Thursday, April 18, 2013

በአፋር እና በኢሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

ከአራት ቀናት በፊት በገዋኔ እና ቡሊወላይቶ ወረዳዎች በሚባሉት አካባቢዎች የታጠቁ የኢሳ ጎሳዎች በሰነዘሩት ጥቃት የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከአራት ቀናት በፊት ኢሳዎች በአፋሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሰዎች በጊል ተመትተው ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ወደ ናዝሬት ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተሰጣቸው ነው። ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ መንገድ በደረሰ ጥቃትም እንዲሁ አንድ የአፋር ብሄረሰብ ተወላጅ ተገድሎ ሌሎች ሰባት ሰዎች ቆስለዋል።

... ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በሁዋላ ወደ አፋር ክልል የተጓዙ የኢሳ ጎሳ አባላት ልዩ ወረዳ መጠየቃቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። በኢሳዎች የቀረበውን የወረዳ ጥያቄ አፋሮች አጥብቀው እየተቃወሙት ነው።

በተመሳሳይም ሁኔም አፋር ውስጥ ዞን ሁለት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ወደ 15 ሺ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ልዩ ወረዳ ይገባናል በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ አሁንም ገፍተውበታል። በርካታ አፋሮች እንቅስቃሴውን እየተቃወሙ ሲሆን፣ ለኢሳ የልዩ ወረዳ ከተሰጠ በአፋር ውስጥ ለሚኖሩት የትግራይ ተወላጆችም ሊሰጥ ይችላል በማለት ድርጊቱን አጥብቀው እየተቃወሙ ነው። የአፋር ተወላጆች የትግራይ ክልል ባለስልጣናት አካባቢውን ወደ ትግራይ ለመውሰድ ሆን ብለው በአፋር ክልል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን እየተጠቀሙ ነው በማለት ይቃወማሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ ላይ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።


ESAT ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

No comments:

Post a Comment