Tuesday, December 10, 2013

ጅዳና ጀዛን - በጅዳ እና በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞች በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት 
የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ተበራክቷል። "ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር
 ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል! " እያሉ ነው! የሰሚ ያለህ! ጅዳ - ከጅዳ 
ወደ ሃገር ቤት የሚተመለሱ ዜጎች ቁጥር ወደ 60 ሽህ መጠጋቱን መረጃ ደርሶኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጅዳ 
ቆንስል መስሪያ ቤት ከአሰሪዎች ጋር የትሰሩ ማናችሁም ዜጎች ያለማወላወል በሰላም ወደ ሃገር ግቡ በሚል 
ባሳለፍነው ያሰራጨው ጥብቅ ማሳሰቢያን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት የሚዘጋጁት ዜጎች ቁጥር ከፍ እያለ 
መጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዥ "የሳውዲ ህግ ተለዋዋጭ ነው ፣ የምህረት አዋጁን ያራዝሙት ይሆናል!" በሚል 
ያልተጨበጠ ተስፋን የሰነቁ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መዘናጋት አግባብነት እንደሌላውና " ህገ ወጥ " በሚል
 የተፈረጁ ከሃገር ይውጡ የሚለው ትዕዛዝ ከሳውዲው ንጉስ ቀጥተኛ የተላለፈ የማይታጠፍ ትዕዛዝ መሆኑን መራጃ 
ስለሆነ ዜጎች መዘናጋትን አስወግደው ያለማወላዎል ቁርጣቸውን አውቀው ይህን መልካም እድል ተጠቅመው ወደ 
ሃገር ቢገቡ ይሻላል " በሚል የሳውዲና የመንግስታችን ተወካዮች በአጽንኦት በመምከር ላይ ናቸው! ደማም - 
ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በደማም የሚገኙ ኢትዮጵያንን ወደ ሃገር መግባት ለማመቻቸት የሄዱት ልዑካን ከፊል 
ስራቸውን ሰርተው ቢመለሱም እጃችሁን ለመንግስ ት ስጡ የተባሉ ዜጎች አሻራ ለመስጠት እየተጉልሉ በመሆኑ 
ተሰምቷል። "ከስራ ወጥተን ከምንኖርበት ቤት ተፈናቅለን እየተቸገርን ነው !" ብለዋል። ጀዛን - መኖሪያ ፍቃድ 
እያለን በመኖሪያ ቤታችን፣ በስራና በየመንገዱ በሚደረግ ፍተሻ ወደ ለእስር የተዳረጉ ዜጎች ጅዳ ለሚገኙት የጅዳ 
ቆንስል ም/ ኃላፊ ለአቶ ሸሪፍ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያሰሙም ሃላፊው ከማረጋገት ከመርዳት ይልቅ እያበሳጩን 
ነው ብለውኛል። ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ አልሰሙ ይሆን? ሪያድ - በመንፉሃና በአካባቢው የሚኖሩ ቪዛን 
በደላላ ገዝተው የመጡ ዜጎች ትናነት ከእኩለ ቀን እስከ ምሽት የሚከተሉት ጥያቄዎች ተሰብስበው በሪያድ 
ኢትዮጵያ ኢንባሲ አቅርበዋል ። የማመልከቻና ጥያቄዎቻቸውን በጽሁፍ ልከውልኛል ... " ይድረስ ለኢትዮጵያ 
ኤምባሲ ዋናው ጽህፈት ቤት ሪያድ ።በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን በመቀጠል መልስ የሚሹ 
ጥይቄዎችን ለተከበረው ኤምባሲ በማቅረብ ኤምባሲያችንም ከሚመለከታቸው የሣዑዲ አራቢያ መንግስት ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ይፈታልን ዘንድ ቀጣይ ጥያቄዎችን እናቀርባለን ።እነሱም

1: ነፃ የሙያ ቅየራ /free profishional change/ ይፈቅድልን ።
 2 : ነቅል ከግለሰብ ወደ ሸሪካ እንድናደርግ ይፈቀድልን ። 
3 : በሆነ ባልሆነ ምክንያት የሚደረግ የእቃማ በላግ ይቁምልን ። 
4 : ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ። 
5 : ፖሊስ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ እያንገላታን ያለ ፍርድ ከፍለህ ውጣ እያሉ የሚፈፅሙት ምዝበራ ይቁምልን ።
 6 : ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈፅሙት የአየር በአየር ንግድ ከአንዳንድ ሳኡዲዎች ጋር በመሆን ቀርቶ ስራ እና ሠራተኛው በቀጥታ እንዲገናኙ ይደረግልን ።
 7 : ለዕድሳት የሚሰጡ ኢቃማዎች በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን።
 8 : የሳኡዲ ወጣቶች በራሳችን እና በሴት እህቶቻችን ላይ የሚፈፅሙት እንደ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር አጠቃላይ ወከባ እና በደል ይቁምልን ። 
9 : ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ የተከበረው ኤምባሲያችን ያወጠነውን የዕቃማ ሙሉ ወጪ ከነሞራል ካሳው 
ጠይቆልን በሰላማዊ መንገድ ወደ ሃገራችን የምንገባበትን ሁኔታ ይጠይቅልን።
 በማለት ለተከበረው ኤምባሲ የምናቀርበው እኛ ሪያድ የምንኖር. ቁጥራችን በቀላሉ 1000 የሚጠጋ በመንፉሃ እና 
በዙሪያ ያለን ኢትዮጵያዊያን ነን።እቃማ ይዘን ስራ ተከልክለን ያለን የተበደልን እና ነገን ያላወቅን የኢትዮጵያ ዜጎች 
ነን አፋጣኝ መፍትሔ ይፈለግ " የሚል ማመልከቻ ከ1000 በላይ ፊርማ ያሰባሰቡ ወገኖች በትናንትናው እለት 
የሪያድ ኢንባሲንና ከሃገር ቤት የመጡትን ከአምስት በላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን መፍትሔ ፈልግው አቤት ቢሉም 
መላ ማግኘቱ ቀርቶ " ጥያቄያችሁ አግባብነት የለውም ፣ ይህንን የማይሆን ጥያቄ እንዳትንገላቱ ወደ ሃገር በሰላም 
ግቡ! " የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጸውልኛል! ወደ ሃገር የሚገቡ ዜጎች ስጋት: የሳውዲን ሁከት ተከትሎ "ወደ
 ሃገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ! " ያለን መንግስት በአስከፊው ስደት ከምንበላው ቆጥበን የጠራቀምነውን ንብረት 
ይዘው ሰገቡ መመሪያ እየተባለ የሚቀረጡበትና የንብረት መውረስ በማዋከቡ ዜና ሃገር ውስጥ በሚወጡ መገናኛ 
ብዙሃን እየተነገረ ነው ። ይህ መሰል አሰራር ጉዳይ ነዋሪውን በጣሙን አሳስቦታል።መንግስት ከቀረጥ ነጻ ለተቸገሩት 
ይፈቅዳል ተብሎ ሲጠበቅ ይህ አሳዛኝ ዜና በእርግጥም አሳዛኝ እስከፊ ነው። ተቃዋሚ ተብለው የተፈረጁት ስጋት: 
በተለያየ አጋጣሚዎች መንግስት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመቃዎም ሃሳብ የሰጠ ፣ በድምጻችን ይሰማ ደጋፊነት
 የተጠረጠረ እና በሳውዲ የመንግስት ተወካዮች የአስተዳደር በደል የሰላ ሂስ በማቅረባቸው በአይነ ቁራኛ እንታያለን 
ያሉ ዜጎች ወደ ሃገር ስንገባ እንዳንዋከብ እንሰጋለን በሚል ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ይህን ስጋት ይዥ 
የጠየቅኳቸው አንድ የጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊ " ስጋቱ አይኖር ማለት ባይቻልም ይህን መሰል ስራ እስካሁን 
በገቡትበላይ አልተሰራም ፣ ከዚህ በኋላም ማሳደድ ማዋከብ ማሰር ብሎ ነገር አይኖም። ያመ ሆኖ በአልም አቀፉ 
ኢንተር ፖል ተፈላጊ የሆኑ ካሉ ይጠየቃሉ! " ብለውኛል! መረጃው በሹክሹክታ ቢደርሰኝም መረጃው እውነትነት 
አለው ፣ እናም በጅዳና በሪያድ የሚገኙ የመንግስታችን ተወካዮች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት በነዋሪው 
የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይመልሱ ዘንድ እመክራለሁ!
 ጀሮ ያለው ይስማ! ነቢዩ ሲራክ

No comments:

Post a Comment