Friday, November 29, 2013

በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጠገብ የተገኘው ጥቅል ቦምብ መሆኑ ተረጋገጠ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ በፖሊስና አነፍናፊ ውሻ አማካይነት የተገኘው ጥቅል፣ ቤት ሠራሽ ቦምብ መሆኑን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎት ማረጋገጡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ ዘ ቮይስ ኦፍ ራሺያ (የሩሲያ ድምፅ) የተሰኘው የአገሪቱ ሬዲዮ በድረ ገጹ እንዳለው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በፖሊስና በአጋዥ አነፍናፊ ውሻ አማካይነት በኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ ተቀምጦ የተገኘው ጥቅል ዕቃ ወደ ላብራቶሪ ተወስዷል፡፡ በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ አቅራቢያ ወድቆ ከተገኘውና በኋላም በቤት ውስጥ እንደተሠራ ከተረጋገጠው ቦምብ ጋር አብሮ የሞባይል ስልክ ተያይዞ መገኘቱን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎትን የጠቀሰው ዘገባ ያመለክታል፡፡ በሩሲያ የአገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎት ላብራቶሪ የተመረመረው ጥቅል ዕቃ፣ በሦስት የፕላስቲክ ብልቃጦች ውስጥ በግምት 400 ግራም የሚሆን ፓይሮ ፓውደርና ሮው ቦልትስ የተሰኘ ተቀጣጣይና የፈንጂ ዱቄት ተሞልቶ ታሽጐ ነበር፡፡ የታመቀ ተቀጣጣይ ዱቄት ከተሞሉ ብልቃጦች ጋር ተያይዞ የተቀመጠው የሞባይል ስልክም ከርቀት ፍንዳታውን ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን ምርመራው አረጋግጧል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማግኘት ያረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ethiopian reporter

No comments:

Post a Comment