ኢትዮጵያዊቷን የማደጎ ልጅ በርሀብ የገደለችው አሜሪካዊት በ37 አመታት እስራት ተቀጣች ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment