ESAT መንግስት የሰማያዊ ፓርቲን ሰልፍ በሀይል በተነ፤ በርካቶች ተደበደቡ፤ ታሰሩ በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አከባቢ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመ ነው። አሁን በስልክ ያገኘናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች አመራሮች በእንባ ታጅበው ሲቃ ይዟቸው ''የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረደን'' ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወጣት ይድነቃቸው ከበደ እና ወጣት ሀና ዋለልኝ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ወደ 50 የሚጠጉ የፓርቲው አባላትና የሰልፉ ታዳሚ ወደ እስርቤት ተወስደዋል። ''በህግ አምላክ! እያለን እየጮህን በፌደራል ፖሊስ ተቀጠቀጥን" አለ ወጣት ይድነቃቸው። ''ወገን አለቀ ሳኡዲ አረቢያ ከሚገደሉት ከሚቀጠቀጡት ባልተናነሰ እኛም በሀገራችን ግፍ ተፈጸመብን'' ብላለች ወጣት ሃና። ''ኢትዮጵያዊ መንግስት ከወዴት ነው ያለነው?'' የዛሬው ከፍ ብሎ የሚሰማው ጩኸት!
No comments:
Post a Comment