Monday, November 18, 2013

በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ? “… በየምሽቱ ሁላችንንም ወደ ምርመራ ክፍል ይወስዱናል ፡፡ ከዚያም እያንዳችንን ለያይተው ይገርፉናል ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስጠራ ሶስት ወንዶች በክፍል ውስጥ ይጠብቁኝ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑ ሶስቱም በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ ፡፡ ወደነበርንበት ጉድጓድ ስመለስ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየሁ ነበር ፡፡ አሁን ድረስ ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ፡፡ በዚያ እስር ቤት ለሶስት ወራት ስቆይ በ12 ወታደሮች በተደጋጋሚ ተደፍሪያለሁ ፡፡ በግርፊያውና በአስገድዶ መድፈሩ ላይ የአካባቢው ኮማንደርም ተሳታፊ ነበር ፡፡ በዚያ የነበሩ ልጃገረዶችም ሆኑ እናቶች በሙሉ ተደፍረዋል ፡፡ በሶስቱ ወራት ውስጥ ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሴቶች የእኔ እጣ ደርሷቸዋል ፡፡ ” በኦጋዴን አካባቢ ታስረው ከተፈቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሂዩማን ራይትስ ዎች ካናገራት አንዲት ወጣት ታሪክ የተቀነጨበ፡፡ ምንጭ “ፋክት” መፅሄት ቁጥር 19 ጥቅምት 2006 እትም በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?

No comments:

Post a Comment