Monday, April 29, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ



ኢትዮጵያ በቻይና ብድር እየተንበሸበሸች ነው
በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ታላላቅ ስምምነቶች ይጠበቃሉ
ከአፍሪካ ጋር መሳ ለመሳ የገባችው ቻይና በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ 4.5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለማበደር ወስናለች። ከአባይን ግድብ የሚመነጨውን ሃይል የማስተላለፍና የማከፋፈል ጣቢያ ለመገንባት ከሚፈለገው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 85 በመቶውን ለመስጠት መዋሰኗን የመንግስት ሚዲያዎች ዘገበዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘወትር እንደሚደረገው የቻይና የኤሌክትሪክ ፓወር ኢኪውፕመንት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ግንባታውን በሰላሳ ቀን ውስጥ ለመጀመርና በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ ተስማምቷል። ስለዚህ ብድሩ ከቻይና ኪስ ወጪ ተደርጎ ወደ ቻይና ኪስ ይዛወራል።
በሌላ ተመሳሳይ ወሬ ለአትዮጵያና ለጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ የሚውል 3.3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት የቻይና መንግስት መወሰኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ስምምነቱ ከወር በኋላ ለሚደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ከሚመጡ ከፍተኛ ቻይና ባለስልጣናት ጋር የቻይና ኤግዚም ባንክ ባለስልጣኖች አዲስ አበባ ተገኝተው የስምምነቱን ፊርማ እንደሚያኖሩ ጋዜጣው ገልጿል።
ከብድር ስምምነቱ በፊት በተጠናቀቀው የግንባታ ስራ ተቋራጭ ውል መሰረት ከሰበታ ተነስቶ ጅቡቲ የሚደርሰውን የባቡር መስመር ሁለት የቻይና ኩባንያዎች እንደሚያከናውኑት ሪፖርተር በስም ጠቅሶ አመልክቷል። አንደኛው ኩባንያ የአዲስ አበባን ቀላል የባቡር መስመር ዝርጋታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።”
የመከላለያ ጄኔራሎች በታንታለም ንግድ ዝርፊያ ተሰማርተዋል”
የመከላከያ ጀነራሎች በታንታለም ማዕድን ዝርፊያ ላይ መሰማራታቸውን ኢሳት አስታወቀ። ኢሳት ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው የመከላከያ ሰራዊት ኩባንያ በአካባቢው የመንገድ ስራ ተቋራጭ በመሆን መንገድ እየሰራ ሲሆን፣ ለመንገድ ስራ ተብለው የተመደቡት ተሽከርካሪዎች ከመንገድ ስራ ይልቅ የታንታለም ማእድንን እየዘረፉ በሶማሊላንድ በኩል ያሻግራሉ። ማዕድኑንን  የማውጣቱን ስራ ከሚሰራው የቻይና ኩባንያ ጋር ሽርክና በመፍጠር ዝርፊያውን እንደሚያካሂዱም ኢሳት አመልከቷል።
ይህ ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደጋግመው አቤቱታቸውን በማቅረብ፣ ጥሬ እቃውን ወደ ውጭ መላኩ እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ያስታወሰው ኢሳት፣ በቅርቡ መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ፣ የማእድን ማውጣቱን እና መላኩን እንደገና ለመጀመር በመወሰኑ እነዚህ የህወሀት ጄኔራሎች ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር አክሲዎን በመመስረት ታንታለም በጅቡቲ በኩል መላክ መጀመራቸውን ሰራተኞቹ አስረድተዋል።tantalum
አገር ወዳድ የሆኑ ሰራተኞች “ይህ ማእድን እያለቀ ነው፣ ታንታለም ስትራቴጂክ ማእድን ነው፣ ማእድኑ አሁን ካለቀ አገሪቱ ለወደፊቱ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ታጣለች” በማለት መናገራቸውን ኢሳት አመልክቷል። የህወሀት ጄኔራሎች ዝርፊያውን የሚፈጽሙት ከዞን ባለስልጣናት ጋር በመዛመድ መሆኑን ምንጮች እንደነገሩት ኢሳት ጠቁሟል።
ምንም እንኳ በአካባቢው ካሉ ተወካዮች ለማረጋገጥ ባይችልም፣ በህገወጥ መንገድ ከሚወጣው ማእድን ጨረር ጋር በተያያዘ በርካታ የአካባቢው ሰዎች መሞታቸውን ኢሳት ሰራተኞቹን በመጥቀስ ይፋ አደርጓል።
መንግስት እገዳው ከመጣሉ በፊት 80 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ታንታለም የሚሸጠው ቻይና ውስጥ እንደነበር ያመለከተው ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ወገንን ሪፖርት ለማካተት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካ ተናግሯል።
ታንታለም ሊተካ የማይችል እጅግ ውድ የሆነ ማእድን ሲሆን፣ የሞባይል ስልኮችን፣ ኮምፒዩተሮችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ ለተለያዩ የኬሚካልና የፋርማሲዩቲካል ውጤቶች መስሪያ፣ ለኤሮስፔስ፣ ለኢነርጂና ባልስቲክ ምርቶች በግባትነት ያገለግላል። ቀንጢቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቦ እንደነበር ኢሳት በዘገባው አስታውሷል።
የሳዑዲ የመከላከያ ሚኒስትር በኢትዮጵያ አቤቱታ ተነሱ?
የሪፖርተር አስቂኝ ዜና የሳምንቱ መዝናኛ ተደርጎ ተወስዷል። ዜናው የሚጀምረው “የህዳሴውን ግድብ የተቃወሙት የሳውዲ ልዑል ከሃላፊነታቸው ተነሱ” የሚል ነው። የሳዑዲ አረቢያ  ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ በግብጽ ተደርጎ በነበረ የዓረብ አገሮች የውሃ ምክር ቤት ኮንፍረንስ በመገንባት ላይ ያለውን “የህዳሴ ግድብ” መቃወማቸውን በማስረጃነት ያሳየው ሪፖርተር ከዜናው ግርጌ ሚኒስትሩ ስለተነሱበት ምክንያት የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ያለው ነገር እንደሌለ አመልክቷል።
Khaled_Bin_Sultanሚኒስትሩ  በአገራቸው ፖለቲካ ውስጥ አወዛጋቢ ጉዳይ ማንሳታቸውን ፣ በዚህም ምክንያት  ከሃላፊነታቸው  መነሳታቸውን  የሚገልጹ ጠንካራ አስተያየቶች ከሳዑዲ እየወጡ ነው። ጉዳዩን  የሚከታተሉ ወገኖች የሚኒስትሩ መነሳት አገራቸው ውስጥ እያራመዱ ካለው ያልተለመደ እንቅስቃሴ ጋር ከመያያዙ ውጪ አባይ ግድብን አስመልክቶ ከተናገሩት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ለጎልጉል ተናግረዋል።
የህዳሴው ግድብ በማንኛውም ምክንያት የመፍረስ አደጋ ቢገጥመው ሊያጠራቅም የሚችለው 70 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ውኃ ሱዳንን ሙሉ ለሙሉ ያጠፋል፡፡ ከዚህ አልፎም በግብፅ የአስዋን ግድብ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ነበር ምክትል የመከላከያ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡ በዚህ የኢትዮጵያ ግድብ በዋናነት ተጎጂ የምትሆነው ግብፅ መሆኗን፣ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግብፅ ከዓባይ ውኃ ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላት በመሆኑ ነው ብለው ነበር፡፡ በማከልም ኢትዮጵያ በዚህ ግድብ አማካይነት እያደረገችው ያለ እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ይልቅ ፖለቲካዊ ትንኮሳው ያመዝናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዓላማ ፍፁም ፖለቲካዊ ሴራ መሆኑን በመግለጽ መናገራቸውን ሪፖርተር በዜናው መጨረሻ አስታውሷል። ኢትዮጵያም ባለስልጣኑ ለተናገሩት የሳዑዲ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥበት መጠየቋ አይዘነጋም።
ኬኒያና ኢትዮጵያ ለወደብ ግንባታ በጋራ ብር ሊያፈላልጉ ነው
በኬኒያ ተፈጽሞ በነበረ የጅምላ ግድያ ተከስሰው ጥፋተኛ የተባሉት አዲሱ የኬኒያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና በጠ/ሚ/ር haile uhuruሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ልዑክ ኬንያ ተገኝቶ በልማትና በግልጽ ባልተነገረ ጉዳይ መወያየታቸው ተሰምቷል።
የኢህአዴግ ልሳናትና የተለያዩ መገናኛዎች ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን በጋራ ለሚጠቀሙበት ግድብ ማስገንቢያ ገንዘብ በጋራ ለማፈላለግ መስማማታቸው ተመልክቷል። በሶማሊያና በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።
አቶ ሃይለማርያም አወሮፓ ያደረጉትን “የቃል ማደስ” ጉዞ እንዳከናወኑ ወደ ኬኒያ ማምራታቸው ሶማሌ ውስጥ ከኬኒያ ጋር መስራት ስለሚገባቸው ጉዳይ የተቀበሉትን የቤት ስራ ለመተግበር ያስችላቸው ዘንድ እንደሆነ ግምት አለ።
አቶ ሃይለማርያም ናይሮቢ በነበራቸው የአንድ ቀን ቆይታ አብረዋቸው ከተጓዙት መካከል ወታደራዊ ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።
በአዲስ አበባ አፍሪካ ፍልስጤምን ነጻ ስለመውጣት ልምድ ልታካፍል ነው
በፍልስጤም ጉዳይ በሚቀጥለው ሳምንት የሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ እንደሚስተናገድ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል አስታወቀ። የኢህአዴግ አንዱ የንግድ ተቋም የሆነውና ዜና ከመንግስት እየወሰደ ለመንግስት የሚሸጠው ዋልታ ጉባኤው አዲስ አበባ ስለሚካሄድበት ምክንያት አላስታወቀም።
Ethiopian President Meles Zenawi (R) and PLO chair
(Photo: Getty Images)
“ጉባዔው የፍልስጤማውያን የማይገሰሱ መብቶችና ለፍልስጤም ሉአላዊና ነጻ አገር የአፍሪካውያን አጋርነት” በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2005 ዓ ም እንደሚካሄድ ዋልታ አመልክቷል። ጉባኤው አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ በመውጣት ሉአላዊነቷንና ነጻነቷን ለመጎናጸፍ ያደረገችውን ተጋድሎ እንደ ልምድ ተወስዶ ውይይት ይደረግበታል። ፍልስጤም ባለችበት አስተዳደር የገጠሟት ችግሮችና አስተዳደሩ በዓለም አቀፍ ሕጎች ያለበትን ኃላፊነትና ተጠያቂነትም ይገመግማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋልታ በዘገባው አስፍሯል።
በጉባዔው ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሚስተር ካርሎስ ሎፔዝ፣ የፍልስጤማውያን የማይገሰሱ መብቶች ኮሚቴ ሊቀመንበር አብዱ ሰላም ዲያሎ፣ የፍልስጤም ነጻ አውጪ ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጣሂር ካሊድ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።
ለእሥራኤልና ፍልስጤም ሰላም ሂደት ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰቡ እያበረከቱት ያለውን ድርሻም ጉባዔው እንደሚያጤን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የላከው መግለጫ ጠቅሶ ዋልታ ዘግቧል። እስራኤልን በጉባኤው ላይ ስላላት ሚናና ስሜት በዘገባው ላይ የተባለ ነገር የለም።
አንደበት
. . . እነዚህ “ሕገ ወጦች” ከሰሜንም ይምጡ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ ይፍለሱ ከመሀል አገር ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ደግሞ ዜጎች በፈለጉት አካባቢ ሄደው ለመስራት፣ ሀብት ለማፍራትና ለመኖር እንደሚችሉ ደንግጓል፡፡ እናም እነዚህ “ሕገ ወጥ” የተባሉት ሰዎች ከተወለዱበት ክልል ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ሌላ ክልል ሄደው ኑሮአቸውን መመስረታቸው ከቶም ወንጀል ሊሆንና ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ሊባሉ አይችሉም፡፡ ደን መጨፍጨፍና ሕገ ወጥ ሰፈራ ማካሄድ ግን ወንጀል ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ፤ ዜጎች (ሰሜንም ይወለዱ ደቡብ) ሕግ ጥሰው፣ ስርዓት አፋልሰው፣ ጥርስ ሰብረው፣ ቋንጃ ቆርጠው፣ ንብረት ዘርፈው፣ ቤት አቃጥለው፣ እንስሳ ነድተው፣ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተው ቢገኙ በአገሪቱ ሕግ መሰረት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲቀጡ ይደረጋል እንጂ “ወደተወለዳችሁበት ቀዬ ተመለሱ” ማለት ተገቢም ሕጋዊም አይመስለኝም … እኔ አቶ አያሌው ጎበዜን ብሆን ኖሮ ሁልጊዜ አማራ ተፈናቀለ፣ አማራ ተፈናቀለ የሚለውን መስማት ስለማልፈልግ ይህንን እርምጃ እወስድ ነበር፡፡ አማራ ክልል እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ ለተወላጆቹ በቂ የሆነ መሬትም ሀብትም እንዳለው አምናለሁ፡፡ የክልሉን ተወላጆች ይሄ “የነፍጠኛነት” ውርዴ አለቅ ብሏቸው ካልሆነ በስተቀር ጉራ ፈርዳ ድረስ የሚያስወርድ ሁኔታ ያለ አይመስለኝም …” አቶ አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞው የፓርላማ አባል ለሰንደቅ ጋዜጣ በዘር ላይ የተመረኮዘ መፈናቀልን አስመልክቶ ካቀረቡት ጽሁፍ የተወሰደ
ታዳጊዋን የደፈሩ አዛውንት 11 ዓመት እስር ተፈረደባቸው
አዛውንቱ የፈጸሙት ተግባር የአውሬ ነው። የልጅ ልጃቸው የምትሆን ታዳጊ አስገድደው በመድፈር ላልተፈለገ እርግዝና ዳርገዋታል።injustice1 አዲስ አድማስ የፍርድ ሂደቱን አስመልክቶ እንደሚከተለው ዘግቧል። በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ግራባ ፊላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ የ14 ዓመቷን ታዳጊ አስገድደው የደፈሩ የ60 ዓመት አዛውንት፣ የአስራ አንድ ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸው፡፡ የታዳጊዋ ወላጆች በእርሻ ሥራ ላይ የቀጠሯቸው እኚሁ አዛውንት፣ ወሲባዊ ጥቃቱን የፈፀሙት ቤተሰቧ‹‹ቤት ጠብቂ›› ብለው ወደ ገበያ መሄዳቸውን አረጋግጠው እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል። ታዳጊዋ የደረሰባትን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ወዲያው ለቤተሰቦቿ አልተናገረችም፡፡
ወራት እየተቆጠሩ ሲሄዱ ግን ሰውነትዋ እየወፋፈረ፤ ሆድዋ እየገፋ መሄዱን የተረዱ ቤተሰቦችዋ ጥርጣሬ አድሮባቸው ጠየቋት፡፡ ታዳጊዋ የደረሰባትን ተናገረች፡፡ ያኔ የአምስት ወር እርጉዝ ነበረች። ቤተሰቦችዋ ጉዳዩን ለፖሊስ አመለከቱና ክስ ተመሠረተ፡፡ ከትናንት በስቲያ በዱግዳ ወረዳ የዋለው ችሎት፤ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀማቸውን በማረጋገጡ የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደፈረደባቸው፤ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር አስቻለው አለሙ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ዘወትር እንደሚባለው ሁሉ ፍርዱ አነስተኛና ከበደሉ ጋር የሚጣጣም እንዳልሆነ ግን አልተዘገበም።
የሱዳን ታጣቂዎች በመተማ አርሶ አደሮችን ገደሉ
በሰሜን ጎንደር በመተማ ዞን ደለሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ለረዥም ዓመታት ግብር እየከፈሉ የሚኖሩበትን  ህጋዊ መሬት ለቀው እንዲወጡ በወረዳው እንደተወሰነባቸው ሪፖርተር ምንጮች ጠቅሶ ዘገበ። የሱዳን ታጣቂዎች ሶስት አርሶ አደሮችን መግደላቸውም ተገልጿል።
አርሶ አደሮቹ ለዓመታት ከኖሩበት ርስታቸው እንዲፈናቀሉ መታዘዙን የወረዳው አስተዳደርና የክልሉ የአካባቢ ጥበቃና የመሬት አስተዳደር ባለስልጣን ሃላፊ አስተባብለዋል። ይሁን እንጂ ሶስቱ አርሶ አደሮች መገደላቸውን ሳያስተባብሉ አምነዋል።
soldierየመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ መኮንን አርሶ አደሮቹ በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል መባሉ እውነት መሆኑን ቢያረጋግጡም፣ ምክንያቱ ግን ከድንበር ልኬትና ከእርሻ ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የመተማ አርሶ አደሮች ድንበር ተሻግረው የመስፈር ሁኔታ መኖሩንና ከሱዳኖቹም በኩል ተመሳሳይ ባህሪ እንደሚታይ የገለጹት አቶ ተስፋ፣ ከሱዳኖች በኩል አንድ ታጣቂ ተገድሎ እንደነበርና በዚያ ድርጊት ቂም ይዘው ግድያውን ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡ የድንበሩን ጉዳይ በፀባይ መያዛቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆነውንና የማይሆነውን መሬት ለመለየት በጂፒኤስ ለክተው መጨረሳቸውንም አሳውቀዋል፡፡ ዝቅተኛ የመሬት መጠን ያላቸው አርሶ አደሮች በገመድ ተለክቶ እንደሚከፋፈሉም አክለዋል፡፡
አቶ ተስፋ የአርሶ አደሩን መፈናቀል በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አርሶ አደሩ መሬቱን አልተነጠቀም፡፡ ቦታው ተለክቷል፡፡ መሬቱ ሲለካ አርሶ አደሩ መረጃ ስላልደረሰውና ወጥቶ ስላላየ የሚደረገውና የሚወራው አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አርሶ አደሩ አግባብ ባልሆነ መንገድ አግበስብሶ የያዘው መሬት አለ፡፡ የሚመለከተውን ያህል ይሰጠዋል፡፡ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እየተሠራ በመሆኑ ማንም አይፈናቀልም፡፡ ሲለካ ለምን ይለካል ብሎ የሚያኮርፍ አለ፡፡ ይኼ ደግሞ ሥርዓትና አሠራር በመሆኑ ሕጉን ጠብቆ ይሠራል፤›› ማለታቸውን ሪፖርተር አመልክቷል።
በአዲስ አበባ የትራፊክ መብራቶች ከጥቅም ውጪ ናቸው
በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መብራቶች ቆመው ቢታዩም አገልግሎት እንደማይሰጡ አዲስ አድማስ ዘገበ። ጋዜጣው ተገልጋዮችንaddis-ababa-city-traffic በማናገርና ተዘዋውሮ በመመለክት እንደዘገበው በከተማዋ ካሉት 26 የትራፊክ ማስተናበሪያ መብራቶች ውስጥ አገልግሎት የሚሰጠው አንዱ ብቻ ነው። አዲስ አድማስ ባይገልጸውም የትራፊክ መብራቶቹ ምሶሶዎች ቀለማቸው የወየበ። የተገነጣጠሉና  የከተማውን ውበት እንዲያበላሹ ታስበው የተቀመጡ መስለዋል።
በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎችንና የአዲስ አበባ የትራፊክ ጽ/ቤት ችግሩን እንዳመኑ ያመለከተው አዲስ አድማስ ዜናውን አስገራሚ አድርጎ ያቀረበው የማይሰሩትን የትራፊክ መብራቶች ለመጠገን የመለዋወጫ ችግር መከሰቱን በመግለጽ ነው። ጥገና ለማካሄድ ተፈልጎ የመለዋወጫ እቃ ሲጠየቅ “እንዲህ ያለ እቃ አለ እንዴ”  የሚል መልስ እንደሚሰጥ የጠቀሰው ጋዜጣው የአዲስ አበባ የትራፊክ መብራት ዘመን ያለፈበትና ሊጠገን አይችልም ብሏል። ከባቡር ግንባታው ጋር በተያያዘ አዲስ የመብራት ተከላ ለማካሄድ ጨረታ መውጣቱንም አመልክቷል።

ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ዛሬም በኦስሎው፣ ታሪክ ሰሩ!


ወያኔ በልማት ስም ገንዘብ ለመቃረምና ደጋፊ ለመመልመል አቅዶ ከሳምንት በፊት በስታቫንገር አንዲሁም በዛሬው እለት ደግሞ በኦስሎ ስብሰባ ለመጥራት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው የውርደት ካባቸውን ለብሰው መሄድ እጣፋንታቸው እንዲሆን የግድ ሆኗል፡፡ እንደሚታወቀው ባለፈው ሳምነንት ማለትም እንደ ኢሮፓ አቆጣጠር ሚያዝያ 20፣ 2013 በነበረው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያዊያን ከየተለያዩ ቦታዎች በመሰባሰብ የወያኔ አምባሳደር በስዊድን የሆኑትንና የዲያስፖራ ተወካዩን ከስብሰባ በማባረር ከፍለውበት የነበረውን አዳራሽ ተረክቦ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን አጀንዳ እና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን እርዳታ የሚሆን ገቢ እንዲሰበሰብና ይህን አምባገነንና ዘረኛ ቡድን መታገል የሚቻለው በ አንድነት መሆኑን ሁሉም የሚስማሙበትና እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል እንዳለብን አስምረው፣ ከ አንድ ሳምንት በሗላ ለሚደረገው የወያኔ ገቢ ማሰባሰቢያ ይህንኑ ድል መደገም ያለበት መሆኑን በመስማማት ነበር የተለያዩት፡፡
ይህንንም ተከትሎ የስታቫንገሩን የወያኔ ፕሮግራም ለማክሸፍ ከፍተኛው ሚና የተጫዎተውን ግብረ-ሓይል በማጠናከር ሳምንቱን ሁሉ ውጤታማ ሥራ ለማድረግ የሙስሊም ወንድሞቻችንን፤ ኦሮሞና ሶማሌ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ሌት ከቀን  ሲሰራ ሰነንብቷል፡፡ የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ከፍተኛ ዝግጅትና ቅስቀሳ ሲከታተሉ የነበሩ የወያኔ ቅጥረኞችና አገላጋዮች ስብሰባ ሊደረግ ታቅዶበት የነበረውን አዳራሽ የስብሰባው ሰዓት ሊደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሲቀረው የመሰብሰቢያው አዳራሽ በፀጥታው፣ በጥራቱና በደህንነቱ በታወቀው ራድሰን ብሉ ሆቴል እንደሚካሄድ አስታውቀው፣ ስብሰባውን ለመሳተፍ ግን ህጋዊ መታወቂያ እንደሚያስፈልግ ተገልፆ የሞባይል አጭር መልዕክት ተላለፈ፡፡ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ስብሰባው ይካሄድበታል ተብሎ ከታሰበበት አዳራሽ አካባቢ ከአስር ሰዓት ጀምሮ ወደዚያ የሚያልፈውን የወያኔ ቅጥረኛ ለመቃኘት ወረውት የነበረ ቢሆንም ዘግይቶ የመጣውን አጭር የሞባይል መልዕክት ማለትም የስብሰባ ቦታ መቀየር በመረዳት፣ ወደዚያው ተመመ፡፡
ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን ከመድረሳቸው በፊት በገቡት የወያኔ ተወካዮች በመበሳጨቱ ወደ ሆቴሉ ለመግባት በነበረው ግብግብ፣ ምንም ዓይነት ሰው እንዳይገባ ተከለከለ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ለማስቆም ከ15 መኪና በላይ የፖለስ ሃይል የተጨመረ ቢሆንም የጀግኖች ኢትዮጵያዊአንን ቁጣና እልህ መቋቋም አልቻሉም ነበር፡፡ አካባቢው የግልና ተቃውሞውም ህገወጥ እንደሆነ በማስረዳት  ከአካባቢው ገለል ለማድረግ ቢሞክሩም አልተቻለም፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በሆቴሉ የታደሙት የወያኔ ቅጥረኞት ወጥተው ካልሄዱ አካባቢውን ለቀን አንሄድም፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለንበማለት አብዘተው ጮሁ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሁለት ሴቶች እህቶቻችንና ዘጠኝ ወንድሞቻችን ለሰዓታት ታስረው የተፈቱ ሲሆን፤ ፖሊስም የተቃውሞውን ሓይለኝነት በማየት የወያኔ ተወካዮችንና የስብሰባው አስተባባሪዎች በጓሮ በር ማለትም በመኪና ማቆሚያ በኩል ከህዝብ ሰውረው ከሆቴሉ ሸኝተዋቸዋል፡፡
ከዚያም ኢትዮጵያዊያን አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ እያሉ በመዝለል ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሚከተሉትን የፎቶ ትዕይንት ይመልከቱ፡፡
DSC_0010DSC_0012DSC_0015DSC_0922DSC_0931DSC_0938Arrestationarrestation 2.

Oromo-Norwegians Stage Protest Against Neo-Neftegna TPLF in Oslo – 11 Arrested for Civil Disobedience


Gadaa.comAccording to a Norwegian paper dagbladet.no and Google Translate service, Oromo-Norwegians protested against TPLF officials who were holding a meeting at the luxurious 4-Star Radisson Blu Scandinavia Hotel in Oslo, Norway, on April 28, 2013. The paper also said 11 were arrested for a short-period for civil disobedience, a form of nonviolent protest.
The Neo-Neftegna TPLF, which has been militarily occupying Oromiyaa since 1991, was forced to cancel its meeting. TPLF is using the overseas meetings to divert the attention from the ongoing land-grabs (farmland thefts)deforestation and gross human rights violations, including lack of press freedom, in Oromiyaa and elsewhere in the colonized South in the Ethiopian empire.
More coverage here:
The Gulele Post
Ayyaantuu.com
Gadaa.com

Saturday, April 27, 2013

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስለሶማሊያው ጦር ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጡ

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ያሏትን ወታደሮቿን በማውጣት ኃላፊነቷን አታሣንስም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታወቁ፡፡ሚኒስትሩ ይህንን የሃገራቸውን አቋም ያሳወቁት ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ሰሞኑን ለፓርላማቸው ባደረጉት ንግግር ሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ጦር በተመለከተ በአፍሪካ ኅብረት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው እንደነበረ ይታወሣል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የመንግሥታቸውን የስምንት ወር የሥራ አፈፅፀም ሪፖርት ባቀረቡበት የፓርላማው ማብራሪያቸው ወቅት የሠራዊታቸውን ከሶማሊያ መመለስ ለማፋጠን እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያየኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት ነው ያሉትን አልሻባብን ከመታገልና ከማክሰም ወደኋላ እንደማይሉ ለሶማሊያ ሕዝብና መንግሥትም ማሳወቃቸውን ገልፀው አሁን ባለው ሁኔታ ጦሩን እንደማያስወጡና ከውጊያውም እንደማያፈግፍጉ አመልክተው ነበር፡፡
ከጥቂት ሣምንታት በፊት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁዱር ከምትባለው ስትራተጂክ ከተማ ድንገት መውጣታቸው በአካባቢው የፀጥታ ክፍተት መፍጠሩና የአልሻባብ ተዋጊዎችም ወዲያው የኢትዮጵያን እግር መውጣት ተከትለው ከተማይቱን መቆጣጠራቸው ይታወቃል፡፡
ይህ ሁኔታ ደግሞ በነሐሴ 2003 ዓ.ም ዋና ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ ለቅቀው እንዱወጡ ለተገደዱት ፅንፈኛ ናቸው ለሚባሉት ቡድኖች የተወሰነ የመሬት ድል እንዳስጨበጣቸውም ተሰምቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሁዱርን ለቅቆ መውጣት የአፍሪካ ኅብረቱና የመንግሥታቱ ድርጅት ጦር – አሚሶም አክራሪዎቹን ጠራርጎ ለመምታት እየተንቀሣቀሰ ነው በሚባልበት ጊዜ ኢትዮጵያ ከአልሻባብ ጋር ከገጠመችው ውጊያ “እያፈገፈገች ለመሆኗ ፍንጭ ይሰጣል” የሚሉ ግምቶችንና ንግግሮችን በስፋት አስነስቶ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ትናንት – ሐሙስ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያ ጦር ከሁዱር እንደሚወጣና ቀጥሎም ከክልሉ ዋና ከተማ ከባይዶዋ እንደሚነቅል ቀደም ሲል ተነግሮ ገልፀዋል፡፡

“ይህ ጉዳይ የተዛባ መረዳትን ያዘለ በመሆኑ ማብራሪያ ይፈልጋል፤ ኢትዮጵያ ስለመውጣቷ ማንንም አላማከረችም ወይም የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አልሰጠችም የሚለው ጥያቄ መሠረተ-ቢስ ነው፡፡ ሊያውቁ የሚገባቸው ከመውጣታችን በብዙ ወራት በፊት እንዲያውቁ ተደርጓል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ያለመግባባት የለም፡፡ የተፈጠረው ሁኔታ ግን የኢትዮጵያ ኃላፊነትና ድርሻ በምንም አያሣንሰውም፡፡” ብለዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ በመንግሥታቸው በኩል ያለውን በየጊዜው እያደገ የመጣ ቅሬታም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የጎረቤቷን የሶማሊያን ደኅንነት ለመከላከል የምታወጣውን ግዙፍ ወጭ ያለአንዳች የገንዘብ እርዳታ እራሷ እየሸፈነች መቀጠሏና በበቂ በጀት የሚንቀሣቀሰው አሚሶም የኢትዮጵያን ወታደሮች ይተካል የተባለውም ቃል ሳይጠበቅ መቅረቱ አዲስ አበባን እያሳሰባትና እያበሣጫት ይገኛል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ በዚሁ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ማብራሪያቸው “ወጭን የመካፈል ጥያቄ ለእኛ ሁልጊዜ የሥጋታችን ምንጭ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠው ጥያቄ ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር የተሠማራው ሶማሊያ ውስጥ እየታየ ያለውን ግስጋሴ ሊያደናቅፍ የሚችለውን ሥጋት ለመጋፈጥ ተጨማሪ እሴት ሊኖረው በሚችል ሁኔታ ነው ወይ የሚል ነው፡፡ የእኛ ድምዳሜ አይደለም፤ የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ሶማሊያ ውስጥ ሠላምና መረጋጋትን ለማስፈን ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት በምንም አይቀንሰውም፡፡ ሆኖም ቀደም ሲል እንዳልኩት ወጭን ለመካፈልና አሁን ግዳጅ ላይ ያሉትን ኃይሎች በአግባቡ የመጠቀምን አስፈላጊነት ለሚመለከቱት ጉዳዮች ነው አሁን ቀዳሚውን ወይም ግዙፉን ቦታ የምንሰጠው፡፡ ከባለድርሻ አካላት ጋር ልንገነጋገርባቸው የምንፈልጋቸውም ጉዳዮች እነዚሁ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በዚህ ሣምንቱ የፓርላማው ንግግራቸው ሠራዊቱን ከሶማሊያ እንደሚያስወጡ አልተናገሩም፡፡ ይሁን እንጂ የአሚሶም ኃይሎች “ከዛሬ ነገ መጥተን እንረከባለን እያሉ” የኢትዮጵያ ወታደሮች ባሉበት እንዳሉ አንድ ዓመት ማለፉን በመጥቀስ ወቅሰዋል፡፡
ይህ አባባላቸውም ከሁዱር የወጡት “አንዳች ትኩረት ለማግኘት ሲሉ ነው” የሚል ግምትም በታዛቢዎች ዘንድ እንዲያድር ማድረጉ እየተሰማ ነው፡፡
አብዛኛው ሠራዊት የተውጣጣው ከዩጋንዳ፣ ከቡሩንዲ፣ ከኬንያ፣ ከሲየራ ሌዖንና ከጅቡቲ የሆነው የአሚሶም ጦር ከአውሮፓ ኅብረትና ከአፍሪካ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል፡፡
የኢትየጵያ ጦር የአሚሶም አካል ባለመሆኑ ምክንያት ሙሉው ወጭው የሚሸፈነው በራሷ በኢትዮጵያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
voa ameharic

50 Ethiopian immigrants sentenced to lengthy jail term with hard labor in Zambia

The Horn Times News 26 April 2013
Getahune Bekele-South Africa
Although the word “hard labour” sounds brutal and primitive, Zambian magistrate Shadreck Chanda was merciless in passing judgment when he sent 50 destitute Ethiopians to jail for entering the landlocked nation illegally on 29 March 2013. cr

Victims of human smugglers…Kembatta Ethiopians flocking south in search of better life…
The Ethiopians aged 11 to 37 were caught by Zambian police at Nakonde Border post, according to the Post online website, an online Zambian paper April 21st edition.
The magistrate who failed to show compassion to the juveniles, ordered all 50 including the well known human smuggler Sisay Asefa to serve a one-and-half-year imprisonment with hard labour or to pay fine of KR 400.00.
“The government of Zambia would not allow or tolerate people entering the country without proper papers.” Chanda told the stranded Ethiopians, victims of a well organized TPLF sponsored human smuggling gang operating between Johannesburg and Addis Ababa.
“I would have only deported you to Ethiopia but that the offence committed is serious as it borders on national security.” The Zambian magistrate added warning the Ethiopians that if they repeat the same offence, the court would not be lenient towards them.
The original charge sheet alleges that the Ethiopians didn’t inform an immigration officer upon entry as required by Zambian law.
Meanwhile the Horn Times is working to expose a multimillion dollar smuggling ring operating from GP Street in central Johannesburg involving unscrupulous Kenbatta slave traders, immigration officials and TPLF diplomats.

Friday, April 26, 2013

STOP LAND GRAB


You must watch this video to better understand   "African Land and Natural Resource Grabs Destroy Lives and Futures of Africans"      
http://www.youtube.com/watch?v=15xyVHIABvQ&list=UU8lBdGjabxkhLGRun46D-Ow

This is impact of the land grab investment on the people even while the government denies it all. This is why I call it not only a land grab, but a life and future grab from these innocent people. There are too many other examples to tell; not only in Gambella, Ethiopia or Africa but throughout the world.

The solution to this burgeoning problems of land and natural resource grabs is to have a government where the law can protect the people and where the law is not only limited to the elite, its cronies and partners. For positive change to come, citizens must be able to claim their rights—human, civil, land and religious.

Until there is such a government to protect the rights of the people, which upholds democratic principles of free speech, freedom of movement, freedom of assembly, freedom in the media, an independent judiciary and institutions, an independent appeal process, a non-politicalized military and similar aspects of free and open societies, the people will be seen as impediments to whatever the government wants for its own interests.

No one is safe in such a political climate. This is where donor countries like the US can become involved in pressuring these governments to be accountable to the people; not supporting autocratic regimes that are creating poverty by pushing people off their land.

Africans who used to feed themselves from farming their own land are now hungry and needing food aid. Some who have been hired to work on these agricultural farms, are often working for wages below the World Bank’s minimum wage standards.
BY  OBANG METHO

Wednesday, April 24, 2013

የኦነግ አባል በመሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ


• ተጠርጥረው ከተከሰሱት 20 ግለሰቦች ሦስቱ ነፃ ተደረጉ
የአገሪቱን ሕገ መንግሥት በመፃረር የኦሮሚያ ክልል እንዲከፋፈልና እንዲገነጠል፣ በሕገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሚባለው ቡድን አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል ተጠርጥረው፣ ክስ ከተመሠረተባቸው 20 ግለሰቦች መካከል 17ቱ ሚያዝያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው ጥፋተኛ የተባሉትን ተከሳሾች ክስ የሚመረምረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት ነው፡፡ ጥፋተኛ የተባሉትና ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ያረጋገጠባቸውን የወንጀል ድርጊት ባቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮቻቸውና ሰነዶች ማስተባበል ያልቻሉት ጌትነት ገመቹ (ቅፅል ስም ከድር ኢዘዲን)፣ ምትኩ ጌታቸው፣ ኢብሳ አለሙ፣ ጌቱ አሰፋ (ቅፅል ስም ከፍያለው አደሪ)፣ ተስፋ ሞተራ፣ መገርሳ ኩማ፣ ደምሴ ዳበሳ፣ ዋጋሪ ዲሪቢሳ፣ ደሳለኝ ደበል፣ ጌታቸው ብሩ፣ ጫላ አብዲሳ፣ ሐሞዛ አብዱ፣ ኮ/ር ረጋሳ ፈቀደ፣ ደርባቸው አመንቴና ለቺሳ ኢዶሳ ናቸው፡፡
ጥፋተኛ ከተባሉት 17 ተከሳሾች መካከል ሦስቱ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች የሚኖሩ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 14ቱ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚኖሩ ናቸው፡፡ የተጠረጠሩበትን የሽብር ወንጀል በመከላከል ነፃ የሆኑት ደግሞ ተካልኝ አበራ፣ ሙህዲን አባቡልጉና ካሊድ መሐመድ የሚባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
አንደኛ ተከሳሽ ስሙን በመቀየር ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ኬንያ ስሎሎ ወታደራዊ ማሠልጠኛ በመግባት፣ የኦነግ ካድሬ አመራርነት ሥልጠና መውሰዱን ክሱ ይገልጻል፡፡
በመመልመል፣ በማሠልጠን፣ መዋጮ በመሰብሰብ፣ በሴል በማደራጀት፣ አመራር በመስጠትና በ2003 ዓ.ም. የኦነግን ተልዕኮ የያዘ 56 ገጽ ያለው የቅስቀሳ ጽሑፍ በማሰራጨት፣ ‹‹ከኦነግ ዓላማ ወደኋላ ያለ ሰው ሞት ይጠብቀዋል›› ብሎ በማስፈራራትና ሌሎች የሽብር ድርጊቶችን በመፈጸም የኦነግን ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሠራ እንደነበር ክሱ ይዘረዝራል፡፡
ሌሎቹም ጥፋተኛ የተባሉት ተከሳሾች የኦነግ ዓላማ ፍፃሜ እንዲያገኝ በመንቀሳቀስ፣ የቅስቀሳ ጽሑፎችን በማሰራጨት፣ በተለያዩ የቀበሌ ገበሬ ማኅበር አካባቢዎች የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጐችን በመመልመልና ለሽብር እንዲነሱ በመገፋፋት፣ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ውስጥ እንዲሳተፉ ሲያደርጉ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ በዝርዝር ያብራራል፡፡
ዓቃቤ ሕግ 32 የሰዎች ምስክሮች፣ ዘጠኝ የሰነድና ሁለት የኤግዝቢት ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ፣ ያስመሰከረና ያስረዳ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ክሱንና ማስረጃውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱን ትናንትና ፍርድ ሲሰጥ አስታውሷል፡፡
ተከሳሾቹ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ለማስተባበል ቢሞክሩም፣ ከሦስቱ በስተቀር 17ቱ ማስተባበል አልቻሉም ብሎ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃና የተከሳሾቹን የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የኦነግ አባል በመሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ


• ተጠርጥረው ከተከሰሱት 20 ግለሰቦች ሦስቱ ነፃ ተደረጉ
የአገሪቱን ሕገ መንግሥት በመፃረር የኦሮሚያ ክልል እንዲከፋፈልና እንዲገነጠል፣ በሕገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሚባለው ቡድን አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል ተጠርጥረው፣ ክስ ከተመሠረተባቸው 20 ግለሰቦች መካከል 17ቱ ሚያዝያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው ጥፋተኛ የተባሉትን ተከሳሾች ክስ የሚመረምረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት ነው፡፡ ጥፋተኛ የተባሉትና ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ያረጋገጠባቸውን የወንጀል ድርጊት ባቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮቻቸውና ሰነዶች ማስተባበል ያልቻሉት ጌትነት ገመቹ (ቅፅል ስም ከድር ኢዘዲን)፣ ምትኩ ጌታቸው፣ ኢብሳ አለሙ፣ ጌቱ አሰፋ (ቅፅል ስም ከፍያለው አደሪ)፣ ተስፋ ሞተራ፣ መገርሳ ኩማ፣ ደምሴ ዳበሳ፣ ዋጋሪ ዲሪቢሳ፣ ደሳለኝ ደበል፣ ጌታቸው ብሩ፣ ጫላ አብዲሳ፣ ሐሞዛ አብዱ፣ ኮ/ር ረጋሳ ፈቀደ፣ ደርባቸው አመንቴና ለቺሳ ኢዶሳ ናቸው፡፡
ጥፋተኛ ከተባሉት 17 ተከሳሾች መካከል ሦስቱ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች የሚኖሩ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 14ቱ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚኖሩ ናቸው፡፡ የተጠረጠሩበትን የሽብር ወንጀል በመከላከል ነፃ የሆኑት ደግሞ ተካልኝ አበራ፣ ሙህዲን አባቡልጉና ካሊድ መሐመድ የሚባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
አንደኛ ተከሳሽ ስሙን በመቀየር ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ኬንያ ስሎሎ ወታደራዊ ማሠልጠኛ በመግባት፣ የኦነግ ካድሬ አመራርነት ሥልጠና መውሰዱን ክሱ ይገልጻል፡፡
በመመልመል፣ በማሠልጠን፣ መዋጮ በመሰብሰብ፣ በሴል በማደራጀት፣ አመራር በመስጠትና በ2003 ዓ.ም. የኦነግን ተልዕኮ የያዘ 56 ገጽ ያለው የቅስቀሳ ጽሑፍ በማሰራጨት፣ ‹‹ከኦነግ ዓላማ ወደኋላ ያለ ሰው ሞት ይጠብቀዋል›› ብሎ በማስፈራራትና ሌሎች የሽብር ድርጊቶችን በመፈጸም የኦነግን ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሠራ እንደነበር ክሱ ይዘረዝራል፡፡
ሌሎቹም ጥፋተኛ የተባሉት ተከሳሾች የኦነግ ዓላማ ፍፃሜ እንዲያገኝ በመንቀሳቀስ፣ የቅስቀሳ ጽሑፎችን በማሰራጨት፣ በተለያዩ የቀበሌ ገበሬ ማኅበር አካባቢዎች የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጐችን በመመልመልና ለሽብር እንዲነሱ በመገፋፋት፣ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ውስጥ እንዲሳተፉ ሲያደርጉ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ በዝርዝር ያብራራል፡፡
ዓቃቤ ሕግ 32 የሰዎች ምስክሮች፣ ዘጠኝ የሰነድና ሁለት የኤግዝቢት ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ፣ ያስመሰከረና ያስረዳ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ክሱንና ማስረጃውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱን ትናንትና ፍርድ ሲሰጥ አስታውሷል፡፡
ተከሳሾቹ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ለማስተባበል ቢሞክሩም፣ ከሦስቱ በስተቀር 17ቱ ማስተባበል አልቻሉም ብሎ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃና የተከሳሾቹን የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሹማምንቱን አስጠነቀቁ


8451fae78b6a67a12ffed23a03c952ee_L• የኦብነግና የኦነግ አመለካከትን የተሸከሙ እንዳሉ ጠቁመዋል
• የባቡር ፕሮጀክት ሪፖርታቸው ከትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጋር ይጣረሳል
• ነዳጅ ስለመገኘቱ ማረጋገጫ የለም አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከተገቢው ጊዜ በላይ የዘገየውን የመንግሥታቸውን የሥራ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ዕለት አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ኃላፊዎች ባህሪ ያስደሰታቸው አይመስሉም፡፡ በየደረጃው ያሉ ባለሥልጣናትንም አስጠንቅቀዋል፡፡
በሕገ መንግሥቱና በፓርላማው ደንብ መሠረት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሥራ አፈጻጸሙን በዓመቱ አጋማሽና ማጠናቀቂያ ላይ ማቅረብ የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ ከተሾሙ የሰባት ወራት ዕድሜ ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ግን ከተገቢው ጊዜ ለሦስት ወራት በመዘግየት የስምንት ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡
ያቀረቡት ሪፖርት በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮችን ለስለስ አድርጐ ያቀረበ አንዳንዶቹን ደግሞ የዘለለ ነበር፡፡ ነገር ግን ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት ጠጠር ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁ ሲሆን፣ ይህም በሪፖርታቸው ያልተነሱ ነጥቦችን እንዲዳስሱ አስችሏል፡፡
ከምክር ቤቱ አባላት የተነሱ የተወሰኑ ጥያቄዎች በመንግሥታቸው መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች ባህሪን እንዲናገሩ፣ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክቶችንም እንዲያስተላልፉ ያስገደደ ነበር፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በቅርቡ ተፈናቅለው ስለነበሩ ሦስት ሺሕ የሚሆኑ የአማራ ክልል ተወላጆች ጉዳይ፣ እንዲሁም በሐረርጌ ዞኖችና በሶማሌ ክልል መካከል የዜጐችን ሕይወት በቀጠፈው ግጭት ላይ የቀረቡላቸው ጥያቄዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በምሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች ነዋሪዎችና በሶማሌ ክልል የሽንሌ ነዋሪዎች መካከል ተከስቶ ስለበረው ደም ያፋሰሰና የዜጐችን ሕይወት የቀጠፈ ግጭት ያነሱት አንድ የምክር ቤቱ አባል፣ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡
ጥያቄውን ያቀረቡት የምክር ቤት አባል በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው ደም አፋሳሽ ግጭት በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ቢሆንም፣ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ቀላል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግጭቱን የቀሰቀሱት በክልሎቹ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ኃላፊዎች መሆኑን በመጠቆም መንግሥት በዚህ ዙሪያ የወሰደውን ዕርምጃ ጠይቀዋል፡፡
የችግሩ መንስዔ ከሕዝብ የመነጨ አለመሆኑን በማንሳት ምላሽ መስጠት የጀመሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ በአካባቢው የሚገኙ የታጠቁ ተቃዋሚዎችንና (መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸው ድርጅቶች) በክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፡፡
‹‹ይህ ችግር የሁለት አካላት ችግር ነው፡፡ አንደኛው ይህንን መንግሥት እፋለማለሁ ብለው የሚንቀሳቀሱት ኦነግና ኦብነግ የእርስ በርስ ግጭት ነው፡፡ ሁለተኛው በእኛው መዋቅር ውስጥ ያሉ የኦብነግና የኦነግ አመለካከትን የሚሸከሙ ሰዎች ናቸው፤›› ብለዋል፡፡ ችግሩ የሚከሰትበት ወቅትና ጊዜ እንዳለው የጠቆሙት አቶ ኃይለ ማርያም፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው በአሸባሪነት የተፈረጁ ድርጅቶችን አመለካከት መሸከም ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በኋላ አንዲት ነፍስ በዚህ አካባቢ ብትወድቅ በቀጥታ ወደሚፈለገው የሕግ ዕርምጃ እንደሚኬድ በመንግሥት በኩል በፅኑ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ድርጊት በኬንያ ድንበር ሞያሌ አካባቢ ግጭት የፈጠሩ በሙሉ እስር ቤት መሆናቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሶማሌና በሐረርጌ ግጭት የተሳተፉ የክልሉ አመራሮችና ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በምርመራ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
‹‹የፌደራል መንግሥት የትኛውም ክልል ገብቶ ሰብዓዊ መብት የማስከበር ግዴታ አለበት፤›› በማለት ማንኛውም አመራር ይህንን እንዲገነዘብ ከክልሎቹ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መመርያው እንደተሰጣቸው አብራርተዋል፡፡ ‹‹ይህ በክልሎች ጣልቃ የመግባት ጉዳይ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም ክልል ተዘዋውሮ የመሥራት መብት እንዳለው በመግለጽ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሌላ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ መደረጉን ኮንነዋል፡፡ ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ብሔር ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ፣ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችም መፈናቀላቸውን ጠቁመዋል፡፡ ድርጊቱን በፈጸሙ የክልሉ አመራሮች ላይም ሕጋዊ ዕርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ ‹‹አፈናቃይ ተብዬዎቹ አመራሮች በሌብነት የተጨማለቁ ናቸው፤›› ያሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ አመራሮቹ መሬት በመቸብቸብ ተግባር ላይ የተሰማሩ እንደሆኑና ከዚህ ጥቅም ጋር የተሳሰሩ አማሮችም ሆኑ ኦሮሞዎች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አብራርተዋል፡፡
ይህ ተግባር አገርን የሚያጠፋ እንደሆነና ማንኛውም አመራር የዜጐችን መብት የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት አለበት ብለዋል፡፡ ይህንን በማይተገብሩ በየትኛውም ደረጃ ባሉ አመራሮች ላይ ደግሞ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ይህን መልዕክት በየትኛውም ክልል ያለ የአመራር አካል ሊገነዘበው ይገባል፤›› በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡
ሌላው አስገራሚ የሆነው ንግግራቸው የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ከወር በፊት ለፓርላማው ካቀረቡት ሪፖርት ጋር የሚጋጭ መሆኑ ነው፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ዲሪባ ኩማ በትራንስፖርት ዘርፍ የመሥርያ ቤታቸውን የስምንት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ከተያዙት የባቡር ፕሮጀክቶች ውስጥ በተያዘላቸው ዕቅድ እየተከናወኑ ያሉት የአዲስ አበባ ጂቡቲ መስመርና የአዲስ አበባው ቀላል የባቡር ትራንስፖርት መሆናቸውን ጠቁመው ነበር፡፡ የተቀሩት የባቡር ፕሮጀክቶች በተለያዩ ችግሮች በዋናነት ደግሞ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ከተያዘላቸው ጊዜ በእጅጉ እንደዘገዩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከአምስት አበዳሪ አገሮች ጋር የብድር ድርድር እየተደረገ መሆኑን ለምክር ቤቱ አስረድተው ነበር፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሪፖርት በእጅጉ ከዚህ የተቃረነ ነው፡፡ ‹‹የገንዘብ ችግር የለብንም፤›› ያሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ በባቡር ፕሮጀክቶቹ ላይ የተስተዋለው መዘግየት በዋነኛነት በማስፈጸም ችግር የተነሳ ነው ብለዋል፡፡
የቻይና መንግሥት ለማበደር ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ‹‹ብድር ለመጠየቅ የሚያስችል ጥናት ባለመሠራቱ ነው ፕሮጀክቶቹ የዘገዩት፡፡ ይህ ደግሞ በዘርፉ ላይ የሚስተዋል የማስፈጸም፣ የዕውቀት ማነስና የልምድ ችግር ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው፤›› ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በደቡብ ኦሞ በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው የሦስት ኩባንያዎች ጥምረት ነዳጅ ስለማግኘቱ የሚያሳዩ ፍንጮችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ማስነገሩን የተቹ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ ተረጋግተው መቀመጥ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ በነዳጅ ፍለጋ የተሰማሩ ኩባንያዎች ብድር ለማግኘት ሲሉ እንደዚህ ዓይነት ተግባር እንደሚፈጽሙ በመጠቆም፣ በደቡብ ኦሞ ነዳጅ ፍለጋ የተሰማሩት ኩባንያዎች ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይደለም ብለዋል፡፡ ኩባንያው ገና ቁፋሮውን አለማጠናቀቁንና በዚህ ደረጃ የተገኙ ፍንጮች ነዳጅ አለ ለማለት እንደማያስችሉ ተናግረዋል፡፡


New York, April 22, 2013--The Committee to Protect Journalists protests Ethiopian authorities' transfer of independent newspaper editor Woubshet Taye to a remote prison several hours away from his family's home. Woubshet has been imprisoned since June 2011 on vague terrorism charges that CPJ has determined to be unsubstantiated.
"Moving detainees to prisons far from their families is a tactic long used by governments that wish to not only further penalize the individuals but to punish their loved ones as well," said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. "Woubshet Taye should not be in prison at all, never mind held in one so far from his family. We call on Ethiopian authorities to return him to a facility closer to his home, and to reconsider the unjust conviction that put him behind bars in the first place."

Authorities on Friday transferred Woubshet from Kilinto Prison, outside Addis Ababa, to a detention facility in the town of Ziway, about 83 miles southeast of the capital, according to local journalists and the U.S.-based exile-run AwrambaTimes.com. The authorities did not provide a reason for the transfer. Local journalists told CPJ that Woubshet's wife and four-year-old son would now have to travel more than four hours to reach the prison to visit the journalist.
Woubshet, former deputy editor of the now-defunct independent weekly Awramba Times and a recipient of Human Rights Watch's Hellman/Hammett Award, was sentenced in January 2012 to a 14-year prison sentence on charges lodged under Ethiopia's broad anti-terrorism law. The journalist was arrested a couple of weeks after he published a column in Awramba Times that critically assessed the ruling party's performance in its two decades of rule. The paper was known for its bold coverage of local issues.http://cpj.org/2013/04/ethiopia-transfers-journalist-woubshet-to-remote-p.php
The U.N. Special Rapporteur on torture and other forms of cruel, inhuman or degrading treatment or punishment, said last month that Ethiopia had violated Woubshet's rights by failing to address his allegations of being tortured in custody, despite Ethiopia's commitment to "uphold the highest standard of human rights."
CPJ research shows that other states that have imprisoned journalists have used the tactic of moving journalists to prisons far from their homes as a means of punishing them and their families. Cuba, for example, p


የማረሚያ ቤቱ ድራማ በርዕዮት እምቢተኝነት ከሸፈ


ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡ የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡
ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡ በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡ በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡  
የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣ በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ ርዕዮትም  ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች  ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ›› በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡
ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ  ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡
ከፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

Tuesday, April 23, 2013

Ethiopia transfers editor Woubshet Taye to remote prison



New York, April 22, 2013--The Committee to Protect Journalists protests Ethiopian authorities' transfer of independent newspaper editor Woubshet Taye to a remote prison several hours away from his family's home. Woubshet has been imprisoned since June 2011 on vague terrorism charges that CPJ has determined to be unsubstantiated.
"Moving detainees to prisons far from their families is a tactic long used by governments that wish to not only further penalize the individuals but to punish their loved ones as well," said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. "Woubshet Taye should not be in prison at all, never mind held in one so far from his family. We call on Ethiopian authorities to return him to a facility closer to his home, and to reconsider the unjust conviction that put him behind bars in the first place.
Authorities on Friday transferred Woubshet from Kilinto Prison, outside Addis Ababa, to a detention facility in the town of Ziway, about 83 miles southeast of the capital, according to local journalists and the U.S.-based exile-run AwrambaTimes.com. The authorities did not provide a reason for the transfer. Local journalists told CPJ that Woubshet's wife and four-year-old son would now have to travel more than four hours to reach the prison to visit the journalist.
Woubshet, former deputy editor of the now-defunct independent weekly Awramba Times and a recipient of Human Rights Watch's Hellman/Hammett Award, was sentenced in January 2012 to a 14-year prison sentence on charges lodged under Ethiopia's broad anti-terrorism law. The journalist was arrested a couple of weeks after he published a column in Awramba Times that critically assessed the ruling party's performance in its two decades of rule. The paper was known for its bold coverage of local issues.
The U.N. Special Rapporteur on torture and other forms of cruel, inhuman or degrading treatment or punishment, said last month that Ethiopia had violated Woubshet's rights by failing to address his allegations of being tortured in custody, despite Ethiopia's commitment to "uphold the highest standard of human rights."
CPJ research shows that other states that have imprisoned journalists have used the tactic of moving journalists to prisons far from their homes as a means of punishing them and their families. Cuba, for example, placed journalists in prisons hundreds of miles from their families at the height of the Black Spring crackdown in 2003, according to CPJ research.

ግብጽ የውሃ ጦርነት ለማድረግ ሃይል እያደራጀች ናት።


በአሜሪካ ከፍተኛ እገዛ የሚደረግለት የግብጽ ጦር ሃይል የናይል ወንዝን ለመቆጣጠር ሲባል መጠሪያው የዉሃ ጦርነት ሊባል የሚችል ጸብ አጫሪ ተግባር ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ይገኛል። የምዕራብ የደህንነት ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ የጦር ክፍሉ የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ሞርሲን ማንኛውንም የናይል ወንዝ ፍሰት የሚያስተጓጉል ተግባር ለመቀልበስ ጦሩ የሚደራጅበትን ፈቃድ ጠይቋል።
አካላቱ የሚሉት የጦር ሃይሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከፍተኛ ጸብ ሊፈጠር እንደሚችል እና ያም የግብጽን እና የሱዳንን የውሃ ፍጆታ አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት ይሆናል ያለው ሜንልነው።”ለግብጽ የጦር ሃይል እና መንግስት ይህ ምናልባትም የዛሬው ትልቁ እና አንገብጋቢ የጸጥታ ጉዳይ ነው” ብለዋል ምንጮቹ።
ምንጮቹም አክለው ሞርሲ ከሱዳን ጋር የጦር ሃይል ውህደት በማድረግ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ የምታደርገውን የግድብ ግንባታ ለማስቆም በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ሲሉም ለኢትዮጵያ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ሊባል የሚችል ሃሳብ ሰንዝረዋል። የህዳሴ ግድቡ ወደ 84 ቢሊዮን ኪዩቢክ ዉሃ በማስቀረት ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ በቂ የሆነ ክምችት ለማድረግ ታስቦበት እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል።”የጦር ሃይሉ በቅርቡ የአየር ጥቃት ለማድረግ ትእዛዝ የሚደረግበትን መንገድ እና የግድቡን ግንባታ ለማስቆም ወይም የኢትዮጵያዋን ልዕልት በቀላሉ ለማውደም እየተዘጋጀ ይገኛል” ይላል ይህ ምንጭ።የዉሃውን ስልሳ በመቶ የምትጠቀመው ግብጽ የቀድሞውን ያለፈ ”መብት” ለማስጠበቅ የሙጥኝ ማለቷ የማያለሰልስ አቋም እየሆነ መጥቷል።
በማስቀጠልም ምንጮቹ የሞርሲ መንግስት ለአዲስ አበባ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ግምታቸውን አስታውቀዋል። ይህም ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው በመጪው የግንቦት ወር መገባደጃ አከባቢ በግብጽ-ሱዳን-ኢትዮጵያ ሶስትዮሽ የቴክኒካል ቀጣይ ስብሰባ ነው ተብሏልም። ናይል በአስር ሃገራት የጋራ ሃብትነት ይታወቃል”ኢትዮጵያ ለግድቡ ተግባር የሚጠቅማትን  ወይም የሚሆናትን ዉሃ ብቻ ማጠራቀሟን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው እርምጃዎች መወሰዳቸው ግድ ነው ይህም ከግብጽ ፈቃድ እና መስመር ጋር የተስማማ መሆን አለበት” ሲሉ የተደመጡት ደግሞ የዛሬ አራት ቀን በግብጽ የመንግስት ዜና አውታር አል አህራም ዴይሊ ንግግር ያደረጉት የሃገሪቱ ባለስልጣን ናቸው።
የዜና ምንጮች ይህን ያሉት የግብጽ የጦር ሃይል  ከዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ኤፍ-አስራ ስድስት ብሎክ ሃምሳ ሁለት የተባለ ለብዙ ተግባራት የሚውል የጦር አውሮፕላን መረከቧን እንደ ዋቢ መረጃ በመጥቀስ ነው። በማስቀጠል እንዳሉትም  በአ.አ 2013 ወደ ሃያ የሚሆን ቁጥር ያላቸው መሰል የጦር አውሮፕላኖች የሚቀበለው የግብጽ የአየር ሃይል በሰጠው መረጃ የቅርብ ጊዜው ኤፍ አስራ ስድስት ቫሪያንት ተቀጥያ የነዳጅ መያዣዎች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያዋ ልዕልት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያስችለናል ሲል አስታውቋል።
የህዳሴው ግድብ በየዓመቱ ከአስራ ስምንት እስከ ሃያ ሚሊዮን ኪዩቢክ ዉሃ እንድናጣ ያደርገናል ስትል ግብጽ አስታውቃለች። ምንጮቹ እንደሚሉትም ግብጽ ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ግድብ ፕሮጀክት አደገኛነት ማሳሰቧን ገልጸዋል።
”በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ድርሻ በጣም ወሳኝ ነው ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሊደረግ የሚችለው ጥቃት ላይ ምርቷ የሆነው የጦር አውሮፕላን ግልጋሎት ላይ ሊውል ታቅዷል እና ነው” ያለው ይህ ምንጭ ነው።
wolaita.com

ከእሁድ እስከ እሁድ (በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው)


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)


ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል።
በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል።
ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው በማለት ራሱን ከምርጫው ያገለለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፤ ከምርጫው በኋላም እስሩና እንግልቱ መቀጠሉን ማስታወቃቸውን፣ በአንድ ሳምንት 26 አባላቱ እስር እንደተፈረደባቸው፣ በሲዳማ ዞን በየወረዳው ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶችና ሸንጎዎች እየተቋቋሙ የፓርቲው እጩዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት ከ400 ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና ከ3ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚደርስ እስራት እየተፈረደባቸውና ፍርደኞቹ ወህኒ መውረዳቸውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደርጅቱ ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር አየለ አሊቶ በመጥቀስ ኢሳት ዘግቧል። የኢህአዴግ አመራሮች ከሳሽም ፈራጅም በሆኑበት ሁኔታ ዜጎቻችን እየተንገላቱ ነው፤ ከምርጫው ብንወጣም ትግላችን ይቀጥላል ማለታቸውን የኢሳት ዘገባ ያስረዳል። 
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረው ተፈቱ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር semayawiይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ ታስረው ተፈቱ። ኢሳት ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓም እንደዘገበው አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል፣ ከክልል መንግስትና ከዞን ባለስልጣናት ወደ ወረዳው ገብተው ሰዎችን ለማነጋገር የሚያስችል የፈቃድ ወረቀት ይዛችሁ አልመጣችሁም በሚል ነው። “ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለፈቃድ ሄዶ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ለመነጋገር አይቻልም፣ በዚያ ላይ እናንተ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ናችሁ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ኢ/ር ይልቃል፣ እንዲህ አይነት ስራ ለመስራት በቅድሚያ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ፣ ይህን አለማድረግ ደግሞ የብሄረሰቦችን የራስን በራስ የማስተዳደር መብት መናቅ ተደርጎ እንደሚታይ እንደተነገራቸው ኢ/ር ይልቃል ከእስር ተለቀው እየተመለሱ እያሉ ለኢሳት መናገራቸውን ዘገባው ያስረዳል።
በስፍራው ተገኝተው አንዳንድ ሰዎችን በማናገር ያዘጋጁት ቪዲዮ በወረዳው ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲደመሰስ መደረጉን ኢንጂነሩ ተናግረው፣ ይሁን እንጅ በአይናቸው ያዩት፣ በጆሮዋቸው የሰሙት በቂ መረጃ እንደሰጣቸው ኢሳት በዘገባው አመልክቷል።
ታሪካዊ የሪፖርተር አንደበት
azeb“ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የመክፈቻ ንግግራቸውን አድርገው ሲያበቁ፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተዘጋጀ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሕይወት ዘመን ትውስታ ከሕፃንነት እስከ ግባተ መሬት ድረስ የነበረውን ዘጋቢ ፊልም ሲታይ በታዳሚዎች ላይ የተደበላለቀ ስሜት ሲፈጠር ተስተውሏል፡፡ በተለይ በዘጋቢ ፊልሙ የአቶ መለስ አስከሬን ከቤልጂየም ብራሰልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስና ቤተሰቦቻቸው ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ፣ አስከሬኑ ከቦሌ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቤተ መንግሥት ሲጓዝ፣ የቀብራቸው ዕለት በመስቀል አደባባይ አስከሬናቸውን የያዘው ሳጥን ሲቀመጥና ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ አስከሬኑ በሰረገላ ሆኖ ወደ ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሲያመራ የሚያሳየውን ፊልም የተመለከቱ በአፍሪካ ኅብረት የታደሙ ሰዎች፣ ከንፈራቸውን ከመምጠጥ እስከ እንባ ማፍሰስ ድረስ በሐዘን ስሜት ውስጥ ገብተው ተስተውሏል፡፡ ሌላው አዳራሹን ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሐዘን ድባብ ውስጥ የከተተ ክስተትም ተፈጥሮ ነበር፡፡ ዘጋቢ ፊልሙን ከሚመለከቱ ታዳሚዎች መካከል የነበሩት የአቶ መለስ እህቶች ድምፅ አውጥተው ለቅሶ በመጀመራቸው፣ ከሰባት ወራት በፊት የነበረውን የሐዘን ሁኔታ ያስታወሰና የሁሉንም ታዳሚዎች ቀልብ የሳበ ሆኖ ነበር፡፡”
ምንጭ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ “ከለቅሶ ቤት” እንደዘገበው (10 April 2013)
አርበኞች ግንባር ማርኬ ገደልኩ አለ
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ስፍራ  በሁለት ተከታታይ ቀናት ከአገዛዙ  የፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ባካሄደው  የፊት ለፊት eppfውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን ስለመቀዳጀቱ ለጎልጉል በላከው መግለጫ አስታወቀ።
ግንባሩ ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ ም በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሃያ አንድ የአገዛዙ ወታደሮችን ግዳይ ማድረጉን፣ ሃያ አምስት ማቁሰሉን፣ በቀጣይ ቀን በዋልድባ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ በተከፈተ ውጊያ  ሃያ አምስት የአገዛዙ ወታደሮችን መግደሉንና ሰላሳ ዘጠኝ በማቁሰል ከፍተኛ ድል እንዳገኘ በመግለጫው አመልክቷል።
ግንባሩ ካደረሰው ሰብአዊ ጥቃት በተጨማሪ  የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አገኘሁ ስላለው ድልና ተቀዳጀሁት በሚል በይፋ የገለጸውን ዜና አስመልክቶ ከመንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መልስ የለም። ግንባሩም ቢሆን ሪፖርቱን በምስል አላስደገፈም።
የአውሮፓ ህብረት አቋም አልጠራም
የሰብአዊ መብት ማስከበር የህልውናችን ጉዳይ ነው
eu-300x191ከሰብአዊ መብት፣ ከፕሬስ ነጻነት፣ ዜጎች አመለካከታቸውን በነጻ የማራመድና የተፈጥሮ መብታቸው መገፈፉንና አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነው አምባገነንነት አስጊ ደረጃ መድረሱን አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት የጠራ አቋም አለመያዙ ታውቋል። አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ በአውሮፓ የቀድሞውን ወዳጅነት አጥብቀው እንደሚቀጥሉበት ለማረጋገጥ አውሮፓን  የዞሩትን  የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ  ጉብኝትን አስመልክቶ የጀርመን ሬዲዮ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ኢህአዴግን ከማድነቅ አልፎ የ30 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ መስጠቱን አመልክቷል። በሶማሊያ ስለተፈጠረው መረጋጋት፣ በደቡብ ሱዳን ጉዳይና በምስራቅ አፍሪቃ አጠቃላይ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ያወሳው ሬዲዮው፣ የህብረቱ ሊቀመንበር ማሳሰቢያ ቢጤ ማስተላለፋቸውን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ያደነቁት የህብረቱ ሊቀመንበር፣ “ይህ ዕድገት ቀጣይነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ፣ የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊ መብቶች፣ የመናገርና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነቶች ሲከበሩ ብቻ ነው” ብለዋል። በጋራ በተዘጋጀው መግለጫ አቶ ሃይለማርያም “የሰብአዊ መብቶች መከበር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው”  አያይዘውም “የመሬት ወረራ ብሎ ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፤ አንድም ጋዜጠኛ ሃሳቡን በመግለጹ አልታሰረም “ሲሉ የተለመደውን የመለስን ዓይነት መልስ በመመለስ ሸምጥጠዋል።
goolgule.com