Tuesday, December 10, 2013
ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ኢሳያስ አፍወርቂ በሱዳን ሊገናኙ ነው። ቢሮውን ዘግቶ የጠፋው በረከት ስምኦን ኢትዮጵያን በማሻሻጥ ስራ ተጠምዷል። በቅርቡ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት በወያኔ እና በሻእቢያ መካከል እያካሄድኩ ነው ያለችው ሱዳን የመጀመሪያውን ምስጢራዊ ስብሰባ በአቶ በረከት ስምኦን እና በአቶ የማነ ገብረመስቀል መካከል መጀመሩ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት የተጀመረው ውይይት በረከት ስምኦንን በስራ ወጥሯቸው ቢሮቸውን ዘግተው እንዲጠፉ አድርጓቸዋል። በቢሮዋቸው አከባቢ ያላዩቸው ሰዎች በረከት ስምኦን ከዳ እስከማለት ቢደርሱም አቶ በረከት ኢትዮጵያን በማሻሻጥ ስላ ላይ ተጠምደዋል። የድንበር ጉዳይ ያሳሰበው እና የታጠቁ ተቃዋሚዎች ጉዳይ የእግር እሳት የሆነበት ወያኔ ለሻእቢያ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በማድረግ ከስምምነት ሊደርስ ይችላል ሲሉ አቶ በረከት ለአቶ የማነ ቃል ገብተውላቸዋል። በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የሚያንጸባርቁት ኤርትራዊው ባለስልጣን አቶ የማነ ገብረመስቀል አስመራ ተወልደው ያደጉትን ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለመገናኘት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለአቶ በረከት ተናግረዋል። አቶ የማነ ሕወሓትን ማጥፋት አስፈላጊ ነው ብለው የሚናገሩ ናቸው። በቅርቡ በሱዳን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን እና አቶ ኢሳያስ አፍወርቂን ለማገናኘት የታቀደ ሲሆን ለዚሁም ውይይቱ በተከታታይ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሱዳን ካርቱም በመመላለስ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። ~~EthiopianReview~~
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment