በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውጥረት ነግሷል፡፡ (Minilik Salsawi)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውጥረት ነግሷል፡፡
በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 5ኪሎ ግቢ(institution of technology) ተማሪዎች ከ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይወጡ መከልከላቸው ታወቀ፡፡
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 5ኪሎ ግቢ(institution of technology) ተማሪዎችን በአክራሪነት እና ጽንፈኝነት ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በማቀድ የግቢውን ተማሪዎች ለመስብሰብ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች የገለጹ ገልጸዋል::
ሆኖም ግን በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ተማሪዎች በአክራሪነት ዙሪያ እንደማይወያዩ እና ሙስሊም ተማሪዎቹ የጁምአ ሰላት ስግደት ስላለባቸው ለመውጣት ቢሞክሩም የግቢውን ቅጥር ግቢ በመዝጋት ወደ ስብሰባው ቦታ በግደጅ ለማስኬድ መኪና ውስጥ እያስገቧቸው እንደደሆነ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment