Monday, November 11, 2013

መከራው ቀጥሏል - የኛም ጩኸት እንዲሁ ይቀጥላል! ኩዌት ደግሞ ሌላ የኛን ትኩረት የሚሻ ነገር ዛሬ ተፈጽሟል። በኩዌት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 1ሺ የሚሆኑት የሚሰሩት በአንድ የጽዳት ኩባንያ ውስጥ ነው። ነገር ግን በምን ምክንያት እንደሆነ ባልተገለጸ ሁኔታ ይኸው የጽዳት ኩባንያ 1ሺዎቹንም ኢትዮጵያውያን ከትናንት እሁድ ጀምሮ ከሥራ አባሯል። ኩዌት ታይምስ ዛሬ ህዳር 2 (ኖቬምበር 11) እንደጻፈውና ድንቅ መጽሔት እንደተረጎመው ወሬ ከሆነ ፣ ሰራተኞቹ ለምን እንደተባረሩ አላውቁም። እነዚህ የኛ ወገኖች ሜዳ ላይ ወድቀው ለማኝ ሊሆኑ ነው? ወይስ ኩዌትም እንዲሁ ውጡ ብላ ዘመቻ ልትጀምር ነው? እነሱ ግን ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ መባረራችንን እንቃወማለን ብለዋል። አላግባብ ወገኖቻችን ብቻ ተለይተው መባረራቸው በሚመለከተው የኩዌት መንግስት አካል ሊመረመር፣ የተባረሩትም ወደሥራቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ እንጠይቃለን። በተባበሩት መንግስታት የሰብ አዊ መብቶች ቻርተር መሰረት ማንም ሰው ሰርቶ የመኖር መብት አለው። በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ጥቂት ሰዎች ሊባረሩ ይችሉ ይሆናል፣ ኢትዮጵያውያኑን በሙሉ ማባረር ግን ከማንነት ጋር የተያያዘ በደል እንዳለ የሚያመላክት ነው።






1 comment:

  1. من افضل شركات تنظيف بالدمام هى شركة ركن الجوده لتتنظيف فى الدمامشركة تنظيف منازل بالدمام

    ReplyDelete