Friday, November 15, 2013

ሰበር ዜና ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ ሰልፉም እንዳይደረግ ከለከለህዝብ መንግስት ከሳውዲ ጋር አበረ እያለ እያማረረ ነው፡፡ የስዑዲ ፖሊስ በጅዳ ከተማ የሚገኙ ኢትዮዽያውያን ስደተኞች ‘ሕገ ወጥ ኗሪዎች’ በሚል ሰበብ እያሰረና እየደበደበ ይገኛል። የኢህአዴግ ፖሊስም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ዜጎች ‘ሕገወጥ ሰልፈኞች’ በሚል ሰበብ እየገረፈና እያሰረ ይገኛል።

ሰበር ዜና ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ ሰልፉም እንዳይደረግ ከለከለ

ህዝብ መንግስት ከሳውዲ ጋር አበረ እያለ እያማረረ ነው፡፡ 
የስዑዲ ፖሊስ በጅዳ ከተማ የሚገኙ ኢትዮዽያውያን ስደተኞች ‘ሕገ ወጥ ኗሪዎች’ በሚል ሰበብ እያሰረና እየደበደበ ይገኛል። የኢህአዴግ ፖሊስም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ዜጎች ‘ሕገወጥ ሰልፈኞች’ በሚል ሰበብ እየገረፈና እያሰረ ይገኛል። 
በዚህ መሰረት ሰለማዊ ሰልፉ ያስተባብሩ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች በፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ባሁኑ ግዜ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ወደ 14 የሚጠጉ ፖለቲከኞች አራት ኪሎ አከባቢ በፖሊስ ታግተው ይገኛሉ። ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች በመኪና ታፍሰው እየተወሰዱ ነው።  
የስዑዲና የኢህአዴግ የፀጥታ አካላት በኢትዮዽያውያን ስደተኞች ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው ማለት ነው? የኢትዮዽያውያን ሰቆቃ በመቃወም ሰልፍ ላደረጉ ዜጎች ማሰርና መደብደብ ምን አመጣው? መልእክቱስ ምንድነው? ኢህአዴግ ለስዑዲ መንግስት ያለው አጋርነት በግልፅ አሳይተዋል። 
ድሮውም የኢትዮዽያ መንግስት ለዜጎቹ ክብር ቢኖረው ኢትዮዽያውያን ስደተኞች ይህን ያህል ክብር ባላጡ ነበር። ‘ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ’ ይባል የለ። 
source:_freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment