Friday, October 18, 2013

አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እሥረኞች ቁም ስቅል የኢትዮጵያ ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት የፖለቲካ እስረኞችን ቁም ስቅል እንደሚሳይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዘገባ ፖሊስ የፖለቲካ እስረኞችን እውነትም ይሁን ውሸት የተለያዩ ወንጀሎች መፈፀማቸውን ለመናገር እስኪስማሙ ድረስ ቁም ስቅል እንደሚያሳይ አስታውቋል ።

By zenebu on

ዜና | 18.10.2013 | 16:47

የኢትዮጵያ ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት የፖለቲካ እስረኞችን ቁም ስቅል እንደሚሳይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዘገባ ፖሊስ የፖለቲካ እስረኞችን እውነትም ይሁን ውሸት የተለያዩ ወንጀሎች መፈፀማቸውን ለመናገር እስኪስማሙ ድረስ ቁም ስቅል እንደሚያሳይ አስታውቋል ።

 በHRW አጥኚ ሌስሊ ሌቭኮቭ

« በዘገባው ከአንዳንድ ሰዎች መረጃ ለማግኘት ወይም የሚጠየቁበትን ጉዳይ ፈፅመናል ብለው እንዲያምኑ ለማድረግ እንዴት እንደተደበደቡ ወይም ቁምስቅል እንደሚፈፀምባቸው ወይም በአሰከፊ ሁኔታ እንደተያዙ ተመልከተናል ። እንዲሁም ሰዎች በከፋ ሁኔታ እንደሚያዙም አሳይተናል። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ብርሃን በማይገባበት ጨለማ ቤት ውስጥ ይታሰራሉ ። »

HRW ባለፉት ሶሶት ዓመታት ፖሊስ በምርመራ ወቅት ጥፊና እርግጫን ጨምሮ በድብደባም እስረኞችን እንደሚያሰቃይ እስረኞችን በእማኝነት ጠቅሶ ዘግቧል ። 35 የቀድሞ እስረኞችን ማነጋገሩን የጠቀሰው HRW አንዳንዶቹ ሰውነትን እጅግ በሚያስጨንቅና በሚጎዳ ሁኔታ ይያዙና እጃቸው በገመድ ተንጠልጥሎም ይገረፉ እንደነበር መናገራቸውን አስታውቋል ።
የኢትዮጵያ መንግስት ዘገባውን ሃሰት ሲል አስተባብሏል ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ
ድምፅ
http://www.dw.de

No comments:

Post a Comment