DECEMBER 24, 2013
አንጀታቸው እጥፍ ያለ፣ በርሃብ የከሱና የጠቋቆሩ፣ የሚለብሱት የሌላቸው 102 ልጆች እስር ቤት ገብተው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፈልገው እሰሩን ቢሉም ጭራሽ ፖሊስ ከቦታው እንዲሄዱ አባረራቸው፡፡ ነፍሳቸውን ለማዳን ሮጡ፡፡ ጥለውት የሮጡትን ልብስ እና በእንደ ብርድ ልብስ የሚጠቀሙበትን ከሰው ያገኙትን ልብስ ሰብስበው ፖሊሶቹ አቃጠሉባቸው፡፡ በዛ አጥንትን በሚሰብር ብርድ እንዲሁ ራቁታቸውን አድረው ጦም ውለው ነው እንግዲህ እኔ የደረስኩት፡፡ ምንስ ባደርግ የተሰመማኝ ሀዘን ከውስጤ ይወጣል፡፡ አማራጭ የለኝም፡፡ ዞሬ የሄድኩበት እና ቆሞ የሚጠብቀኝ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡ ሄለን እና ነጅብ በመለቀው ቪዲዬ ላይ ታዩዋቸዋላችሁ እነሱን ይዤ ለ100 ሰው ምግብ ላገኝ የምችልበትን አካባቢ እና ሆቴል ፍለጋ ዳከርኩ፡፡…ይህ ከትላንት ወዲያ ቅዳሜ ዲሰምበር 21/2013 ነው፡፡ ትላንት ምሳ አሰርቼ የምችለውን ያል ልብስ ገዝቼ ለማዳረስ ሞከርኩኝ፡፡ በቪዲዮው ላይ የምታዩትም ይህን የማዳረስ ሰራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ ከስውዲን፣ ጽዮን ሀብተሚካኤል፣ ንግስት ፍሬው ሰላም ብሩክ፣ ሰለሞን መንግስቱ ከዋሽንግተን፣ ዮሀንስ ዘርፉ ከሀገረ እንግሊዝ፣ ሰላም ብሩክ ከሳዑዲያ እና ቲጂ ላቭ ሀበሻ በሚል የምትጠቀመው እህቴ ከኩዌት የየበኩላቸውን አስተዋጽዖ አበረከቱ፡፡ ለሁሉም በወገኖቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እነዚህ ሰወገኖቼ ከ50 ጀምሮ ሁሉም አቅማቸው እስከቻለው በላኩልንኝ ዛሬ ዲሰምበር 23 ድረስ አልብሰናል አብልተናል፡፡ ነገን ማን ያውቃል ነገ ራሱ ያውቃል ….
No comments:
Post a Comment