Monday, June 17, 2013

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ “ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”


በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።   
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። 
አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል።  
ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል። 
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ። 
ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ። 
በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር። 
አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ። 
አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ። 
ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር። 
ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። 
አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡ 
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል። 
“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል። 
የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።  
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡

Saturday, June 15, 2013

አንድነት ፓርቲ ለመድረክ ምላሽ ሰጠ፤ የተደበቀውን አፍረጠረጠው

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
በመሠረቱ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) መድረክ እንዲመሠረትና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ለመድረክ መፈጠርና መጎልበት በአደረገው ጉልህ ተሳትፎ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት መሆኑን መድረክም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡   
የግምገማው ግኝቶች በየትኛውም ገጽና ቦታ የመድረክ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብና የስምምነት ሰነድ በመድረክ አባል ድርጅቶች በጋራና በሙሉ ስምምነት መጽደቃቸውን አላስተባበለም፡፡ አልካደምም፡፡ በተጨማሪም መድረክ እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ህሊና ውስጥ ከፍተኛ ተስፋን የፈጠረ ብቻ ሳይሆን አዲስ የጉዞና የአሠራር አቅጣጫን የቀየሰ መሆኑን ጭምር አንድነት ያውቀዋል፡፡ ያምንበታልም፡፡  
መድረክ ከመቀናጀት ወደ ግንባር የተሸጋገረበት ሂደትም ብዙ ችግሮችና ድክመቶች ቢኖሩትም በአባል ድርጅቶች ሙሉ ስምምነትና ፍቃደኘነት መሆኑን አንድነት አምኖ የሚቀበለው እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም የመድረክ ድክመቶች፣ ስህተቶችና ችግሮች በሙሉ አንድነት ፓርቲም አብሮ የሚጋራውና የሚጠየቅበት ነው፡፡ የግምገማው ዓላማ ችግሮችንና ድክመቶችን ወደ ሌሎች የመግፋት (blame-shifting) አባዜ አለመሆኑን አበክረንና አጠንክረን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡   
በአባል ድርጅቶች መካከል ስምምነት ያልተደረሱባቸው የፕሮግራምም ሆነ የህገ-ደንብ ጉዳዩችም በቀጣይ ውይይቶች ለማቀራረብ እንደሚሞከርና ይህ ካልተሳካም መድረክ የመንግሥት ሥልጣን ሲይዝ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሔ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሙሉ ስምምነት ያገኘ ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው፡፡ 
የመድረክ መግለጫ፣ ችግርች የሚጀምረው በመጀመሪያ ያልተካሄዱ ጉዳዩችን እንደተካሄዱ አርጎ ከማቅረቡ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛውና መሠረታዊው ችግር ደግሞ ድርጅቶች በአንድ ወቅትና ሁኔታ ተስማምምተውና ወደው የተቀበሉት ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግምገማ ማካሄድ የለባቸውም የሚለው ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአንድ ወቅትና ሁኔታ የተወሰኑ ሰነዶችን ፓርቲዎች በስምምነት ስለተቀበሉት ብቻ ሰነዶችን ትክክል ያደርጋቸዋል የሚለው ግንዛቤ ነው፡፡ ባጠቃላይ ሕይወትና በውስጡ ያሉ ክስተቶች በሙሉ የማያቋርጥ የለውጥ ሂደትና እንቅስቃሴ አካል ናቸው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሥነ አመክኖ (Logic) ሰነዶች ከወቅት፣ ከጊዜና ከሁኔታዎች አኳያ (አንፃር) ይፈተሻሉ፣ ይገመገማሉ ይሻሻላሉ፣ ይለወጣሉም፡፡ 
በመግቢያው ላይ እንደተቀመጠው የግምገማው ዓላማ የመድረክ ድክመቶች የሚስተካከሉበትና ጥንካሬዎቹ የሚጎለብቱበት ሁኔታ እንዲፈጠርና ብሎም ትግሉ የሚፈልገውን ሁለንተናዊ አቅም ለመፍጠር እንዲቻል ነው፡፡ በዚህ ረገድ የአንድነት ፓርቲ ምን ዓይነት ሚና መጫወት ይገባዋል የሚለውን ጭምር ለመፈተሽ ነው፡፡ በግምገማው ሂደትም የታዩት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 
ሀ) ለአለፉት በርካታ ዓመታት በተቃዋሚ ጎራ አብሮ ላለመስራት ፈታኝ ሆኖ የቆየውን የኢትዮጵያ ብሔርተኘነትና ብሔር ላይ በተመሰረቱ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን ክፍተት በተወሰነ መልኩ ማጥበቡ በአዎንታነት የሚታይ ቢሆንም፤ መድረክ ከተመሠረተ አራት ዓመት ቢያልፈውም በፕሮግራም ልዩነቶች ላይ አንድም ቀን ውይይት አለማካሄዱና ደንበቦችንም ቢሆን አብረን የቆየንባቸውን ጊዜያት ያገናዘበና ትግሉ የሚጠይቀው ደረጃ የሚመጥን ለውጥ አለማድረጉን ነው፡፡ ይህም አንዱ ዋና ምክንያት በመሆኑ መድረክ ከተመሠረተ ጀምሮ ፓርቲዎቹ የመድረክ አባል ለመሆን ያለመቻላቸው ነው፡፡ 
ለ) የመድረክን ሕገ-ደንብ በኢ-ዴሞክራሲያዊነት ለማስቀመጥ አስገዳጅ የሆነው አንዱ ምክንያት ፓርቲዎች የመተማመንና የአብሮ የመስራትን መንፈስ መፍጠራቸውና ከ4 ዓመት በኋላም በሙሉ ድምጽ ስምምነት ማለፍ ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸው ጭምር ነው፡፡ የቪቶ ሥልጣን የተሰጠውም የፓርቲዎችን ፍላጎትና ስጋቶች ለማስተናገድ ነው የሚለውም በግምገማው ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው፡፡ ትልቅ ቦታም ሊሰጠው ይገባ የነበረው ለሕዝብና ለአገር ፍላጎትና ስጋቶች ስለ ነበር ነው፡፡ 
ሐ) በግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እያንዳንዱ የመድረክ አባል ፓርቲዎችና አመራሮች በአባል ድርጅቶች ላይ አፍራሽ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው የሚል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በአንድነት ፓርቲና በአመራሮቹ ላይ የተሰነዘሩ አፍራሽና ጎጂ አስተያየቶችን በግልጽ በማስቀመጥ ፓርቲዎችና አመራሮች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫና መስመር ይመለሱ ዘንድ አባሎችና ሕዝቡም የራሱን ገንቢ አስተዋጽአ እንዲያደርግ ነው፡፡ ከሁሉም በጣም ቅር የሚያሰኘው የመድረክ መግለጫ አፍራሽ አስተያየቶችን ሃሳብን በነፃነት ከመግለጽ መብት ጋር ማያያዙ ነው፡፡ በምን መመዘኛ ነው፡- 
‹‹አንድነት ዶ/ር ነጋሶን ሊቀመንበር አድርጎ ቢመርጥም የአማራ ፓርቲ ወይም የአዲስ አበባ ልሂቃን ፓርቲ መሆኑን መካድ አያስፈልግም›› 
‹‹የአንድነት አዝማሚያ በደቡቦች፣ በአረና እንዲሁም በኦሮሞ ላይ የበላይነትን ለማሳየት ነው››
‹‹ አንድነቶች ፌዴራሊዝምን አይወዱም ፌዴራሊዝሙን የሚጠሉት አማራሮች ናቸው››
‹‹ ከዶ/ር ነጋሶ ውጭ መሪዎቹ አማሮች ናቸው፡፡ ይህን የምለው ስለማውቀው ነው››
‹‹ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ሲዳማ ወለጋ ወ.ዘ.ተ ሄዶ ድምጽ ማግኘት አይችልም››
‹‹ ኦሮሞ አማራ ክልል ሄዶ ምረጡኝ ቢል ድምጽ አያገኝም፡፡ ኦሮሞ ከሆነ 
ለምን ኦሮሞ ፓርቲ አይገባም አማራው ኦሮሞ አገር ሄዶ አይመረጥም›› 
ይህን የተናገሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩልም ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በተደጋጋሚ፡- 
1. የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን መመረጥ የሚያውቀው ኢህአዴግ ነው፡፡ የእሳቸው መመረጥ የኢህአዴግ አሻጥር ነው፡፡ 
2. ስንትና ስንት የዴሞክራሲ አርበኞች ባሉበትና ደጋግመው በምርጫ ያሸነፉ ሰዎች እያሉ አንድ ተወዳዳሪ ብቻ አሸንፋል መባሉ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ 
የደቡብ ህብረት ፓርቲ በአቀረበው የክስ ማመልከቻ፡- 
አንድነቶች ‹‹በአቋራጭ ሥልጣን የሚልፈጉ የነፍጠኛ አቋም ያላቸው ናቸው›› እነዚህ አነጋገሮች አፍራሽና አጥፊ ፕሮፓጋንዳ አካል ናቸው፡፡ ከላይ በአንድነት ፓርቲ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑቱ ‹‹ጠባብ ብሔርተኝነት›› ባህሪያት የማያመላክቱ ከሆነ ምንን ነው የሚያመላክቱት? ሌሎችንም ምሳሌዎችንና ድርጊቶችንም መጨመር ይቻል ነበር፡፡ ሁኔታው በአጭሩ ለመተው ሲባል እንጂ፡፡ 
መ) ግምገማው የአንድነትን ብሔራዊ ምክር ቤትን፣ የሥራ አስፈፃሚውንና በመድረክ የአንድነት ተወካዮች ሚና በትኩረት የተመለከተውና የሰሉ ሂሶችን እንደየ ተጠያቂነታቸው ደረጃ የአሳረፈባቸው እንጂ እንዲያው ችግሮችን ወደ መድረክና አባል ፓርቲዎች የወረወረ አይደለም ወደ ውጭ እንዳየ ሁሉ ወደ ውሰጥም አይቷል፡፡ 
ሠ) በመጨረሻም ግምገማው የመፍትሔ አሳቦችን በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ በመከፋፈል ጠቃሚ አስተያየቶችን ሰጥቷል፡፡ በተለይም ተቀዋሚ ፓርቲዎች አሁን የሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ምህዳር እጅግ ፈታኝ የሆነበት ወቅት በመሆኑ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በአገራችን ጠንካራ መሠረት እንዲይዝ የተቃዋሚ ኃይሎች የመጠላለፍ፣ የመጠፋፋት ፖለቲካ የትም እንደማያደርስ በመገንዘብ በመተጋገዝ በአብሮ መስራት መንፈስ አብሮ መቆም እንዳለባቸው ነው፡፡ የሚያሳየው ከአብሮ መሥራት ውጭ በአገራችን ውስጥ ለውጥ ሊመጣበት የሚችልበት እድል ዝግ እንደሆነ ነው ያመላከተው፣ ያሳየው፡፡ ማንኛውም ፓርቲ የቱንም ያህል ትልቅነኝ ቢልም፣ ትልቅ ቢሆንም ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበትን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ብቻውን ሊወጣው እንደማይችል ነው የታመነበት፡፡ 
እውነታውና የግምገማው ዓላማና ግኝቶች ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ አንድነትን በመድረክ አፍራሽነት ለመፈረጅ መሞከር ‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› ያስመስለዋል፡፡ ይልቁንም አንድነት ለግምገማውም ሆነ በተግባር ያረጋገጠው ለመድረክ ጥንካሬ ብርታትና ወደ ፊት መራመድ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ አሁንም በትጋት እንደሚሰራ በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡ ግምገማዎችን ማካሄድና ውስጣዊ ድክመቶች አንጥሮ በማውጣት ከዚያም ትምህርት አግኝቶና እርምት አድርጎ መራመድ ‹‹ኢህአዴግን ነው የሚጠቅመው፤ ሕዝብን ያሳዝናል›› በሚል መርህ በሽፍንፍን መጓዝ ከአገኘነው ተሞክሮ አፃር ሲታይ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 
በመጨረሻም ለመድረክ የምናሳስበው ቁም ነገር የተፈፀሙን የአካሄድ ስህተት ምክንያት በማድረግ የግምገማውን ይዘት አልቀበልም ማለቱ ማንንም እንደማይጠቅም በድጋሚ ተመልክቶ በይዘቱ ላይ ውይይት እንዲከፈት እንዲያደርግ በአጽኖት እንጠይቃለን፡፡ ይህ እስከሆነ ድረስ የአብሮ መስራቱና መተባበሩ ተግባር አሁንም ይቀጥላል፡፡
ሰኔ 5 ቀን 2ዐዐ5 ዓም
አዲስ አበባ

የግብጽ መከላኪያ ሚንስተር በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ግዜው ገና ነው አሉ

Egyptian armed forces spokesperson Ahmed Mohamed Ali said Thursday that it is too early to talk about military action against Ethiopia over the Grand Renaissance Dam dispute. 
Egypt has other political, economic and social means with which to tackle the matter, Ali stated, adding “military action is usually a last resort.” 
The statement comes after President Mohamed Morsy warned Monday that Egypt does not want war with Ethiopia but will keep “all options open,” piling pressure on an ongoing dispute over the giant dam Addis Ababa is building across the River Nile
In a televised speech to cheering Islamist supporters, Morsy voiced his understanding for the development needs of poorer nations upstream in the Nile basin, but still deployed emotive language to claim Egyptians would not tolerate any reduction in water supplies. 
“Egypt’s water security cannot be violated in any way,” Morsy said. “As head of state, I confirm to you that all options are open.” 
“We are not calling for war, but we will never permit our water security…to be threatened,” the president added. 
Drawing on an old Egyptian song about the Nile, he said: “If it diminishes by one drop then our blood is the alternative.”
Source/www. egyptindependent.com

ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ ጋር መተባባር አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀል ነው።

Friday, June 14, 2013
ከሚፈጽመው ብሔራዊ ወንጀልና ከሚያደርስው አገራዊ ጉዳት አኩያ ነው።
እንደሚታወቅው ወያኔ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በካሃዲ በጸረ ኢትዮጵያውያን የመንደር ስብስቦች ጥላቻ ተረግዞ፤ በግራ ቀደም ፖለቲካ ስንኩል ትርኪምርኪ አመለካከት ተጠምቆ ወንድሞቹን ሲያርድ ሲያሳረድ የኖረ፤ የአባቶቹን የእናቶቹን የአያቶቹን የወንድሞቹን የልጆቹን የዘመዶቹን በርሃብ ማለቅ ግድ ያላለው፣ የማይለው፣ ስብዓዊነት የማይስማው፣ ለርሃብተኞች የመጣውን እርዳታ ቀምቶ ከሱዳን እስከ ሊቢያ ሲቸረችር የኖረ ፤ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ማንነቷን ሕልውናዋን ስንደቃላማዋን የካደ፤ አገር አስገንጣይ፤ በኢትዮጵያ ጠላቶች ያደገ የተመነደገ ፤ አገርና ሕዝብን ዘርፎ የሚያዘርፍ፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግን አጥፍቶ ጠፊ መሰሪ፤ በፋሽቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ የከፋፍለህ ግዛ አስተምህሮ፤ በሂትለርና በስታሊን የድርጅታዊ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ብሂሎችን እራሱን የካነ፤ እራሱ ደንቁሮ አገርንና ሕዝብን፤ የሚያደነቁር፤ የሃገሪቱን ዋና ዋና መሠረታዊ መንግስታዊ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር አድረጎ ፤ በአባሪ ተባባሪዎቹ የሆድ አደር አጋሰስ አጋርነት፤ በባእድ አገር የፖለቲካና የገንዘብ ለጋሲነት እርዳታ ብድር ሰጭነት፤ አማካሪነት እየታገዘ፤ ሕዝብን ሃገርን በንቅዘት በምዝበራ አደህይቶ አገርን ለመበታተን ቆርጦ የተነሳ እኩይ ስብስብ ለመሆኑ፤ ከሆድ አደሮቹ፣ከአባሪ ተባባሪዎቹ በስተቀር ማንም ኢትዮጵያዊ በጥሞና የሚያውቀው ማስረጃዎች በዋቪነት የያዙት፤ በታሪክ መሓደር ተረቆ ያለ የማይታበል ሃቅ ነው ። 
የተዚህ ቀደሙ ወንጀል ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ወያኔ በቡኅ ላይ ቆረቆር ሆኖ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት ለማዘጋጀት ህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ፣ በአድርባይ ሆድ አደር ጠርናፊ አስጠርናፊ ስብስብ አቀንቃኝ ሊቀመኩዋሶች ታዳሚዎች እየታጀበ ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉ የአባይ ውሀ አንድም ጠብታ አይቀነሰብኝም ከምትለው ከስግብግቧ ግብጽ ጋር ጦርነትን እየጋበዘን ነው። 
አገራችን ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገሮች በነጭና ጥቁር አባይ የመጠቀም መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ አያክራክርም ። በአለም አቀፍ ህግ መሰረትም ሌሎች ከወንዞቹ ተጠቃሚ ሀገሮች ውሃ እንዳያገኙ ማድረግ የሚፈቀድ አይደለም። አባይን በተመለከተ ተንኮለኛው አጋብሶ አደር የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ሱዳንና ግብጽን ብቻ ይዞ የወሰነው የውሀ ድርሻ/ክፍፍል ትክክለኛ አለመሆኑም አከራራክሪ ኣይደለም– ግብጽና ሱዳን አሌ ቢሉም። ግብጽ በረሀዋን ልታለማና ሚሊዮኖችን ልታሰፍር በመፈለግ የአባይን ውሀ በተጨማሪ ደረጃ መፈለጓና የተፋሰስ ሀገሮችን ጥቅም ከቶም አላዳምጥ ማለቷም የሚደገፍ አይደለም ። ወያኔ በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ግድብ በሌለ ገንዘብ እሰራለሁ ብሎ የተነሳው ለኢትዮጵያ አስቦ (ወያኔና የኢትዮጵያ ጥቅም ሆድና ጀርባ ናቸውና) ሳይሆን የሕዝባዊ አመጽ ነፋስ ወደ ሀገራችንም እንዳይነፍስ በሚል የህዝብን እይታ ለማደናገር የሸረበው ተንኮል መሆኑ ክርክርን አይጠይቅም ። በኢትዮጵያ እስከዛሬ የተሰሩት ግድቦችና ገና ያላለቀው ግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስትንም ጨምሮ ለሀገሪቷ የመብራት ሀይል ፍጆታ ከበቂ በላይ ሆነው ሳለ ዛሬም በብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ እየተሰጠ እንዳለ ሕዝባችን የሚያውቀው ነው። ግዙፍ ግድብ ለመገንባት መነሳትና ይህንንም ግብጽ እንደምትቃወም እየታወቀ በስልት ጉዳዩን በመያዝ ፈንታ ድንፋታና ፕሮፓጋንዳን ማስቀደሙ፤ ቦንድ ብሎ ሕዝብን ማስጨነቁና ማስገደዱ፤ ሀገር ወዳድ መስሎ ለመቅረብ መፍጨርጨሩ ሕዝብን ሊያደናግር የሚችል አይደለም። የለመዳባቸው የወያኔ የገደል ማሚቴዎችና አደናጋሪዎች –በባድሜ ጦርነት እንዳየነው ሁሉ– ሀገር ልትጠቃ ነው ኡኡ በሚል ወያኔን በመታገል ፈንታ ሕዝብ እንዲደግፍና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ ከወዲሁ የተንኮል ቅስቀሳ፤የማደራጀት ስራና ጫጫታ ጀምረዋል። ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህንን በሚገባ ተገንዝቦ ውጉዝ ከመ አርዮስ መባል አለባቸው። 
የግብጽ ሕዝብ ጠላታችን አይደለም። አንዋር ሳዳት የአባይ ወንዝ ከተገደበብን ጦርነት የግድ ይሆናል ያለውንም አንረሳውም–ዛሬም የግብጽ መሪ ተመሳሳይ አቅዋም በመውሰድ እሱም በበኩሉ ልክ እንደ ወያኔ ውስጣዊ ውጥረቱን ዘወር ለማድረግ ይፈልጋል። ተጨባጭ ሁኔታውንና አቅምን ሳያውቁ ሳይመዝኑ ህዳሴ ግድብ ይሰራል ብለው ጫጫታ ላይ ያሉት ክፍሎች ቅዠት ላይ ናቸው ።
ከግብጽ ጋር ጦርነት ቢነሳ ይህ የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ልክ እንደ ባድሜ። 130 ሺ ዜጋ አልቆ ምን ተገኘ ? ወያኔና አጫፋሪዎቹ–አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃዋሚ ነን ሊሉም ኢትዮጵያ በአባይ ልትጠቀም ስትነሳ በግብጽ ተጠቃች ወይም ልትጠቃ ነው በሚል ሀገር ወዳድ ሁሉ ተነሳ ለማለትና ለማደናገር አቅደዋል። የሚሞኝላቸው አይኖርም ማለትም አይቻልም። ለነገሩ ግብጽ ኢትዮጵያን ሊወር አይችልም– አይሮጵላኖች አስነስቶ ግድብ ተብየውን ሊደበድብ ይችላል። የሚያቆመውም አይኖርም ። ዕድሜ ለወያኔ ስንት ሚሊዮን ብር የፈሰሰበትን አየር ሃይል በትኖ በጀሌዎቹ ሞልቶት ይቀልዳል። መካላከያ ተብየው ሆኖ ሕዝብንም ከፋፍሎና አሽመድምዶ ይገኛል ። 
ኢትዮጵያ መብቷን ለማስከበር አቅም የላትም። ወያኔ የአሜሪካ ሎሌና ተገዢ ነው– አሜሪካ ደግሞ ግጭት ከተነሳ ግብጽን መቃወም ኣንችልም/ ብላ ለወያኔ አስጠንቅቃለች። የወያኔ አገዛዝ ከድጡ ወደ ማጡ ሊከተን ነው እየጣረ ያለው። ይህን መቃወም ደግሞ ለሀገራችን ደህንነት ወሳኝ ነውና ወያኔና ቅጥረኞቹን ወግዱ እረፉ ማለት ግድ ነው።ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ከግብጽ ጋር ግጭቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት የለም ። አገርም በመንግስት ስም የሚገዙዋት ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ የስጠ የሚሰጥ በአገራዊ [በብሔራዊ] ክህደት ወንጀለ የሚጠየቅ የወያኔ ስብስብና ተባባሪዎጩ ናቸው።
ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ከግብጽ ጋር ተፈራርሞ የሀገርን ጥቅም መሽጡንም መርሳት አንችልም። ወያኔ ጫካ ሳለም በግብጽ መረዳቱንና የተከዜ ድልድይን ሊያፈርስ መሞከሩንም የምንረሳው አይደለም። ወያኔ ከስረ መሰረቱ ፀረ ኢትዮጵያዊ ጥላቻን መስረት በማድረግ ከባንዳ አያቱና፤ አባቱ፤ ዘመድ አዝማዶቹ፤ የባኤላ አሹቅ እየቃመ፤ቂጣ እየገመጠ፤በለስ እየጋጠ፤ ጥሕሎ እየዋጠ፤ እሳት ዳር ተኮልኩሎ፤ በባላባታዊ የስልጣን ትንንቅ አባዜ የወደቁ ለጠላት ያደሩ ቅድመ አያቶቹ፤ አባቶቹ ያወረሱትን ቂም በቀል የጎሳ ጥላቻ አፈታሪክ አንግቦ፤ በስነልቦና የበታችነት ማንነት በሽታ ተጠምዶ ያደገበትን ማንነት ባሕሪ መሰረት በማድረግ፤ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ አገር ናት፤ ትግሬን ነፃ አገር እናደርጋለን፤ትግሬ ለትግራዊ የሚል ፋሽታዊ ብሂል አንገቦ ፈጣሪውን ሻቢያን ተገን አድርጎ በባእዳን አገራት አጋርነት አደራጅነት አማካሪነት የፖለቲካና የዲፕሎማቲክ፣ የእርዳታ ገንዘብ ለጋሲነት፤ በወገን ደም ሰክሮ ስልጣንን በመጨበጥ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በሚል ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቅዥት ውስጥ ተዘፍቆ ፤በመላው ኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አባቶች እናቶች ያቆዩንን ታሪክ፤ የአማራ ገዥዎች የጻፉት ተረት ተረት ነው በሚል ስንኩል ቱሪናፋ ዲስኩር ፕሮፓጋንዳ፤ የሽግግር መንግስት፤ነፃነት ውይንም ባርነት፤ብሔር ብሔረስቦች፤ የብሔር ብሔረስቦች እስከመገንጠል በሚል፤በወንድሞቹ ደም የተጠመቀውን ጠብመንጃ በሕዝብና በአገር ላይ ወድሮ፤ ያላንዳች ሕዝባዊ ውክልና፤አገርን አስገንጥሎ፤ አገርን ያለባሕር በር ያስቀረ፤ ትውልደ ኢትዮጵያን የባእዳን ቅጥረኛ ምሁራንን በፋሽስቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ መርዝ የተለወስ ወያኔያዊ ሕገመንግስት እራሱ አስረቅቆ እራሱ በአምሳሉ በፈጠራቸው የጎሳ አቀንቃኝ ድርጅቶችና ሆድ አደር ስብስቦች በማስወስን፤ አገርን በአስራ አንድ ጎሳንና ቛንቛን መአከል ያደረገ በ1928 በፋሽት የኢጣሊያ የአምስት አመቱ ወረራ ጊዜያዊ አገዛዝ ቻርታ የተነደፈውን የቅኝ አገዛዝ ሥነስርዓት አማካኝ ያደረገ፤ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ጕድጒድ አውጥቶ የአፍሪቃ የነጻነት ተምሳሌት የሆነችዋን ውድ ሃገራችንን በጎሳ በቋንቋ ተከፍላ በጥቂት ወያኔ ግርቢጦች፣ የውጭ ቅጥረኛ ጎስኞች መዳፍ ውስጥ ገብታ በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን፤ አገር የጎሳ ባላባታዊ አንባ ገነን ሥነመንግሥታዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ የመከረ ያስመከረ የተገበረ፤ ሕዝብና አገርን የካደ፤ የሃገርና የሕዝብን ጥቀም አሳልፎ የሰጠ የሚሰጥ፤ አጥፊ፣ መስሪ ስብስብ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ምግባሩ ሥራውም በጥፋት ላይ ጥፋትን ያነጣጠረ መሆኑ ለማንም አገር ወዳድ ግልጽ ነው። ወያኔ አገርን ለባዕድ ሻጭ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ነበረ–አሁንም ነው። ለዚህም ነው ከባዕድ ጋር የፍጥጫን ጎዳና መርጦ ሀገራችንን ለጥቃት ሊያጋልጥ እየተፍጨረጨረ ያለው። በመሆኑም ነው ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀለኛ፣ አገርና ሕዝብ ገዳይ አንባገነን ስነስርአት ጋር አገራዊ ትብብር ሊኖር የሚያስችል ምንም ጉዳይ የሌለው። በአባይ ስም ሕዝብን በጦርነት ለመማገድ፣ አገርን ለጥቃት አሳልፎ ለመስጠት፣ ከሚያሴሩ ጠርናፊ አስጠርናፊ የወያኔ ቅጥረኞች ተንኮል እራሳችንን አውጥተን፣ ሕዝብና አገርን በጋራ እንታደግ። ለነጻነት ትግል በጋራ በመቆም አምርረን እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ !!!

Wednesday, June 12, 2013

አልጃዚራ ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች ሲል ዘግቧል! ማናቸውንም እርምጃ ለመውሰድ በሩ ክፍት ነው .ግብጽ

አልጃዚራ ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች ሲል ዘግቧል። አቶ ባድር የፖለቲካ ቁማር እንደሆነ የገለጹትን ይህን የሞሃመድ ሞርሲን ንግግር አልጃዚራ ሁኔታው የተባባሰ የማስመሰል ጥረት ማድረጉ ይህ የዜና አውታር ገለልተኛ መሆኑን አጠያያቂ ያደርገዋል ሲሉ የገለጹት ቀድሚ ጋዜጠኛ የነበሩ አስተያየት ሰጪ ናቸው። 
ይህን ያሉትም ሚዲያው በማጋነን ለአንድ አካል ያደላ ዜና ጽፏል በሚል ነው። በተለይም ”ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ያሉት የሞርሲ ንግግር ኢትዮጵያ ለልማት ብቻ እንጂ ግብጽን ለመጉዳት አለመፈለጓ እየታወቀ በመሆኑ ይህንን ክግብጽ የናይል ጥገኝነት እና የጥፋት ፍራቻ ጋር ማያያዝ እንዲሁም የኢትዮጵያን አመለካከት ወደ ጎን መተው ፍትሃዊነት የለውም ሲሉ አበክረው ተናግረዋል። 
በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የአባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው። 
ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት -ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እስከ ወታደራዊ ጥቃት ድረስ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የመከሩበት ስብሰባ በይፋ ታየ፤ 
ይሁንና የግብጽ መንግስት-ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ስለታሰበው እርምጃ ሲመክሩበት የነበረው ስብሰባ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት መተላለፉ፤ግብጽ -ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መፈለጓን የሚያሳይ ተራ ጨዋታ ነው በሚል ብዙዎች ትኩረት ሳይሰጡት ቆይተዋል 
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት የግብጹ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ፦ኢትዮጵያ በምትሠራው ግድብ ሳቢያ ወደ ግብጽ ከሚፈሰው የ አባይ ወንዝ የጠብታ ያህል ከቀነሰ አገራቸው ግብጽ ማናቸውንም እርምጃዎች ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ዝግጁነቱ እንዳላት አስታውቀዋል። 
ከ ኢትዮጵያ ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ፤ ግድቡን ለማስቆም የሚያደርጉት ጥረት ካልተሳካ ግን ሁሉንም አማራጭ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደዱ ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት። 
ኢትዮጵያ – አቅጣጫውን የቀየረው የወንዙ ፍሰት ሀይል ካመነጨ በሁዋላ ተመልሶ በመደበኛው መስመር እንደሚፈስ እና በግብጽም ሆነ በሱዳን ላይ የሚፈጥረው ነገር እንደማይኖር ደጋግማ ብታሳውቅም፤ፕሬዚዳንት ሙርሲ ፈጽሞ የግብጽ የውሀ ደህንነት ሊነካ አይገባም! በማለት የ ኢትዮጵያን ምላሽ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። 
“የ አገሪቱ ፕሬዚዳንት እንደመሆኔ መጠን ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰዱ በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቃለሁ” ነው ያሉት -ፕሬዚዳንት ሙርሲ። 
በማያያዝም፦”ግብጽ የዓባይ ስጦታ ከሆነች፤ዓባይ የግብጽ ስጦታ ነው”ብለዋል-በስሜት ውስጥ ሆነው በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር። 
እንደ አንድ ታላቅ ህዝብ የግብፃውያን ህይወትና ኑሮ ከ ዓባይ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሙርሲ፤ ፍሰቱ በ አንዲት ጠብታ ከቀነሰ ያለን ቀሪ አማራጭ ደማችን ነው”ብለዋል። 
የግብጽን ተደጋጋሚ ዛቻ ተከትሎ የ ትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦<<ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም>>ብሏል። 
ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ለትብብር ፣ ለወዳጅነትና ለጋራ ጥቅም ያላትንም ፅኑ እምነት በወቅቱ ግልፅ አድርጋለች ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ ፥ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ብሄራዊ የናይል ጉባኤ በተሰኘው ስብሰባ ላይ የግብጽ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሚኒስትሮችና ሌሎችም በተገኙበት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ አፍራሽ መልዕክቶች ተላልፈዋል ብላል ። 
በዚህ ረገድ በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል ። 
ጦርነትና ሌሎች አፍራሽ ስልቶችን ስለመጠቀም የሚቀርቡት ሀሳቦች ያረጁና ያፈጁ ፣ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከሙ ፣ እና ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች እንደሆኑ የገለጸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለሰኮንድም አታቆምም ብላል። 
ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተሉ ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ሁለቱ መንግስታት የቃላት ጦርነት ውስጥ የገቡት በውስጣዊ አስተዳደራቸው የተፈጠረባቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመጠምዘዝ እንደሆነ በስፋት አስተያየት ሢሰጡ ይደመጣሉ።

Tuesday, June 11, 2013

Amid dam row, Ethiopian refugees in Egypt protest rising xenophobia

Ethiopian refugees complain of increasingly frequent assaults and harassment amid Egypt's ongoing dispute with Addis Ababa over latter's planned Nile dam project
Amid dam row, Ethiopian refugees in Egypt protest rising xenophobiaHazel Haddon, 

Dozens of Ethiopians protest in front of the 
Egypt UNHCR office on Sunday. (Photo: Al-Ahram Arabic news website)


Protesters, mostly from the Oromo ethnic group, said that embers of their community had faced several violent attacks in Egypt in recent weeks.
The apparent trend comes against the backdrop of mounting tensions between Ethiopia and Egypt over a plan by the former to build a dam on the Blue Nile.




"We have some reports of people being attacked just because of their nationality,"

 protest organiser Jeylan Kassim told Ahram Online.
"We need the UNHCR's protection; and we need the
 UNHCR to raise the awareness of the Egyptian community 
[about our plight]."
Egyptian media has been dominated by speculation regarding
 the new Nile dam project since Ethiopian engineers began partially
 diverting the course of Blue Nile on 28 May to prepare a site for the
 new dam's construction.
Last week, fiery rhetoric reached a climax when a group of leading
 Egyptian politicians, speaking at a meeting with the president, suggested
 sabotage or covert interference in Ethiopian affairs to prevent the dam from
 negatively affecting Egypt’s share of Nile water – without realising the meeting
 was being broadcast live on television.
Ethiopian refugees at Sunday's protest argued that they were suffering the brunt
 of mounting Egypt-Ethiopia tensions.
"Two of my friends were beaten; one was sent to hospital, but they refused to trea
t him," claimed Mulis, an Ethiopian refugee in Egypt since 2011, while speaking to
 Ahram Online.
According to UNHCR Deputy Regional Representative for Egypt Elizabeth Tan, 
a number of Ethiopian refugees in recent weeks have reported being evicted from
 their homes or losing their jobs because of their nationality, along with facing difficulties
 obtaining medical care at Egyptian hospitals.
"The UNHCR is concerned about these allegations and calls on all Egyptians to
 differentiate between the political dispute with the Ethiopian government and their
 treatment of Ethiopian refugees who fled their country seeking asylum in Egypt,"
 commented Tan in a written statement to Ahram Online.
"I was threatened by the owner of the building I live in," Mulis told Ahram Online.
 "He said, 'since you are cutting the river from us, I won't give you shelter'."
"But we're not part of the problem," he added. "We're against the Ethiopian
 government, and against its policies."
Around 2,500 Ethiopian refugees and asylum seekers, of different ethnic groups,
 are currently registered with UNHCR Cairo.
english.ahram.org.

Friday, June 7, 2013

“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”(የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው።
በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር።
shemelis2--620x310ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን ቅስም የሰበረው የ1997 ዓ ም ምርጫ ጣጣውና ቆፈኑ እንዲሁ በቀላሉ የሚለቅ እንዳልሆነ በወቅቱ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር።
“ሁለት አስርት ዓመታት ወደኋላ ተመልሰናል” ተብሎ የተዘጋውን በር የበረገደው ሰማያዊ ፓርቲ ከህዝብ ባገኘው ድጋፍ አዲስ አበባን የተቃውሞ ጎርፍ አጎረፈባት። ሰላማዊ ሰልፉ ሰላማዊና የተሳካ እንደነበር ኢህአዴግ ራሱ ተናገረ። ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ የሶስት ወር ጊዜ ከሰጠ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
አዲስ አበባ አንድ ለአምስት፣ የጎንዮሽ፣ የሽቅብ፣ የህቡዕ፣ የገሃድ፣ የዘር፤ የታማኞች፣ የበጣም ታማኞች፣ የልማት፣ የአነስተኛ ስራ ፈጠራ፣ የጾታ፣ የዘር፣ የእድሜ፣ የተፈጥሮ ሁኔታ፣ የጥቅም ወዘተ የፈጠረው አደረጃጀት አፈር ድሜ መብላቱ ያስጨነቀው ኢህአዴግ ሰልፉ ተበትኖ ሲያበቃ ላንቃውን አላቀቀ።
እንደ ገበጣ ጠጠር በፈለገበት ጉድጓድ የሚወረውራቸውን ቅምጥ አሽከሮች ለመግለጫ አሰማራ። ለስምንት ዓመታት ታፍኖ የኖረ ህዝብ መቦረቁ አስደነገጠውና ከፊልም ክምችት ህግ መዝዞ ለመክሰስ ያመች ዘንድ ህጸጽ እንዲነቀስ አዘዘ። አቶ ሽመልስ ከፈረሹበት ፍራሽ ተነስተው በምርቃና የአፋቸውን ለሃጭ እንኳን በወጉ መቆጣጠር እያቃታቸው በሉ የተባሉትን ተፉ። አቶ ሬድዋንም ሰው በሌለበት የ2002 ምርጫ በስድብ አቶ መለስን በማስደሰታቸው ባገኙት ሃላፊነት ለጌቶቻቸው ምላስ ሆነው ህዝብ አወገዙ። እሳቸውም ተፉ።
አይ ጋዜጠኛነት – “አትነሳም ወይ”   
አንድ ህዝብ ለተቃውሞ ሲወጣ ሊያወግዝ፣ ሊዘልፍ፣ የፈለገውን ጉዳይ በማንሳት ሊራገም፣ ለተነሳበት ጉዳይ “ተነሱ” ብሎ በፍርሃትና ሚና ባለመለየት የተቀመጡትን ለመቀስቀስ፣ ለማበረታታት ነው። ከድሮ ጀምሮ አገርና ህዝብ እንዲተባበሩ ሲፈለግ፣ መሪዎች ሲገዝቱ በሠንደቅዓላማና የሁሉም ማተብ የሆነችውን አገር ስም በመጥራት ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን በጨነቀው ጊዜ ባወገዘውና በሚጠላው ሠንደቅ ሲነግድበት ታይቷል። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ባዋረዱት “ባንዲራ” እንዲገነዙ የፈቀደ ፓርቲም ነው። ታዲያ ከጥንት ጀምሮ ሰንደቅ ዓላማውን “ማተቤ” እያለ የሚጠራ ህዝብ የሰንደቁን ስም እየጠራ “አትነሳም ወይ” በማለት ማዜሙ እንዴት ይበዛበታል? ደግሞስ ኢህአዴግና በዙሪያው የሰበሰባቸው አሽከር ባለስልጣኖቹ ስለ ሰንደቅ ክብር የመቆርቆር ሞራሉስ አላቸው?
ኢህአዴግን “ውሸትህ ሰለቸን” እያሉ ሲረግሙት ከነበሩት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል “ለምን አዲሱን ሰንደቅ ዓላማ ያዝክ” በሚል የሚጨቃጨቁ አስር የማይሞሉ ሰዎች በካሜራ አድኖ ሰልፉን “ህገ ወጥ” ለማስመሰል የዳዳው ጋዜጠኛ ሙያውንም ሆነ ራሱን ስለማርከሱ ጉልህ ማሳያ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው።
ስለ ሰንደቅዓላማ ይነሳ ከተባለ ዜናው “በሰልፉ ላይ ባንዲራ ለምን አልወጣም? ሰንደቀዓላማውን የነፍሱ ያህል የሚያመልክ ህዝብ እንዴት አስቻለው? ሰንደቅዓላማ የተሸሸገበትስ ምክንያት ምንድን ነው?” የሚለውና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ነበሩ።
በባድመ ጦርነት ወቅት በዳግም ጥሪ አገሩን ሊታደግ የመከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀለው /የደርግ ሠራዊት ሲባል የነበረውን/ ወገን ኩርፊያ ለማስታገስ “የቀድሞውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ” በባላደራነት በመስጠት ኢህአዴግ የሰውን ልጅ ለማይጠቅም ጦርነት መማገዱን ለሚያወቁ ዜጎች ኢህአዴግ ስለ ሰንደቅ
flag-e1370495735528-300x157 የመቆርቆር መብት እንደሌለው ይረዳሉ። እንዲህ ያለው “ድርጅታዊ ክህደትና ዓላማ ያለው አታላይነት” ዝም ተብሎ አስር ሰዎች ተሟገቱ ብሎ የክስ ማመቻቺያ ሪፖርት ማዘጋጀት ጋዜጠኛ አያስብልም። ሰዎቹ እነማን ናቸው? አንድ ባንዲራ ብቻ እንዴት ሊታይ ቻለ? ማን አመጣው? እንዴት መጣ? ብዙ መጠየቅ የሚቻልበት ጉዳይ ሆኖ ሳለ መታለፉ አስገራሚ ይሆናል። ለነገሩ ሰልፉን አስመልክቶ አቋም ይዞ የጻፈ የአገር ውስጥ ሚዲያም አላጋጠመኝም። ለለቅሶ ግጥምና ሙሾ የደረደሩ ጋዜጠኞች ለህዝባዊ ተቃውሞ የሰጡት ሽፋን ደረጃው ዝቅ ቢልም ከመወረፍ አያድናቸውም።
አትነሳም ወይ በሚል መፈክር ማውረድና የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቅ ህግን መተላለፍና የፍርድ ሂደት ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሆነ የሚዘግብ ዘጋቢ የሙያው ባለቤቶች ነን ለሚሉ ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ነው። አቶ መለስ እንደ ቴአትር ቤት ድራማ ይጫወቱበት በነበረው ፓርላማ ፊት፣ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍ ዝግጅት፣ በፖለቲካ እስረኞችና ተከሳሾች ላይ አስቀድመው ውሳኔ ሲሰጡና ብይን ያሰሙ በነበረበት አገር “እስረኞች ይፈቱ” ብሎ መጠየቅ ወንጀል ሆኖ “ህግ ተጥሷል” ሲያስብል መስማት ሞቶ መበስበስ ሲታሰብ የሚዘገንነውን ያህል ይቀፋል። ለዚያውም በአቶ ሽመልስ ከማል አንደበት ሲነገር።
“የስካር መግለጫ”
የአቶ በረከት ተላላኪ የሚባሉትና ለታይታ የሚኒስትር ታፔላ የተለጠፈባቸው አቶ ሽመልስ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ ከንግራቸው በላይ መነጋገሪያ የሆነው በወቅቱ የነበሩበት የሙቀት ስሜት ነበር። አፋቸው ዳርና ዳር አረፋ ይደፍቃቸው ነበር። ሲያመነዥጉ የዋሉትን የጫት መጠንና አይነት መዘርዘር ቢከብድም ከፍራሽ ላይ ተጠርተው የችኮላ መግለጫ እንደሰጡ መደረጉን መሸሸግ አይቻልም። እዚህ ላይ “ምን አገባህ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል። ምን አልባትም የግል ጉዳይ እንደሆነ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። እኔ እስከማወቀው ግን ሰክሮ የተከበረ ህዝብ ፊት መቅረብ፣ መናገር እስኪያቅት ድረስ አይን እያጉረጠረጡ ለህዝብ ማውራት አግባብ አይደለም። አንድ ኪሎ ጫት ከ100 ብር በላይ በሚሸጥበት ሁኔታ ቀን በቀን ጫት ማመንዠክ ከመንግሥት ሠራተኛ (ባለሥልጣንም ጭምር) ወርሃዊ ደመወዝ ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ለስርቆትና ሙስና ስለሚዳርግ የሚወገዝ ነው።
አንድ ክስተት ትዝ አለኝ፡፡ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቦሪስ ዪልሲን በአልኮሆል አፍቃሪነታቸው ብዙ የተባለባቸው ነበሩ፡፡ እርሳቸው ከሥልጣን ለቅቀው በስፖርተኛነታቸው የሚታወቁትና በጁዶ የጥቁር ቀበቶ ተሸላሚው ቭላዲሚር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ ጥቂት ዓመታት በኋላ ግመገማዊ ጥናት ተደረገ፡፡ በውጤቱም በዘመነ ዪልሲን እጅግ አሻቅቦ የነበረው የሰካራም ቁጥር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ በኋላ መቀነሱ ይፋ ሆነ፡፡ ኢትዮጵያስ ድሮና ዘንድሮ…?
ወደጉዳዬ ስመለስ እንግዲህ እኚህ ሰው (ሽመልስ) ናቸው “ህገወጥ” በማለት የህዝብን ቁጣ የፈረጁት። የሚላላኩለት ኢህአዴግ ህግ አክባሪ ሆነና ይህ የታፈነ ህዝብ ህገ ወጥ ተብሎ ተፈረጀ። ኢህአዴግና ፍርድ ቤት የተለያዩ አካላት ተደርገው ታዩና “የፍርድ ሂደት ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ፣ ቀናውን የፍርድ ሂደት ለመበረዝ …” የተቃጣ ሰልፍ ሆኖ ቀረበ። ዳሩ ኢህአዴግ የሚሰበስባቸውን ሰዎች ለሚያውቁ፣ አቶ ሽመልስን በቅርብ ለሚያውቃቸው ጉዳዩ አይገርምም። ስርዓቱ የቆመው እንዲህ ባሉ ሰዎች መሆኑ ግን ያሳዝናል። አሁን ከሶስት ወር በኋላ በሚካሄደው ሰልፍ “የባለሥልጣኖች የጫትና የሺሻ ኮታ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን” የሚል ጥያቄ ቢቀርብ ማን ቀርቦ “ሰልፉ ህግ መንግስቱን የሚጻረር፣ ጸረ ሰላም ሰልፍ ነው” ይል ይሆን?
“ይህ መንግስት አይመጥነንም”
ለዚህ ጽሁፍ መነሻዬ ይህ ሃሳብ ነው። መንግስት ህዝብን ካልመጠነ ችግር ነው። የደህንነትና ፖሊስ ሃይል ህዝብን ከሚሰልል ይልቅ ከህዝብ ጋር ሆኖ አገርን በጋራ ሊጠብቅ እንደሚገባ የሚጠይቁ አገር ወዳዶች “የሚመጥናቸው መንግስት” አለማግኘታቸው አሳሳቢ ነው። 22 ዓመት ሙሉ ጥላቻ ቢሰበክም እርስ በርሱ ሳይጫረስ እዚህ ደረጃ መድረሱ የሚያናድዳቸው የኢህአዴግ አውራ መሪዎች “ዛሬም ድረስ አልረኩም” የሚሉ ሰልፉ ላይ ነበሩ። እነዚህ ሰዎች ሲሉ የነበሩት ጉዳይ ከመድረክ ተነሳ። “ይህ መንግስት አይመጥነንም” ሲባል ተጮኸ። ድጋፍ ተሰጠ። በማይመጥናቸው አገዛዝ መተዳደር የማይፈልጉ የፍርሃት ቀንበራቸውን ሰበሩ። ሰማያዊ ፓርቲ ይህን ገድል በልጅነቱ ሰራ።
ሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች በሚጥናቸው ፓርቲ መተዳደር እስኪችሉ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ ተናገረ። አሁንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አስተጋቡ “አዎ” አሉ። ይህ እውነት ነው። የማይመጥን አገዛዝ የሚወከለው አገዛዙ በሚሰበስባቸው ተላላኪዎቹ ነው። በማይመጥነው አገዛዝ መመራት ያንገሸገሸው ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ ሲገባ “ህገ ወጥ ነህ” የሚሉት አስቀድሞ በካርዱ፣ ከስምንት ዓመት በኋላ በድምጹ፣ በየጊዜው በተለያየ መልኩ የሚያወግዛቸው “ገለባ” ባለጊዜዎች ነው። አስቀድሞ አትመጥኑንም የተባሉ፣ ቢናገሩ ማን ያደምጣል? የተሻሉ የሚባሉ ባለስልጣናት ቢኖሩም ዝምታን እስከመረጡ ድረስ ለህዝብ የሚሰጡት ዋጋ የለምና አብረው ከመደመር አይድኑም።
“አለ ገና” – ተባለ!
ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ እንዳስታወቀው ላቀረባቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች መልስ ካልተሰጠው ከሶስት ወር በኋላ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ሌሎች ፓርቲዎችም የሰማያዊ ፓርቲን ፈለግ ተከትለው በየክልሉና በሚታወቁ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ዝግጅት ላይ እንደሆኑ አስታውቀዋል። በኦሮሚያ የኦህዴድ መፋዘዝን ተከትሎ የከረረ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። እንደ ጠላት እየታየ የሚፈናቀለው የአማራ ክልል ተቃውሞ ማካሄድ ከጀመረ ከወረዳ ወረዳ የሚዘል እንደሚሆን ይታሰባል። በደቡብ ሲዳማ የተቃውሞ ሰልፍ ከጀመረ ከርሟል። በቅርቡ በተካሄደው የማሟያ ምርጫ ወቅት አምጾ ነበር። አሁንም በቋፍ ላይ ነው።
የተቀመጠበት መቀመጫ እንደ ምጣድ የጋለበት ኢህአዴግ አስቀድሞ ወደ ማስፈራራት የሮጠው አቶ መለስ  “በ97 የተፈጸመው ዓይነት ጥፋት ሁለተኛ አይታሰብም” በማለት የተናገሩትና ያስተላለፉት ትዕዛዝ “ኦርኔል” ስለታወሰው ነው “አለ ገና” መባሉ እንቅልፍ ስለነሳው ነው። ተቃውሞው ወደ ክልሎች ይዛወራል መባሉ ቅዠት ውስጥ ስለከተተው ነው። ሁሉም ወደ ፊት የሚታዩ ቢሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ መፈቀዱ የሚመሰገን ነው። ተሰለፉ፣ ተቃወሙ ብሎ ፈቅዶ ለምን ጎነተላችሁኝ ብሎ ለክስና ለእስር መሯሯጥ ደግሞ ግለቱን የሚጨምር በመሆኑ ቢቀር የሚል የሚለውን ምክር እንደዜጋ ለመሰንዘር እወዳለሁ። ከሰሜን አፍሪካ ወደተነሳው የውሃ ፖለቲካ አውድማ ተምዘግዝገን ገብተናልና ቢያንስ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ወደሚያስችለን መንገድ ብናመራ ይበጃል። የአሁኑ ሰልፍና ተቃውሞ ጅምር ነው። ኢህአዴግ ከሰማ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አንድ የውስጥ ጉዳያችንን እንዝጋ:: ህዝብ ወሳኝ አካል እንዲሆን የፈሰሰውን ደም እናስብ። በፍርሃቻና በስካር መግለጫ በማስፈራራት ህብረት መፍጠር አይቻልምና። 
(የጎልጉል ሪፖርተር ካለበት የዘገበው)

Oromo refugees attacked in Egypt as the Nile crisis deepens

Created on Friday, 07 June 2013 08:14

(OPride) – An Oromo interpreter for UNHCR in Cairo was beaten, denied police services, and subsequently charged extra for medical care on Thursday in retaliation for Ethiopia’s diversion of the Nile River to build a $4.7 billion hydroelectric dam, according to locals.
“Our friend was beaten seriously by a group of Egyptian youth and he was nearly killed,” wrote Abdulkadir Noor Gumi, a Cairo-based community activist, in a frantic appeal letter sent to OPride.com. “He was beaten by chain, metal, and stick...he had a head injury and other injuries on his body.”
When Ethiopia began diverting the flow of the Nile on May 28 for its so-called Grand Ethiopian Renaissance Dam – the largest in Africa with a 6000 megawatts capacity, the Egyptian blogosphere and media exploded as many called for swift action. Immediately following the announcement, an angry mob gathered in front of the Ethiopian embassy in Cairo to enounce the move, according to media reports.
Egypt is demanding Ethiopia halt the dam construction saying it “adversely impacts Egypt's ability to generate electricity and provide water for irrigation.” Ethiopia says the diversion won’t reduce the flow of the Nile and is insisting on a dialogue to find a more equitable sharing arrangement.
Ethiopia is contesting a colonial-era agreement signed in 1929 between Egypt and Great Britain. The agreement was later revised in November 1959 giving Egypt 55.5 billion cubic meters and Sudan 18.5 billion cubic meters. During the revision, the other eight upstream countries, including Ethiopia, were not consulted.
On Mondayafter a tripartite commission made up of experts from Sudan, Egypt, and Ethiopia – tasked to study the potential impact of Ethiopia’s dam on downstream states – released its final report, Egyptian politicians in a meeting with President Morsi, were inadvertently heard discussing plans to sabotage the project, attack the dam or arm Ethiopian rebels, unaware that their meeting was being broadcast on live TV.
Thursday’s attack in Cairo on an unnamed Oromo national, the second incident in the last week, underscores the grave threat facing Ethiopian refugees living in Egypt. Many of these refugees left Ethiopia fleeing repression and fear persecution if they return home. Several hundred UNHCR-recognized Oromo and other refugees of Ethiopian origin reside in Egypt, according to community estimates. Activists report the situation remains tense and have urged all persons of Ethiopian and Oromo origin to stay in their houses until the situation stabilizes, if ever.
Following Thursday’s incident, Egyptian police refused to take down the report of what transpired saying that the attack was deserved.
“The policeman who was writing the report aimed [a gun] at me...saying that we deserved to be killed,” said Gumi in an email recounting his traumatic experience.
Their troubles did not end there.
“After that we were referred to a hospital to do some check up for our injured friend,” Gumi continued. “In the hospital, we found the same issue, we are asked our nationality for record, we were told that ‘you are going to divert our Nile and you have to pay more for hospital.’”
Even after paying double the amount of normal fees for seeing a doctor, according to Gumi’s report, other patients in waiting room told them, “you deserve[d] it,” after learning their nationality.
The Oromo Community in Cairo is holding a peaceful demonstration in front of UNHCR and is asking all concerned individuals to reach out to Egyptian authorities on their behalf.
 Mohammed Ademo

Sudan and Egypt clash over Ethiopia's Nile dam

A rare disagreement has occurred between Sudan and Egypt over the possible impact of an Ethiopia dam on the downstream Nile basin countries.
The controversial Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) could see the course of the Blue Nile tampered with and Egypt has warned it would spare no effort to guarantee its share of the water.
But Sudan is warning of a possible water war between the Nile Basin countries because of Egypt’s ‘provocative' stance.
Sudanese government spokesman Ahmed Bilal has asked Egypt to stop what he called provocations after an Egyptian opposition leader described Khartoum's stand on in the issue as disgusting.
An Egyptian opposition leader, Mr Ayman Nour, publicly described the Sudanese stand on the Nile as disgusting.
Meanwhile, the US has asked the three countries to resolve the problem amicably through dialogue.
Mr Bilal demanded, at a press conference in Khartoum on Wednesday, that Cairo works with Sudan to safeguard Egypt’s interests instead of resorting to provocations.
He added that Sudan would get many benefits from the dam, including better supply of electricity and year-long regulation of the Blue Nile’s flow.
Egypt has warned that all options were open to protect its share of the Nile waters.
"We cannot let even one drop of Nile water be affected," President Mohammed Morsy said during talks with political and religious leaders broadcast live on state television on Tuesday.
President Morsy also wrote on his official Twitter account: "It is necessary that we take steps to ensure Egyptian water security."
"The current situation necessitates unity among our ranks to prevent any threat against Egypt," added President Morsy.
The border
Egyptian Cabinet also met and issued a statement saying it opposed all projects that could affect the flow of the Nile.
Egypt said it had planned "several scenarios" depending on the outcome of an assessment to be conducted by the three governments.
In Khartoum, the Foreign ministry said Sudan would not be affected by the project, stressing in a statement that there were agreements and consultations between Sudan, Egypt and Ethiopia.
"Sudan respects the agreements to cooperate with those two countries (Egypt and Ethiopia) in matters that concern sharing the waters of the Nile and sharing mutual revenues," the ministry said.
Egypt believes its "historic rights" to the Nile are guaranteed by two treaties of 1929 and 1959, which give it 87 per cent of the Nile's flow as well as veto power over upstream projects.
But a new deal signed in 2010 by upstream Nile Basin countries, including Ethiopia, allows them to work on river projects without Cairo's prior agreement.
The agreement signed in Uganda has endorsed new water sharing between the Nile basin’s 11 countries.
Ethiopia has begun diverting the Blue Nile 500 metres from its natural course to construct a $4.2 billion (3.2 billion euro) the GERD hydroelectric project.
The first phase is expected to be complete in three years, with a capacity of 700 megawatts.
Once complete, the dam will have a capacity of 6,000 megawatts.
The project, in Ethiopia's northwestern Benishangul-Gumuz region near the border with Sudan, was launched in April 2011 by Prime Minister Meles Zenawi.
The Blue Nile joins the White Nile in Khartoum to form the mighty Nile River, which flows through Sudan and Egypt before emptying into the Mediterranean.

Wednesday, June 5, 2013

“የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ …”- ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡ ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ -1. የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤
2. በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤
3. የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው

  • ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው የሰላማዊ ሠልፍ ጥሪ፣ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች ወጥተው ተሰተውለዋል፡፡ አራት ኪሎ ቀበና አካባቢ ከሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መነሻውን ያደረገው ሰላማዊ ሠልፉ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አድርጐ ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት መናፈሻ ደርሶ፣ እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ የተለያዩ መፈክሮችንና ተቃውሞዎችን በመንግሥት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኅንና በአንዳንድ የግል መገናኛ ብዙኅን ላይ አሰምተዋል፡፡
ሠልፈኞቹ ለመንግሥት ካቀረቧቸው ጥያቄዎችና መፈክሮች መካከል፣ ‹‹ዜጐችን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ የመደራጀት መብታችን ይረጋገጥ፣ በኑሮ ውድነት የጐበጠው ትከሻችን እረፍት ያስፈልገዋል፣ ሕገ መንግሥትን የሚፃረሩ አፋኝ አዋጆች ይሰረዙ፣ የመንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባትን አጥብቀን እንቃወማለን፣ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ለፍትሕና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞች ይፈቱና አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ . . . ወኔ የሌለው የአገረ ሸክም ነው፣ ውሸት ሰለቸን . . . ›› የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም እንደተናገሩት፣ አንድ ሕዝብ የሚገባውን መንግሥት ሊያገኝ ይገባል (A people get a government deserved)፣ ሥርዓቱን በትግል መለወጥ ካልተቻለ በትግል የምትፈልገውን ታገኛለህ ብለው፣ በ1997 ዓ.ም. ለዲሞክራሲ ሥርዓት ብቁ መሆኑን ያረጋገጠ ሕዝብ ኢሕአዴግ የሚመራው ሥርዓት እንደማይገባው ገልጸዋል፡፡
ለኢሕአዴግ ሥርዓት መለወጥ ወጣቱ ትልቅ ሚና እንዳለው፣ ‹‹መሬት ላራሹ›› ብሎ በመነሳት ኅብረተሰቡን ቀፍድዶ ይዞት ከነበው የፊውዳል ሥርዓት በማላቀቅ ትግል ውስጥ፣ ግንባር ቀደም እንደነበረ የገለጹት ዶ/ር ያዕቆብ፣ ደሙን ገብሮ ከጨፍጫፊው ደርግ ያላቀቀን ወጣት ዛሬ ነጥፏል የሚባለው አባባል፣ ከሰው ተፈጥሮና ከእውነት ውጭ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
‹‹ሽብርተኞች እንደምን አደራችሁ›› በሚል ምፀታዊ ሰላምታ ንግግራቸውን በዕለቱ ያሰሙት የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ደግሞ፣ ‹‹ይኼ የወጣቶች ሠልፍ ምልክትና መንገድ ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ የእስልምና መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች እስካልተፈቱ፣ ተፈናቃዮች ካሳ ተከፍሏቸው ወደ ቀያቸው እስካልተመለሱ፣ ሙስና እስካልጠፋ፣ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት ተገቢው የፖሊሲ ማስተካከያ እስካልተደረገባቸው ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ ትግሉን በአስተዋይነት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም መስዋዕትነት ሊከፈል እንደሚችል በማከል ገዥው ፓርቲ የተባሉትን እንዲያስተካክል የሦስት ወራት ጊዜያት መስጠታቸውንም ገልጸዋል፡፡ ‹‹አሁን ያለው ሥርዓት ታሪካችንን፣ ክብራችንንና የዕውቀት ችሎታችንን አይመጥንም፤›› ካሉ በኋላ፣ ሕዝብ የመጠየቅ መብት እንዳለውና መንግሥት መፍትሔ የመስጠት ግዴታ እንዳለበትም አክለዋል፡፡
ሰላማዊ ሠልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም በመጠናቀቁ መንግሥትም ዕውቅና የሰጠው ቢሆንም፣ በተለይ መንግሥት የሠልፉን ዓላማና እንቅስቃሴ በሚመለከት ‹‹ሕገ መንግሥቱን የጣሰ›› ብሎታል፡፡
የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ለመገናኛ ብዙኅን በሰጡት ማብራሪያ፣ በሃይማኖት ሽፋን ሲካሄድ የነበረው የፀረ ሕገ መንግሥት እንቅስቃሴ ቀድሞውንም ስውር አጀንዳ የነበረው መሆኑን፣ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ መገለጡን ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ሠልፉን ላልተገባ ተግባር ማዋሉን የተናገሩት አቶ ሬድዋን፣ የፖለቲካ አቋምን በሃይማኖት ሽፋን አድርገውና ቀላቅለው እንዲንቀሳቀሱ ማድረጉና በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ በሰላማዊ ሠልፍና በሁካታ ለማቆም የደረጉት እንቅስቃሴ፣ ሕገ መንግሥቱን የጣሰና ተገቢ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡
አገር እመራለሁ የሚል ፓርቲ ከአጀንዳዎቹ አንዱ የሚሆነው የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ መሆኑን የገለጹት አቶ ሬድዋን፣ የሕግ የበላይነት የሚረጋገጠው ደግሞ የፍርድ ቤትን ነፃነት በማክበር መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ሰላማዊ ሠልፍ የሚወጣለትና ፍትሕ ሊጠየቅለት የሚችል ሰው በፍርድ እንዳይጠየቅ ሲደረግ፣ ሠልፍ የማይወጣለትና ፍትሕ ሊጠየቅለት የማይችል ሰው ዝም ሊባል የሚችልበት አካሄድ፣ ለአገር ሰላም ሊያሰፍን እንደማይችልና የዜጐችንም መብት ሊያረጋግጥ እንደማይችል አስረድተዋል፡፡ ሐሳብን በጽሑፍም ሆነ በሰላማዊ ሠልፍ መግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብት በኢትዮጵያ የተከበረ መሆኑን፣ ነገር ግን በፖለቲካ ሽፋንነት የአክራሪነት አጀንዳን ማራመድ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌዎች የሚጥስ መሆኑን አክለዋል፡፡
መንግሥት በሰላማዊ ሠልፉ ተደናግጦ ነገሮችን ከማቃለልና ሕዝቡን በፖለቲካ ንግግር ከማሸማቀቅ በስተቀር፣ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው የተናገሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሲሆኑ፣ የመንግሥት ንግግር ፖለቲካዊ መሆኑን የሚያሳየው የተሰላፊዎቹን ቁጥር በሁለትና በአንድ ሺሕ አሳንሶ ሲናገር መታየቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲም ሆነ ሕዝቡ ሕገ መንግሥቱን እንዳልጣሱ የገለጹት ኢንጂነር ይልቃል፣ ‹‹ጀሃዳዊ ሀረካት፣ አኬልዳማ›› በማለትና የተለያዩ ሕገወጥ ሥራዎችን በሕግ በተያዙ ጉዳዮች ላይ በመሥራት በፍርድ ቤቶች ላይ ተፅዕኖ የፈጠረው ራሱ መንግሥት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሰላማዊ ሠልፉ የመንግሥትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባትን ለመከላከል፣ ዜጐች አመለካከታቸውን የማራመድ፣ የፈለጉትን ሃይማኖት የመከተልና የማምለክ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር ለማድረግ መሆኑን የገለጹት ኢንጂነሩ፣ የእምነት ነፃነት የመጀመሪያውና የጋራ ነፃነት በመሆኑ ያንን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው አውስተዋል፡፡
መንግሥት ይኼንን ክፍል ለምን ነካችሁ ማለቱ እንዳስገረማቸው አስረድተው፣ ፓርቲው መጠየቅ ያለበት ኅብረተሰቡ ያነሳውን ጥያቄ ባያነሳ እንደነበርም አክለዋል፡፡ ኅብረተሰቡ በመንግሥት ትልቅ በደል እንደደረሰበት ሲናገር፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥትም ማንሳት እንዳለበትና ግዴታው መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ ፓርቲያቸው ማንኛውንም እምነት የማክበርና ፓርቲያቸውም ዜጎች የእምነት ሥርዓታቸውን እንዲያካሂዱ እንደሚፈቅድ አስረድተዋል፡፡
ሕዝብና መንግሥትን ከሁለት ዓመታት በላይ አጣልቶ የቆየንና እስካሁንም ለውጥ ያልታየበትን ንፁኃንን ሽብርተኛ ማድረግ የመንግሥትን ተዓማኒነት ከማሳጣት በስተቀር ሌላ የሚያመጣው ነገር እንደሌለ መንግሥት ሊገነዘብ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
አገርን እንደሚመራ ፓርቲ ኢሕአዴግ መሥራት ያለበት ሕዝብንና መንግሥትን የሚያቀራርብ ሥራ እንጂ፣ ማላገጥና ንግግር ማሳመር የሚያዋጣው እንዳልሆነ ኢንጂነር ይልቃል አስረድተዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ትልቅ ችግር ላይ ነች›› የሚሉት ፕሬዚዳንቱ የኑሮ ውድነቱ ሰማይ መድረሱን፣ ሙስና ተቋማዊ መሆኑን፣ የታሳሪዎች ብዛትና ያላግባብ የሚፈናቀሉ ዜጐች ከምንም በላይ ማሳያ መሆናቸውንና ዓለም ሁሉ ያወገዘው፣ ኢትዮጵያውያን በነፃነት የመነጋገር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ገፎታል ያሉት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉም ሌላው ችግር መሆኑን አክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም ለመንግሥት የሚያቀርበው ጥያቄ እነዚህን ችግሮች ተመካክረን እናስተካክል የሚል መሆኑን ኢንጂነር ይልቃል ጠቁመዋል፡፡
በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠናቀቀ ሰላማዊ ሠልፍን የፖለቲካ ንግግር በማሳመር ሕዝብን ለማሸማቀቅ መሞከር የገዥው ፓርቲ ድርጊት ብቻ ሳይሆን የአምባገነን መሪዎች ባህሪ በመሆኑ፣ ‹‹አትነሳም ወይ›› የሚለውን መዝሙር ሁሉም ወጣት እንዲያዳምጥና ሁሉም ከተኛበት ተነስቶ ለመልካም ዓላማ መሠለፍ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

Breaking News: Armoured Vehicles Surround Ethiopian Embassy In Cairo

Posted by Ethio Tribune on June 5, 2013
Awramba Times – The Ethiopian embassy in Cairo is surrounded by heavily armed personnel and armoured vehicles. Ethiopian citizens, both refugees and Ethiopian-passport holders, are savagely harassed and beaten by ordinary Egyptians and the police everywhere they move.
According to our sources, it is very difficult for Ethiopians to move around and many people are starving as they fear for their life to go out and buy foodstuff and drinking water. Egyptians are preparing a massive demonstration against Ethiopia to be held next Friday.
On the other hand, Ethiopian Ambassador to Egypt Mohamed Dirrir met with Egyptian opposition leader and former Secretary General of the Arab League, Amr Moussa in Cairo today. Ambassador Mohamed Drirr has a two hours meeting with Amr Moussa on the recent developments on the Nile and has made clear that Ethiopia has no any intention of harming egypt or affecting its access to the Nile waters.
source: awrambatimes.com

የብሄር ግጭትና የኤርትራ ታጣቂዎች ሁመራን አመሷት

በምዕራብ ሁመራ ማይካራ መቻች በተከሰተ የብሔር ግጭት የሰዎች ህይወት ጠፋ፤ መንግስት ግጭቱን ለማስቆም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ በአካባቢው ተከታታይ ግጭቶች ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
ሱዳን ጠረፍ ላይ ቅዳሜ ግንቦት24 ቀን 2005 ዓ.ም በብሄር ምክንያት የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ የ12 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉንፉን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ጨምረው ገለፀዋል፡፡ በኢትዮጵያና ሱዳን ጠረፍ አካባቢ በምትገኘው መቻች በረሃ በቀን ስራ የተሰማሩ ሰዎች በብሄር እየተቧደኑ መገዳደል ከጀመሩ ሶስት አመታት ማስቆጠራቸውን ያስታወሱት ምንጮቻችን መንግስት ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ሚና ለመጫወት አለመፍቀዱ የሟቾቹንና የተጎጂዎቹን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጓል፡፡
ሰራተኞቹ በወሎ፣በጎጃም፣በጎንደርና በራያ ተወላጅነት ተቧድነው በካራ፣በዱላና በእሳት በፈጠሩት ግጭት የሰው ህይወት ተቀጥፏል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው አካባቢውን ጠሚያውቁ አስተያየት ሰጪዎች “መንግስት በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄ ተመልሷል በማለት የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል በሚያከብርበት ወቅት በጎሳ ፖለቲካ እንዲህ አይነት ዘግኛኝ ድርጊቶች እየተፈጠሩ የሰው ህይወት መብላታቸው ጥያቄዎቹ በተገቢው መንገድ ላለመመለሳቸው ማሳያ ይሆናል” ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በዚሁ በሁመራ በረከት ወረዳ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ለመዝረፍ የሚሞክሩ ሽምቅ ተዋጊዎች በተለያዩ ጊዜያት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲያስጨንቁ እንደነበር የጠቀሱት ምንጮቻችን በቅርቡ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ከሚጠብቁ ሚልሺያዎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በሁለቱም ወገን ህይወት መጥፋቱን አጋልጠዋል፡፡ በተደጋሚ የማያባራ የተኩስ ልውውጥ መስማት በአካባቢው የተለመደ እንደሆነም የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በሁመራ ስለተከሰተው የግጭት ለማጣራት የአካባቢውን ባለስልጣናትና የፖሊስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡