ከመሬት፣ እንዱ ስትሪና ከተማ ፤ልማት ጋር በተያያዘ ከ990 ሺ በላይ አቤቱታዎች መፍትሄ ማጣታቸው ተመለከተ። ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል። የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት ተስኖታል። የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ከዚህ መነሻ ዕቅድ በመነሳት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ፤የክልል ተቋማትና የዞን አስተዳደሮችም የየራሳቸዉን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ገብተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተከፈተው ሃገር አቀፍ የመልካም አሰተዳደር ንቅናቄ መድረክ የመግቢያ ማስታወሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ህዝብን ማእከል ያደረጉት የመልካም አሰተዳደር ስራዎች ገና አልተንቀሳቀሱም ፡፡ ህዝብን ያማረሩ ፤ የሚያሰለቅሱ አሰራሮች ግን አሁንም አንደተሸከምናቸው ናቸው ሲሉ የችግሩን ግዙፍነት አስታውሰዋል፡፡
ከመሬት፣ እንዱ ስትሪና ከተማ ፤ልማት ጋር በተያያዘ ከ990 ሺ በላይ አቤቱታዎች መፍትሄ ማጣታቸው ተመለከተ።
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል።
የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት ተስኖታል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ከዚህ መነሻ ዕቅድ በመነሳት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ፤የክልል ተቋማትና የዞን አስተዳደሮችም የየራሳቸዉን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ገብተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተከፈተው ሃገር አቀፍ የመልካም አሰተዳደር ንቅናቄ መድረክ የመግቢያ ማስታወሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ህዝብን ማእከል ያደረጉት የመልካም አሰተዳደር ስራዎች ገና አልተንቀሳቀሱም ፡፡ ህዝብን ያማረሩ ፤ የሚያሰለቅሱ አሰራሮች ግን አሁንም አንደተሸከምናቸው ናቸው ሲሉ የችግሩን ግዙፍነት አስታውሰዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የስምንት መስሪያ ቤቶች የሱፐርቪዝን ጥናት ሪፖርት ተጠናክሮ ቀርቧል፡፡ በቀረበው ሪፖርት እንደተጠቀሰው ሰራተኛዉን በወር አንድ ጊዜ ስለመልካም አስተዳደር እንዲሰበሰብ የሚያዘው ህግ ተግባራዊ አልሆነም።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ዘርፍ አሰተባባሪ አቶ ሙክታር ከድር አንዳሉት በመሬት አሰተዳደር ችግር ብቻ በመላ ሃገሪቱ 670 ሺ 857 አቤቱታዎች ቀርበዉ ምላሽ አልተሰጠም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የ9 ሺ 964 መሬት ነክ አቤቱታዎች በሽምግልና መፍታቱን ጠቁመዋል ።
የራስ አገዝ ማህበራት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሠጣጥ ፤የስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም እንዲሁም የቦታ ስታንዳርድ መመሪያ ፡ ጥራት የሌላቸው መሆኑ በሚኒስትሩ ተገልጿል።
በአቶ ሙክታር መሰረታዊ ችግሮች ናቸው ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል ህጋዊ የመሬት ይዞታ ሠነድ ጥያቄ ፤ለተንጠለጠሉ ጉዳዮች በፍጥነት ምላሽ አለመስጠት፤መሬት አሠጣጡ ያለአግባብ ነው ተብሎ በከፍተኛ አመራሩ ውሳኔ ያረፈባቸው ጉዳዮችና ችግሮች እንዲስተካከሉ አለማድረግ፣ይገኙበታል ፡፡ እንዲሁም መሬት መስጠት ከመታገዱ በፊት በህጋዊ አግባብ መሬት እንዲያገኙ የተወሠነላቸውና ህጋዊ ሠነድ ያላቸው ግን ደግሞ መሬት ያላገኙ ግለሰቦች መሬት እንዲያገኙ አለማድረግ፤ተጠያቂነትን አለማረጋገጥ፤ዉሳኔ የተላለፈባቸዉን ጉዳዮች ያልፈፀሙ አመራሮችና ባለሙያዎች በህግ እንዲጠየቁ አለማድረግ፣የዲዛይን ምርመራና ፈቃድ አገልግሎት መዘግየትና የጥራት መጓደልን ማስተካከል አለመቻል፣ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የወጣውን የተሻሻለ አዋጅ አለማስተግበር የዘርፉችግሮች ናቸው ተብሏል፡፡ESAT
No comments:
Post a Comment