DECEMBER 27, 2013

ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ የዩኒቨርስቲው የመማሪያ ክፍሎች መስታውቶች የሰባበሩ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ፖሊሶችን በመጥራት እርምጃ እንዲወሰድባቸው አድርገዋል። በርካታ ተማሪዎች ወከባና እስሩን በመፍራት ወደ የቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውም ታውቋል።
የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ” የሌላ ብሄር ተወላጆች ንብረታችሁን እያወደሙ ነው የሚል ቅስቀሳ በማካሄድ” ተማሪዎችና የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማጋጨት ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ዩኒቨርስቲው በእስር ላይ የሚገኙትን ተማሪዎች ለማባረር በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአስተዳዳራዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተለያዩ ጊዜዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ቆይተዋል።
No comments:
Post a Comment