Thursday, December 19, 2013
የአማራ ክልል ፕሬዝዳት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ለቀቁ::sየአማራው ክልል ፕሬዚዳት ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በመልቀቅ ስራቸውን ያቆሙ ሲሆን በምትካቸው ምክትላቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተተኩ መሆኑ ታውቋል:: በቅርቡ ኢሕኣዴግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመውን የድንበር ማካለል ተግባራቶች በመኮነን የተቃወሙት አቶ አያለው ከዚህ ቀደምም ይህንን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ አልፈርምም ብለው ምክትላቸው የነበረው ደመቀ መኮንን ፈርሞ ለታማኝነቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከት ላይ እንደወጣ ይታወቃል::
የአማራው ክልል ፕሬዚዳት ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በመልቀቅ ስራቸውን ያቆሙ ሲሆን በምትካቸው ምክትላቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተተኩ መሆኑ ታውቋል:: በቅርቡ ኢሕኣዴግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመውን የድንበር ማካለል ተግባራቶች በመኮነን የተቃወሙት አቶ አያለው ከዚህ ቀደምም ይህንን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ አልፈርምም ብለው ምክትላቸው የነበረው ደመቀ መኮንን ፈርሞ ለታማኝነቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከት ላይ እንደወጣ ይታወቃል:: ይህ በድርጅቱ ውስጥ የመተካካት ጉዳይ ሳይሆን አቶ አያሌው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁ መሆኑ ታውቋል:: አቶ አያሌው ጎበዜ ኢሕኣዴግን የተቀላቀሉት ከደርግ ውድቀት በኋላ ሲሆን በአቋማቸው ጽኑ እና ለአላማቸው ወደኋላ የማይሉ ጠንካራ ሰው እንደሆኑ ይወራላቸዋል:: የኢሕኣዴግ ታማኞች ሊያሰሯቸው እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ ሙከራቸው ያልተሳካ እና ሰሚ አካል ያላገኙ የነበረ ሲሆን ከዚህ ቀደም ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል በግል ጸብ የበላይነትን ተጠቅመው በላንቻ መኖሪያ ቤታቸው የግል እስረኛ አድርገዋቸው እንደነበር አይዘነጋም:: አቶ አያሌው ስልጣን ይልቀቁ እንጂ ድርጅታቸውን ያለቀቁ እና ወደፊትም በአምባሳደርነት እንደሚመዱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment