ትሰራለች መሰለኝ፣ እዚያ መስሪያ ቤት ፖሊስ ማህሌት ኮምፒውተርና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሲበረብር አይቻለሁ፡፡ መንግስት መስሪያ ቤት የምትጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ የተገኙ ሰነዶች ላይ ማህሌት ስትፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ የፈረምነው ግንቦት 7/2007 ዓ.ም ነበር፡፡ የገጹን ብዛት አሁን አላስታውስም፤ ወደ 40 ገጽ ይሆናል፡፡ እንግሊዝኛና አማርኛ ጽሁፎች አሉበት፡፡ የተወሰነ የፖለቲካ ይዘት የነበረው አለ፡፡ የፖለቲካ ፕሮግራም ማኒፌስቶ አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ ማህሌትን ሲጠይቃት ከኦነግ የወጣው የሌንጮ ፓርቲ ፕሮግራም ነው ብላለች፡፡ ጎስፕ ንግግሮችም አሉ›› ብሏል፡፡ ዳኛው ጎሲፕ በአማርኛ ምንድነው ሲላቸው ምስክሩ ‹‹ሽሙጥ ንግግር ነው›› ብለው መልሰዋል፡፡ ምስክሩ የተገኙ ሰነዶች ላይ ፌደራል ፖሊስ ሄደው እንደፈረሙና ይሄን ያደረጉትም ግንቦት 9/2006 ዓ.ም ነው ብለዋል፡
15ተኛ ምስክር ፀሐይ ብርሃኔ እድሜያቸው 33 የሆኑ የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹ግንቦት 7/2006 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ፌደራል ጤና ጥበቃ 
ጥያቄ፡- የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብለሃል….ስንት ናቸው
መልስ፡- አንድ ብቻ አይደሉም
ጥያቄ፡- የተለያዩ ፓርቲዎች ሰነዶች ብለዋል እኮ….እነዚህ ላይ ሁሉ ፈርመዋል
መልስ፡- አሁን በትክክል የማስታውሰው የሌንጮ ፓርቲ ሰነድ ላይ መፈረሜን ነው፡፡ ሌሎች ላይ አልፈረምኩም፡፡
(አንድ ሰነድ ቀርቦላቸው ፊርማው የእሳቸው ስለመሆኑ እንዲለዩ ተደርገው የእሳቸው መሆኑን አረጋግጠው የፈረሙበትን ሰነድ ይዘት ግን እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡)
ፍርድ ቤቱ ‹‹40 ገጽ ማየትህን ተናግረሃል፤ 40 ገጽ ላይ ፍርመሃል፣ ይዘቱንስ ታውቃለህ›› ብሎ ጠይቋቸው ምስክሩ ‹‹እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፍረሜያለሁ፤ ግን አላነበብኩትም፡፡ ክፍት የስራ ማስታወቂያ የሚል ግን አይቻለሁ›› ብለዋል፡፡ በተለየ የትኛውን ነው ያነበብከው ለተባሉት ደግሞ ‹‹አሁን አላስታውስም፤ የሌንጮ ሰነድ ላይ ፈርሜያለሁ፡፡ ማህሌት ፖሊስ ሲጠይቃት ሌንጮ የራሳቸውን አዲስ ፓርቲ እያቋቋሙ እንደሆነ ስትናገር ሰምቻለሁ›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
16ተኛ ምስክር ዳግማዊ እንዳለ 25 ዓመታቸው ሲሆን የመንግስት ሰራተኛና የአ.አ ከተማ የካ ክ/ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ በ5ኛ ተከሳሽ አጥናፍ ላይ ለመመስከር እንደመጡ ተናግረው የአባቱን ስም አላስታውስም ብለዋል፡፡
“ሚያዝያ 17/2006 ዓ.ም 11፡00 ገደማ ከስራ ወደ ቤት ስሄድ 22 ትራፊክ ፖሊስ ጀርባ ፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ወረቀት አሳይቶ ታዛቢ ሁነኝ ብሎኝ ተገኝቻለሁ፡፡ አጥናፍ ቤት ገብተን ሰነዶች ሲገኙ አይቻለሁ፡፡ ፍላሽ፣ ሴኪዩሪቲ ኢን ኤ ቦክስ የሚል መጽሐፍ፣ ሲ.ዲ ተገኝተዋል፡፡ ሌሎች ታዛቢዎችም ነበሩ፡፡ ሰነዶቹ ላይ አጥናፍ ሲፈርም እኛም ፈርመናል፡፡›› ብለዋል፡፡
17ኛ ምስክር፡- ሳምሶን ሲሳይ ይባላሉ፤ 29 ዓመታቸው ሲሆን በግል ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡ አድራሻቸው አ.አ የካ ክ/ከተማ ነው፡፡ አጥናፍ ላይ ለመመስከር መምጣታቸውን ተናግረዋል ‹‹ሚያዝያ 17/2006 ዓ.ም 11፡00 አካባቢ ትራፊክ ጽ/ቤት ጀርባ ፖሊሶች ታዘብልን ስላሉኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ሲ.ዲ፣ ፍላሽ፣ የተለያዩ ዶክሜንቶች፣ ላፕቶፕ፣ ማስታወሻ ደብተሮች መገኘታቸውን አይቻለሁ፡፡ በዝርዝር አላስታውስም፡፡ ግን 150 አካባቢ መጽሐፍ ቆጥረናል፡፡ ፋክት መጽሔት ተገኝቷል፡፡ መጽሐፎቹ በእንግሊዝኛና አማርኛ የተጻፉ ናቸው፡፡ አጥናፍ የፈረመባቸው ላይ እኛም ፈርመናል፡፡›› ብለዋል፡፡
18ኛ ምስክር፡- እኒህ ምስክር ደግሞ በረከት ብርሃኔ የሚባሉ ሲሆን እድሜያው 29 ነው፡፡ በግል ስራ ላይ የተሰማሩና የአ.አ አራዳ ክ/ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ 6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ላይ ለመመስከር እንደመጡ በመግለጽ ዘላለምን በአካል ለይተው አሳይተዋል፡፡ ‹‹ግንቦት 16/2006 ዓ.ም ማዕከላዊ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፖሊስ በጠየቀኝ መሰረት ታዝቤያለሁ፡፡ ሰነዶች ልናይ ስለሆነ እይልን አሉኝ፡፡ እሺ ብዬ ወደ ቢሮ ገባሁ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ይሆናል፡፡ እኛ ከገባን በኋላ ዘላለም ተጠርቶ መጣ፡፡ ላፕቶፑን ራሱ ፓስወርዱን ከፈተው፡፡ ከዚያ ከላፕቶፑ የወጡ ሰነዶች ፕሪንት ተደርገው ፈረምንባቸው፡፡ እንግሊዝኛም አማርኛም ነበር፡፡ ደሞ ምሳ ተጋብዘናል፡፡ ዘላለም ብላ ሲባል አልበላም አለ፡፡ አሁን ሰነዶቹ ምን እንደሆኑ አላውቅም፡፡ ዘላለም የፈረመበት ላይ ነው እኔ የፈረምኩት፡፡ ለማንበብ ግን ጊዜ አልነበረኝም፡፡ ስለዚህ ይዘቱን አላውቀውም፤ እሱ የፈረመበት ስለሆነ ብቻ ፈርሜያለሁ፡፡ አልፈርምም ያለው ሰነድ አልነበረም፡፡ ሌሎች ታዛቢዎችም ነበሩ፡፡ እነሱም ፈርመዋል›› ብለዋል፡፡
ምስክሮች ከመሰማታቸው አስቀድሞ አቃቤ ህግ ባለፈው የተሰጠው ቀጠሮ አጭር በመሆኑ ሌሎቹን ምሰክሮች ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ ቀጠሮ አንዲሰጠው አንዲሁም አስመዝግቤያለው ካላቸው ሲዲዊች ውስጥ 7ቱ አንዲሰሙለት የጠየቀ ሲሆን የቀሩት ግን ሲዲውን የያዘው ባለሞያ ከአገር ውጪ በመሆኑ ማቅረብ አልቻልንም ብሏል፡፡ የተከሳሾች ጠበቆች ተከሳሾች ከታሰሩ አንድ አመት ሊሞላ ጥቂት አንደቀረ ምስክሮቸን ማዘጋጀት ቀደም ብሎ መሰራት የነበረበት የአቃቤ ህግ ስራ መሆኑን ነገር ግን በተደጋጋሚ እድል እየተሰጠው አንዳልተጠቀመበት በመጥቀስ ዛሬ የቀረቡት የሰው ምስክሮች መጨረሻ አንዲሆኑ እና የቀሩ ማስረጃዎቸን ለመስማት አጭር ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ “ፍርድ ቤቱ” የአቃቤ ህግን ክርክር በመደገፍ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ከአንድ ወር በላይ በማራዘም ግንቦት 18-21 2007 አም ድረስ እንዲሆን አንዲሁም የሲዲ ማስረጃዎቹ በወቅቱ ተሟልተው አንዲቀርቡና ቀሪ ምስክሮቹም በዚያው ቀን ወስኖ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡
የዞን9 ማስታወሻ
አንደሁልጊዜው ሁሉ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ክስ ፓለቲካዊ ነው ያልተሰራ ወንጀል ምስክር አይገኝለትምና ፈጣን ፍትህን የማግኘት መብትን መቀለጃ ላደረገው ፍርድ ቤትም ሆነ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ ጓደኞቻችንን ለመፍታት አሁንም ጊዜው አልረፈደም የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ አንወዳለን፡፡

በጋሞ ጎፋ ፖሊስ በህዝብ ላይ የጭካኔ እርምጃ ወሰደ ወንጀላቸው – መሬታቸው ለጥምባሆ “ባለሀብት” መሰጠቱን መቃወማቸው

በጋሞ ጎፋ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ አልጌ ቀበሌ ፖሊስ በንፁሃን ላይ የጭካኔ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአባያ ሀይቅ ዙሪያ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት ነዋሪዎች መሬት ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት እንደተሰጠባቸው መነገሩን ተከትሎ የአካባቢው ሽማግሌዎች ከሶስት ጊዜ በላይ ለክልሉ አስተዳደር ማመልከቻ ቢያስገቡም መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ አስተዳደር ምንም አይነት መልስ ባይሰጥም የዞኑ አስተዳደር “መሬቱ ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት ተሰጥቷል” የሚል ውሳኔ በማስተላለፉ ነዋሪዎቹ ይህን የዞኑን አስተዳደር ውሳኔ እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህዝቡን ተቃውሞ ተከትሎም ፖሊስ በአባያ ነዋሪዎች ሰፈር እየመጣ እያስፈራራ እንደሚመለስ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
gamo goffaየካቲት 30/2007 እንደተለመደው ፖሊስ ነዋሪዎቹን ለማስፈራራት ወደ ሰፈር በሄደበት ወቅት ነዋሪዎቹ ፖሊሶቹን “ከሰፈራችን ውጡልን!” እንዳሏቸው ተገልጾአል፡፡ ይሁንና ፖሊስ ከሰፈራቸው እንዲወጡለት የጠየቁትን አዛውንቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙ ተገልጾአል፡፡ ፖሊስ አዛውንቶቹ ላይ ድብደባ መፈጸሙን የተቃወሙ ወጣቶች ላይ ጥይት በመተኮስ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል፡፡ በወቅቱም አንድ ሰው ሲሞት ከ8 ሰዎች በላይ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተገልጾአል፡፡
እስካሁን ድረስ በንጹሃኑ ላይ የጭካኔ እርምጃ የወሰዱት ፖሊሶች ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ እንዳልተወሰደባቸውና በስራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ ፌስቡክ ገጽ)