
ተማሪዎቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ፈተና ድንገት መውሰድ የለብንም ከተማሪዎቹ መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት ውጤት በማጣት ከትምህርት ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለማጥናት ጊዜ ይሰጠን ቢሉም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ምሳ እንደከለከልና ትናንት ጠዋትም ቁርስ ከከለከለ በኋላ አለመግባባቱ ተካሮ በመሄድ ማምሻውን ደግሞ ማደሪያም በመከልከሉ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ካለምንም ህጋዊ ማስታወቂያ በአስተዳደሩ ሳቢያ በግድ ከዩኒቨርሲቲው ከወጡ በኋላ በአካባቢው ባሉ ቤተክርስቲያኖች፣ ሆቴሎችና በየሰው ቦታ እንደተጠጉ ተገልጿል።
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ትዘግባለች።
No comments:
Post a Comment