Tuesday, October 22, 2013

ባለፈው ሳምንት በቦሌ ሩዋንዳ የተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑ ተረጋገጠ::ፖሊስ ምርመራውን አልያዝኩትም የማውቀው ነገር የለም ብሏል::

ፖሊስ ምርመራውን አልያዝኩትም የማውቀው ነገር የለም ብሏል::
ባለፈው ኦክቶበር 13 2013 በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ከመደረጉ ቀደም ብሎ በቦሌ ኡዋንዳ አከባቢ የደረሰው ፍንዳታ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሸበር በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ የአይን እማኞች ለ ተናግረዋል::

addis ababa terrorist explosion

እንደ እማኞቹ መረጃ ከሆነ ከፍንዳታው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ ለሊቱን ከምንሊክ ሆስፒታል ሁለት አስከሬኖች ተዘጋጅተው ወደ ፍንዳታው ሚፈጸምበት ቤት በደህንነት ሃይሎች የተወሰዱ ሲሆን ለዚሁም ስራ ይረዳ ዘንድ ቀደም ብሎ መኖሪአ ቤቱን ከሶማሌ ክልል በደህንነት ሃይሎች ተገዝተው በመጡ ሶማሊዎች እንዲከራዩት ተደርጎ የተዘጋጀ እና የሬሳዎቹን መግባት ተክትሎ ተከራዩ የተባሉት የሶማሌ ተወላጆች ከፍንዳታው ቀደም ብሎ በስውር ወተው ከአከባቢው መሄዳቸው ታውቋል::

ይህንን ዘገባ ያጠናከረው የምርመራ ቡድን እንዳገኘው መረጃ ፍንዳታውን ያቀነባበሩት በሕወሓት የመረጃ ባለስልጣን ደብረጺሆን እና በደህነነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የሶማሊ ተወላጆችን ቀጥታ ከክልልሉ በመግዛት በሕወሓት ልዩ ስሙ 03 ተብሎ በሚጠራው የደህንነት እና የስለላ ቡድን ስር ፍንዳታው እንዲፈጸም ያደረጉ መሆኑ ተደርሶበታል::የእትዮጵያ ሪቭኢው ያነጋገራቸው የአከባቢው የፖለስ ጣቢያ የጸጥታ ሰዎች እና መርማሪዎች ጉዳዩን እንዳልያዙት እና ምንም መረጃ እንዳሌላቸው የተናገሩ ሲሆን የቤቱን ባለቤት ጨምሮ ማንም ሰው ላይ ምርመራ እንዳላደረጉ እና ምንም ማስረጃዎች እንዳሌላቸው ተናግረዋል::
የበለጠ መረጃ እና ከዚህ ቀደም የወያኔ ጁንታ ያደረጋቸውን የሽብር ወንጀሎች ከፈለጉ ይህንን ሊንክ ተጥነው ያገኙታል::
http://www.ethiopianreview.us/49642

No comments:

Post a Comment