FEBRUARY 11, 2014

አሁን ህወሓቶች በአራት ጎራዎች ተከፍለው ይጨቃጨቃሉ። (ስለዚህ ጉዳይ ሌላ ግዜ እፅፋለሁ)። ካልተግባቡ አስቸኳይ ጉባኤ የመጥራት ሐሳብ አለ።
ስለዚህ አርከበ ብቻ አይደለም የተመለሰው። ከነስየ አብርሃና ገብሩ አስራት ጋ ከወሓት የወጣው ቢተው በላይም ወደ ህወሓት (በዕርቁ ሂደት) ተመልሶ ቁልፍ ስልጣን ይሰጠዋል። አርከበ ብቻ አይደለም ስልጣን የተሰጠው፤ አሜሪካ ገብቶ የነበረ የአርከበ ወንድም ጌታቸው ዑቅባይም ታርቆ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማናጀር ተደርጎ ተሹመዋል። ሌሎች አዳዲስ ገቢዎችም አዳዲስ ቁልፍ ስልጣኖች እያገኙ ነው። አርከበ በትግራይ ክልል ስልጣን ይሰጠዋል የሚል ግምት ነበረኝ። ግን አልሆነም።
አርከበ ከህወሓት ከወጣ በኋል ይዞት የነበረውን የሚኒስተር ዲኤታ ስልጣን ተነጥቆ ለሌላ ነበር የተሰጠው። አሁንም አልተመለሰለትም። ሌላ አዲስ ስልጣን ነው የተሰጠው። ምክንያቱም የድሮ ስልጣኑ ተቀምቷል።
It is so!!! Abraha Desta
No comments:
Post a Comment