Friday, October 11, 2013
በሐረማያ ዩንቨርስቲ የመንግስት ባለስልጣናትና የዩንቨርስቲዉ አመራር በጠሩት ስብሰባ ላይ ጽኑ ተቃዉሞ ገጠማቸዉ
መስከረም 30/2006) ቢቢኤን ዋሽንግተን ዲሲ፦ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ዛሬ ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት መበተኑ ታወቀ።
የስብሰባዉ ተሳታፊዎች በግልጽ መንግስት ስም እያመጣ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው የተማረዉ የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ቀርቶ ዛሬ አባቶቻችንም አይቀበሉትም የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል በማለት ተማሪዎችና የዩንቨርስቲዉ መምህራን የመንግስት ባለስልጣናትን መሞገታቸዉ ለማወቅ ተችሏል።
ጽንፈኛ የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት ክርስቲያን ታዳሚ መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች ጦርነት በክርስቲያኑ ላይ ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ህዝበ ክርስቲያኑ እንደማያምን በመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘ ተዓማኒት የለዉ መሆኑን ገልጸዋል።
ዩንቨርስቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለዉ የገለጸ ቢሆንም ታዳሚዎቹ በሐይማኖት ሳይለያዩ ሐሳቡን ዉድቅ ማድረጋቸዉ ም ታዉቋል።ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደልም የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መተግበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም የሐማኖት አልባሳት ከበር መልስ የሚለዉ የዩንቨርስቲዉ እቅድ ተቀባይነት የለዉም ሰዎች ሐይማኖታዊ አለባበሳቸዉን ከቀየሩ አማለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ ተቀባይነት የለለዉ ነዉ በማለት ሐሳባቸዉን የገለጹም ነበሩ።
ሽብር በሌለበት አገር ስለ ሽብር ማዉራቱ ነራሱ ማሸበር ነው ያሉት ሌላ ተሳታፊ ሙስሊም እንደመሆናችን በቀን አምስት ግዜ መስገድ አለብን በዶርም (በማደሪያ) ዉስጥ መስገድ ከተከለከልን ግቢዉ ዉስጥም እንዳንሰግድ ከተደረግን አስቸጋሪ ነዉ የሚሆነዉ ግን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በመሆኔ በጣም እኮራለሁ ስለምን ካላቹህ ኢትዮጵያ የሰላም አገር ናትና! ምን አልባትም ሶማሊያዊ፣ናይጄሪያዊ ካልያም አፍጋኒስታናዊ ብሆን ኖሮ ይህንን ያገኘሁት ሰላማዊነት አለገኝም ነበር በማለት አስተያታቸዉን ሰጥተዋል።
ወደ ኢትዮጵያዉ መዝገበ ቃላት የሚገቡ አዳዲስ የፖለቲካ ቃላቶች እየተፈጠሩ ለስብሰባ እየተጠራን ለምን ግዜ ይባክናል? ለምን አገርን ለማስደግ ለልማት አንሰበሰብም አያዉቁም ብላቹህ አትናቁን እኛ ከናንተ የበለጠ እናዉቃለን በማለት የመንግስት ካድሬዎችን ያሳፈሩ እንደነበሩ ለማወቅም ተችሏል።
መንግስት ፍርሃትንና መፈራራትን በህዝብ ዘንድ ለማንገስ አክራሪነት፣አሸባሪት እና ጽንፈኝነት በማለት በተለያዩ የትምርት ተቋማት በስልጠናና በዉይይት ስም የሚጠራዉ ተከታታይ ስብሰባ መንግስት ኪሳራን የሚጎናጸፍበት ነዉ! ህዝቡ ከፍርሃት ተላቆ ለመብቱ እንዲታገል የሚጋብዝ መሆኑ በገሃድ እየታየ በማለት ሀሳባቸዉንም የሚገልጹ አሉ።
በዛሬዉ እለት በሐረማያ ዩንቨርስቲ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አክራሪነትንና አሸባሪነትን አስመልክቶ ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ በድምጽ እና ስብሰባዉን ረግጦ በመዉጣት ዉድቅ አድርገዉታል።
አንደ ታዛቢዎች አገላለጽ ስልጠናዉ በተገላቢጦሽ ለመንግስት የአመራር አካላት ስልጠና የተሰጠበት ነበር።
ቢቢ ኤን በዛሬዉ ፕሮግራሙ ሰፋ ያለ ዘገባ ይኖረዋል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment