በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስና ተከሰው ጉዳያቸው እየተጣራ ከቆዩ የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ። ኩማ ደመቅሳና አለማዮህ ታፈሰ ክስ ህዳር 30/ 2006 አ/ም ያየው የወረዳው ፍርድ ቤት። ተከሳሽ ለሆነው አለማዮህ ታፈሰ ለ10 አመታት ፅኑ እስራት ፍርድ ሰጥቶ። ለኩማ ደመቅሳ በሌላ ቀን ቀጠሮ እንዲታይ በወሰነበት ግዜ። የፍርድ ውሳኔ የተሰጠው አለማዮህ የይግባኝ ጥያቄ በማቅረቡ። የወረዳው ፍርድ ቤት የወሰነውን በድጋሚ ያየው ምንም ነፃነት የሌለው የዞኑ ፍርድ ቤት። በላይኞቹ የስርአቱ ባለስልጣናት ውስጣዊ ትእዛዝና ተንኮል መሰረት። ወንጀሉ ኩማን እንዳይነካው በማለት ለተከሳሹ ነፃ ብሎ እንደለቀቀው ለማወቅ ተችለዋል፣
ሁለቱም ተከሳሾች ተከፋፍለው በልቶውታል ተብሎው የተከሰሱበት 70 ሚሊዮን የሚገመት ብር። ለተለያዩ የከተማው መሰረተ ልማቶች እንዲውል በማለት ከህዝብና ከሃገር ሃብት የተመደበው ባጀት። ይዘውት ያሉትን ስልጣን ተጠቅመው ሥራ ላይ እንደዋለ በማስመሰልና ወጪ በማድረግ። ለግል ጥቅማቸው እናዳዋሉት የሚያረጋግጥ እውነተኛ መረጃ እንዳለ ከከተማው የተገኘው መረጃ ኣረጋግጠዋል:: ይህ በእንዲህ እያለ ኩማ ደመቅሳ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል። ህጋዊ ውሳኔ ለመስጠት እየተቃረበ በነበረበት ግዜ። ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ተነስቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማካሪነት እንዲሰራ ስልጣን ከተሰጠው በኋላ። ክሴታው ውሳኔ ሳያገኝ እስካሁን መስተጓጎሉና። ይኸውም ስርአቱ ሆን ብሎ በሙሱና ለተጨማለቁ ባለ ስልጣናት ተጨማሪ ስልጣን እየሰጠ ወደ ላይ እንዲወጡ ማደረጉ። የስልጣኑ የተዛባና ግለኝነት የተጠናወተው አካሄድ እንደሆነ። በውስጣቸው ፀሃፊ ሆና ለረጅም ግዜ ያገለገለች ወይዘሮ ህድረማርያም የተባለች ዜጋ። ቀደም ሲል ስርአቱ እየተጠቀመበት ለነበረ ውስጣዊ አስራር መሰረት አድርጋ እንደተናገረች ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል::
Source : Debirihan
No comments:
Post a Comment