Saturday, November 9, 2013
ሪያድ ከተማ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ በሳኡዲ ፖሊስ ዳግም እየታመሰች ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ትዊተር ላይ ይዝናናሉ::#Ethiopia #Saudiarebia @DrTedros ሪያድ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት በሰላም ሃገራችን አሳፍሩን አትደብድቡን ብለው ከየቤታቸው ነቅለው መወጣታቸው ያስበረገጋቸው የሳኡዲ ፖሊሶች እጁን በሰላም ለመስጠት አደባባይ የወጣውን ከ 600 የሚበልጥ፡ ኢትዮጵያዊ ለመበተን የሃይል እርምጃ ወስደዋል:: ኢትዮጵያውያኑ አሁን ማምሻውን በገዛ ቤታችን ከምታሰቃዩን በአደባባይ ግደሉን ብለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከየቤቱ በመውጣቱ በፖሊስ እና በኢትዮጵያውያኑ መሃከል በተፈጠረ ግጭት የመንገድ ትራፊክ ተስተጓጉሏል:: የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተጨማሪ ሃይል ወደ ተጠቀሰችው መንደር በምጣት የኢትዮጵያውያኑ ላይ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸው እይተነገረ ባለበት ሰአት ኤምባሲው በቦታው ነኝ ቢልም በቦታው ለመኖሩ መረጃዎች የሉም:: ድ/ር ቴዎድሮስ እንደ ቀላል ነገር በትዊተር ዘና ብለው እየተዝናኑ መሆኑ ይበልጥ አሳፋሪ ስራዎች መሰራታቸው ኢትዮጵያውያኑን ከ ሳኡዲ ፖሊሶች ይልቅ የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ የሚለው ወያኔ እየገደላቸው ነው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment