በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል !
December 23, 2013በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !
ከ9 ሚልዮን በላይ የተለያዩ የውጭ፡ሃገር ዜጎች በጥገኝ ነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረ እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ ሰፈር ሃገራቸው ለመግባት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን እና በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መሃከል በተነሳ ግጭት አያሌ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሷች ተደፍረዋል እህቶቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ለመከላከል ጩሀታቸውን ያሰሙ ንጽሃን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ በሳንጃ እና በጓራዴ ተገድለዋል ፡፤
ይህንንም ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻች ከአሰቃቂው ጥቃት እርሳቸውን ለመታደግ ከዳር እስከዳር «ሆ »ብለው አደባባይ በመውጣት የሳውዲ አረቢያ አውራጎዳናዎችን በማጨናነቅ የአለምን መገናኛ ብዙን ሽፋን በማጝት በሳውዲ አረቢያ በጠራራ ፀሃይ እና በሌሊት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነበረው ጭፍጨፋ ስቃይ እና በደል በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ወገኖቻቸውን ዘንድ ቁጣን በመቀስቀስ በሳውዲ መንግስት ላይ ባደረጉት ተጸዕኖ በማን አለብኝነት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነረውን ኢሰባዊ ድርጊት ለግዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አስችሏል።
የኢትዮጵያኑ አለማቀፍ ቁጣ ያስደነገጠው የሳውዲ አረቢያን መንግስት በሚልዮን ለሚቆጠሩ የውጭ፡ሃገር ያወጣው ህግ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ እንዲያትኩር አስገድዶታል። ይህ በዚህ እንዳለ እስካሁን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውያን ስደተኞች የስውዲ አረቢያን ምድር በሰላም ለቀው ለሃገራቸው እንደብቁ የሚናገሩ ምንጮች አሁንም 80 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ጅዳ ጣይፈ መካ መዲና ከተሞች ውስጥ መሸገዋል ተብሎ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እይተሰጠ ያለው መግለጫ ቅንነት የጎደለው መሆኑንን ይገልጻሉ። በሃጂ እና ኡምራ አሊያም በባህር ወደ ሳውዲ ምድር ድንበር አቅርጠው ገብተውል ተብለው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የማይዘረዘርው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንላ የመንግስት ሹማምቶች መግለጫ ህገወጥ የተባሉት ወገኖች በግዜ እጃቸውን ሰጠተው ወደ ሃገር ካልተመልሱ በሪያድ መንፉሃ የተከስተው አይነት አልቂት እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል።
ይህ በቆንስል ዘነበ ከበደ የሚመራው ጽ/ቤት ሰሞኑንን እያሰማን ያለው ጩህት ወገናዊነት የጎደለው እና ሳውዲያኖቹ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ በማነጣጠር መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ጭምር ከሳውዲ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት የተያዘ እቅድ አንዱ አካል መሆኑንን የሚናገሩ የጅዳ ነዋሪዎች የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች በሳውዲ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ህልውናቸው አስተማማኝ ባልሆነበት አጋጣሚ እንደዚህ አይነት መግለጫ ማውጣት ሃላፊነት የጎደለው መሆኑንን ይናገራሉ። እንዚህ ወገኖች የጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት እንደዚህ አይነት አስገራሚ መረጃ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ በራሪ ወረቅቶች ቅስቀሳ ማካሄዱ ትላንት ሪያድ ከተማ መንፉሃ ውስጥ፡ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቀዋል የሚል የተሳስተ መለዕክት በማስተላለፍ ወገኖቻቸውን ካስፈጁት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ከፈጸሙት ስህተት የማይለይ መሆኑንን ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል ሰሞኑንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በየጥጋጥጉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶች በመበትን እያሰማ ያለው የተለመደ የአዞ እንባ « ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ » መሆኑንን የሚገልጹ የአካባቢው ነዋሪዎች የምህረቱን አዋጅ ተከትሎ ጉዳዮቻቸውን እስካሁን ማስፈጸም ተስኗቸው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለመኖር የሚያስችሏቸውን ማመዘኛ ያላሞሉ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየቀረቡ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የሚለው መለዕክት ለኢትዮጵያውያኑ ታስቦ ሳይሆን ዲፕሎማቱ የተለመደውን ድብቅ አጀንዳቸውን በቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ ለማስፈጸም እንደሆነ ይናገራሉ።
በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለደረስኝ፡በወገኖቻችን ሽፋን በመቶሺ የሚቆጠሩ ሪያሎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ከተጠቀሱት ወገኖች ኪስ ለተለያዩ ገዳዮች ማስፈጸሚ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ እቀድ እንዳላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር ቴድሮስ አድሃኖም በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አስቃቂ ግድያ ግፍ እና በደል ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የገቡትን ቃል ከፖለቲካ ግበአትነት እንደማያልፍ የሚናገሩ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ያሳረፈው ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ተጸኖ ባለመኖሩ ሳውዲያኑ ለኢትዮጵያውያኑ ያላቸው ጥላቻ አገርሽቶ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሪስፖንሰሮቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዳቻቸው በመሰረዙ አያሌ ወገኖች ለህገወጥነት እይተዳረጉ መሆናቸው ይነገራል።
No comments:
Post a Comment