ከሳምንት በፊት እዚህ ኖርዌይ አንድ የደቡብ ሱዳን ተወላጅ ነው የሚባል ሰው ፣ የስደተኝነት ጥያቄው አሉታዊ መልስ እንዳሰጠው አውቆ ከከራረመ በኋላ ፣ እንደ ነገ ከመጣበት አግር ወደ እስፔን ሊመለስ በፖሊሶች ዝግጅቱ አልቆ ሳለ መረጃውን ከየት እንዳወቀ ባልታወቀ ምክንያት ፣ ክተጠለለበት ካምፕ ወጥቶ አውቶብስ ይዞ እንደወጣ ፣ ሰይጣን ጆሮው ላይ ምን ሹክ እንዳለው ሳይታወቅ ፣ ከካምፑ ይዞት በወጣው ቢለዋ ፣ አውቶቡሱን አግዶ በአውቶቡስ ውስጥ ያሉትን ሶስት ሰዎች ይገድላል ፡፡
በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ሰለባ የሆኑት ፣ የአውቶቡሱን ሾፌር ጨምሮ ፣ አንዲት የ19 አመት ሴት ልጅና አንድ ስዊድናዊ ዜግነት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ ፡፡ሁለት ኖርዌጅያኖችና አንድ የጎረቤት አገር ስዊዳናዊ ሰው ፡፡ ይህ ግድያ አንድ መዘዝ ጎትቶ እዚህ ኖርዌይ ያለነውን ኢትዮጵያውያኖችም ሰሞኑን አንገታችንን እንድናጎነብስ እያደረገን ነው ፡፡ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2003 ዓ.ም አንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰው እንዲሁ ፣ በአንድ ካምፕ ውስጥ አብሮት የነበረውን አንድ የኮንጎ ዜጋ ገድሎ ሲያመልጥ ፣ እርሱም እንዲሁ የተሳፈረበትን አውቶቡስ ሾፌር ገድሎ ተይዟላ ፡፡ከአስር አመት በፊት የተፈጸመው ይህ ክስተት ሰሞኑን ፣ የኖርዌይ ጋዜጦችን አጣቧል ፡፡ ኢትዮጵያዊው ! ኢትዮጵያዊው እየተባለ ፡፡ህዝቡ የሰሞኑ ግድያ አንገፍግፎት ሳለ ! መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ከአስር አመት በፊት በኢትዮጵያዊው ገዳይ የተፈጸመውንም በአዲስ መልክ በማራገባቸው ፣ ህዝቡ ለምን አስር አመት ሙሉ እዚህ አገር ተቀመጠ ? ለምን ወደ አገሩ አልተጠረዘም በማለት መንግሥታቸው ላይ በማጉረምረማቸው ፣ ከሶስት ሳምንት በፊት ስልጣን የያዘው አክራሪ የቀኞች አዲስ መንግስት ፣ ጥፋቱ የቀድሞዎቹ የግራ መንግስቶች ችግር ነው ፣ እስከዛሬ ቁጭ አድርገው ሲቀልቡት በማለት ፣ ጦሱን ከስልጣን ለወረደው መንግስት አቀብለውታል ፡፡ ኢትዮጵያዊው ገዳይ ከፍተኛ የአይምሮ መቃወስ ችግር ያለበት ሰው ስለሆነ ፣ ወደ አገሩ ከህመሙ ሳይድን መስደድ አንችልም ፡፡ በዚህ ህመሙ አገሩ ብንሰደው የአገሩን ህዝብ ሊጨርስ ስለሚችል የግድ መዳን አለበት ፣ ወደ አገሩ ከመላኩ በፊት እያሉ የጤና ኃላፊዎቹ ፈርጥመው እየተናገሩ ነው ፡፡ እስቲ እንግዲህ አስቡት ፡፡ የአገራቸውን ዜጎች የገደለባቸው የኖርዌይ መንግስት ሹሞች ፣ ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያ ውስጥ ሄዶ ህዝብ ስለሚገድል፣ አክመን አድነን ነው የምንሸኘው ብለው ሲከራከሩ ፣ የአገራችን መንግሥት ደግሞ ፣ ዜጎቹ በአረብ አገር እንደውሻ ሲታደኑ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሏል ፡፡ምን አይነት ጊዜ ላይ እንደደረስን አይገባኝም ፡፡ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን እንደዛሬው አረብ አገር ቤንዚን ወጥቶ እንዲህ ሳይቀማጠሉ በፊት ለሃማልነት/ ወይም ኩሊነት እንዲሁም ለግንበኝነት ስራ ተቀጥረው ኢትዮጵያ ውስጥ አረቦችን ያሠረና ያበላ ህዝብ ነው ዛሬ በተራው ተዋርዶ በአረብ አገር የሚገደለው ፡፡ ይህ ታሪክ ለአዲሱ ትውልድ በደንብ መነገር አለበት፡፡ ዛሬ የመንን የሚያስተዳድሩት ሚንስትሮች አብዛኞቹ ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው አረቦችና ፣ መወለዶች ናቸው በልጅነታችን አረብ ሱቅ ሄዳችሁ ቡና ግዙ ስንባል በከረሜላ ምርቃት የሚያፈዙን ኢትዮጵያ በግንበኘነት ቀጥራ ያመጣቻቸው አረቦች ነበሩ ሱቅ ከፍተው አገራችን የከበሩት ፡፡ እስቲ እዚህ ላይ የምታውቁትን ታሪክ አክሉበት ፡፡ አዲሱ ትውልድ የግድ ታሪኩን ማወቅ አለበት ፡፡
Engida Tadesse
No comments:
Post a Comment