ጥቅምት 3/2006 ዓ/ም በአ/አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በፈነዳው ፈንጅ የሞቱት ዜጎች ሶማሊያዊያን መሆናቸውን የሚገልጽ በኢህአዴግ ሚድያ የተሰራጨው ዘገባ ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ የተደረገ እንደሆነና በአደጋው የሞቱት ሁለት ሰዎችኢትዮጵያዊያንመሆናቸውንበመታወቅያ ወረቀታቸው ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን የሟቸቹ ስምም ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባለ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባለ ሲቪል መሆናቸውን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ከአደጋው ጋር በተያያዘ በአከባቢው ታይታችሃል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት የታሰሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል አቶ ፍስሃ ገ/ዮዋሃንስ ፤ አቶ አብርሃ ታወቀና አቶ መርእድ ገ/ስላሴ የተባሉ የኢዴፓ አባላት ይገኙበታል፣
No comments:
Post a Comment