Monday, November 18, 2013

ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪ.. በታላቁ ሩጫ ላይ ሀዘናችንን እንግለፅ!

ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪበሳዑዲ ለሚሞቱና ለሚንገላቱ ወገኖቻችን ያለንን ተቆርቋሪነትአሁንም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባዉሰልፍ የተፈፀመዉን መንግስታዊ ሽብር ሁላችንም በሀዘንአልፈነዋል፡፡ ነገር ግን ለብሔራዊ ቡድናችን ያደረግነዉ ጥሪበቸልተኝነት መታለፉ ፣ በሀይማኖት ተቋማትም የሚፈለገዉን ያህል ጥሪዉን ባለመቀበላቸዉ የዘንን ቢሆንም ህዝቡን ከጎናችንበማቆም የደረሰበትን ነገር ሁሉ በፅናት መቀበሉ አኩርቶናል፡፡ በቀጣይነትም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ታስቧል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ በመጪዉ እሁድ ህዳር 15 ቀን በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ ላይ የምንሳተፍ ሰዎች ጥቁር ሪቫኖችን አድርገን እንድንሳተፍ፤ በአንድነት መንፈስም አጋጣሚዉን በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ሰዎች ድምፃችንን የምናሰማበት ሀዘናችንን የምንገልፅበት እንዲሆን ሰማያዊ ፓርቲ በ ወገኖቻችን ስም ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
የሰማ ላልሰማ ያሰማ!!

No comments:

Post a Comment