Friday, November 22, 2013

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።  
በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከ አንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ፡አውቂ ምንጮች ገልጸዋል። 
አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል እራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒትው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ጉዳዩቻቸውን ተከታትለው ሊያስፈጽሙላቸው ባለመቻላቸው በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ግቢ በሚገኝ፡አንድ ኮንቴነር ውስጥ፡ሲሰቃዩ መኖራቸውን የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። ከ 12 በላይ ነፍሰጡሮች እና የአይምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ያለምንም የህክምና እርዳታ ሲሰቃዩ ከከረሙት እህቶቻችን ውስጥ 3 ቱ በሞት መለየታቸውእና 5ቱ ለአይምሮ ጭንቅት መዳረጋቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ የማይጠፋ መሪር ሃዘንመሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሰሞኑንን መንፉሃ ውስጥ፡የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደ ገባ ለሚነገርለት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሎኡካን ቡድን ገበናችንን ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ዲፕሎማቱ እነዚህን ወገኖቻችንን ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶብስ ጭነው መውሰዳቸው ትክክል እንዳልሆነ ይገልጻሉ። 
ስደተኞቹ የሉበት ሁኔታ እስካሁን በውል እንደማይታወቅ የሚናገሩት የሪያድ ምንጮች ምናልባት ወደ አህገራቸው ለመግባት ለፖሊስ እጅ ስጠተው በየ ግዜያዊ ጣቢያ ከሚሰቃዩ ወገኖቻችን ጋር ቀላቅሎዋቸው ሊሆን እንድሚችል ግምታቸውን ያሚያጠናክሩት እንዚህ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ኮኔትንር ውስጥ ላለፉት ወራት ያሳለፉትን የችግር እና የመከራ ግዜያቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩቻቸውን ባሉበት በማስፈጸም ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ይገልጻሉ ። ዲፕሎማቱ የፈጸሙት ድርጊት ወገናዊ ነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹ ምንጮች የተጠቀሱት እህቶቻችን ኮሚኒቲው መጠለያ ግቢ ውስጥ፡በነበሩባቸው ግዜያቶች አንዳንድ እህቶቻችን በዲፕሎማቱ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ሽፋን ማታ ማታ እይተጠሩ እዛው ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር በማስታወስ በእህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት ሳይፈጸምባቸው እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
እንዲህ አይነት አስጸያፊ ድርጊት አልፎ አልፎ የሚከሰት መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ መከስቱን ተከትሎ ኮሚኒው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አናባቶች ወጀለኛውን ፍ/ቤት በማቆም 60 ሺህ ሪያል ካሳ እንዲከፍል ማስወሰናቸውን የሚያወሱ አንድ አባት ጉዳዩን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ተከታትሎ እንዲያሰፈጽም አደራ ቢሰውም ሃላፊነቱን በብቃት ሳይወጣ በመቅረቱ ወንጀለኛው ከእስርቤት ተለቆ ተበዳይ እህት ሰሞኑንን ከሌሎች ወገኖቻንጋር ወዳልታወቀ ስፍራ እስከተወስደችበት ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ግቢ ውስጥ በህመም ስትሰቃይ እንደነበር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል ። በተመሳስይ ሁኔታ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሚገኙ እህቶቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መሞከሩን የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች አንዲት ወጣት በቆንስላው ጽ/ቤት ዘበኛ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ጉዳዩ ፍ/ቤት ደርሷ እንድነበር እና በቆንስላው የመንግስት ባለስልጣኖች ተድበስበሶ መቅረቱ የሚያስታውሱ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ የኖሩ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ የ12 ቱ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ጉዳይ ሳይጣራ ሰሞኑንን በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ ከኮሚኒው ግቢ በስቸኳይ እንዲለቁ መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥርጣሬ የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል፡
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment