FEBRUARY 11, 2014
ታዋቂው ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ቃል እንዲሰጡ በፌደራል ፖሊስ ተጠሩ
——————–
——————–
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባልና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረባ የሆኑት ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ቃል እንዲሰጡ በፌደራል ፖሊስ መጠራታቸውን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች ገለፁ ፡፡
መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን የመለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ “በሙት መንፈስ ሀገር ሲታመስ” በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያደረሱት አነጋጋሪ መፅሀፍ የኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናትን እንዳስቆጣ ይታወቃል ፡፡ ደራሲ አንዳርጌ መስፍን በፌደራል ፖሊስ ስለመጠራታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ አንዳርጌ መስፍን “ጥቁር ደም” የተባለውን ታዋቂ መጽሐፍ ጨምሮ 10 መጽሐፍት ለአንባቢያን ያደረሱ አንጋፋ ደራሲ ናቸው፡፡
ፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧ ይታወሳል፡፡
No comments:
Post a Comment