Sunday, November 24, 2013

ሰበር ዜና ሪያድ-በኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።

ሪያድ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ውስጥ፡ግዜያዊ መጠለያ ሜዳል ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ። 
ሪያድ መንፉሃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ሰሞኑንን በውሳዲ ፖሊሶች ታፍሰው ከከተማይቱ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኝ፡ በተለምዶ ሚንዛህሚያ እየተባለ የሚጠራ እስርቤት ተወስደው ከነበሩ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን መሃከል ግማሽ፡ያህሉ በ 17 አውቶብስ ተጭነው ማምሻውን ሪያድ ከተማ አሚራ ኑራ እየተባለ የሚጠራ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተከትሎ ከባድ ሁከት መቀስቀሱን ከሪያድ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ ።
ይህን ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ፡በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል ከባድ ግጭት መከሰቱን የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች አዲት ነፍሰጡር ሴት ከድንጋይ ውርወራው ለማምለጥ፡ ከግቢው ለመውጣት ሲበሩ በነብሩ አውቶብሶች በአንዱ ተጭፍልቃ መሞቷን ገልጸዋል። ግጭቱ በጣም ዘግናኝ፡አሰቃቂ እንደነበር የሚገልጹት የአይን ምስክሮች የሳውዲ ፖሊሶች ማንም ሰው ካሜራ እንዳይቀርጽ ለማገድ ከአካባቢው ኢትዮጵያውያኑንን በማራቅ አስከሬኑን ነጭ ነገር ሸፍነው በቅጽበት በአንፖላንስ ተጭኖ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ዛሬ ረፋዱ ላይ በ 17 አውቶብስ ተጭነው ሚንዛህሚያ እይተባለ ከሚጠራ አካባቢ እንደመጡ ከሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያንመሃከል በአብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና ነፍሰጡር እንደሆኑ የሚናገሩት ምንጮች አውቶብሶቹ የተጠቀሰው አካባቢ ሲደርሱ በውስጥ፡የነበሩ ኢትዮጵያውያኖች ኤርፖርት እንወስዳችሃለን ብላችሁ እዚህ ባዶ ሜዳ ላይ አምጥታችሁ ለምን ትበትኑናላችሁ በማለት ከአውቶብሱ አንወርድም በሚል የኡ ኡ ታ ጩሀት በማሰማት ተቃውሞቸውን ሲገልጽ የሳውዲ ፖሊሶች የአካባቢውን ጸጥታ ያደፈርሰውን የህዝብ ኡ ኡታ ጩህት ለማርገብ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት ድንጋይ ውርወራ መጀመሩን የሚገልጹ እማኞች በፖሊስ እና በህዝቡ መሃከል በተነሳው ግጭት አያሌ ህጻናት እና አረጋውያን መረጋገጣቸውን በመጥቀስ እስካሁን በወገኖቻችን ህይወት ላይ የደረሰው አደጋ በውል ባይታወቅም ብዛት ያላቸው አንፑላሶች ኢትዮጵያውያኑ ከተጠለሉበት ግቢ «ሳይረን» እያሰሙ ሲወጡ መታየታቸውን አክለው ገልጸዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ ሚን ዛህሚያ እይተባለ ከሚጠራው መጠለያ በ 17 አውቶብሶች ተጭነው የመጡጥ ወገኖቻችን ከአውቶብሶቻቸው እንዳልወረዱ እና በአሁኑ ሰአት ብጥብጡ ተባብሶ መቀጠሉ ተገልጾል። ቀደም ሲል ለፖሊስ አሻራ ትሰጣላችሁ ተብለው ከተለያየ አካባቢ ሪያድ ከተማ መለዝ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ዩንቨርሲት ግቢ ውስጥ፡ እስከ 7 ሺህ የሚጠጉ ወገኖቻችን ያለዳስ « ድንኳን » ሜዳ ላይ ተጠለው ፀሃይ ብርድ እና ዝናብ እይተፈራረቀባቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሎል ።
በዚህ ዙሪያ ጉዳዩ ወደ ሚመለከታቸው በሪያድ የኢትዮጵያ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ስልክ በመደወል ስለጉዳዩ ለማነጋገር ያደረኩት ጥረት እስካሁን አልተሳካም ! የዲያስፖራው ሃላፊ ክቡር ዲፕሎማት አቶ ተመስገን ኡመር ተሌፎን ቁጥር ይህ ሁከት ከተቀሰቀስ ወዲህ መስመሩ ከአገልግሎት ውጭ ነው የሚል መለዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ የኤባሲውን ተጠሪዎች እሳክሁን ማግኘት አልተቻለም ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment