Tuesday, December 31, 2013

በ”ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ”ና በሁለት ተጨማሪ መጽሀፎች ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት

December 31, 2013
ፋሲል የኔዓለም
በፖለቲካው ዓለም ጉልህ ስፍራ ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አዲስ መጽሃፍ ያነበብኩት ዘግይቼ ነው ፤ ለመዘግየቴ ሶስት መሰራታዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፣ አንዱና ዋናው ዶ/ሩ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ስላቀረቡ በመጽሀፉ ውስጥ እምብዛም አዲስ ነገር ያቀርባሉ የሚል እምነት ስላልነበረኝ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ዶ/ሩ ራሳቸው በከፊል የጠቀሱት ነው፣ “ በአገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር አባል መሆኑን ሲመለከት፣ ከቅንጦትም ባሻገር በተወሰነ ደረጃ “ የስራ ፈትነት” ወይንም የበለጠ ጠርጣራ ( cynic) ለሆነ ሰው “ በተግባር ስራ ለመስራት ካለመቻል “ የመጣ፤ ተግባራዊ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ሊመስል ይችላል” የሚለው ነው። ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ፣ ፋሽን በሚመስል መልኩ በአገር ቤት የሚኖሩ ፖለቲከኞች በተከታታይ መጽሃፎችን በማሳተማቸው ለእነሱ ቅድሚያ ለመስጠት በመፈለግ ነው።Ethiopian books review
ዶ/ር ብርሃኑን ያነበብኩት ሁለቱ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች -ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ” እንዲሁም ኢ/ር ሃይሉ ሻውል “ ሕይወቴ እና የፖለቲካ እርምጃዬ” በሚሉ ርዕሶች ያሳተሙዋቸውን መጽሃፎች ካነበብኩ በሁዋላ በመሆኑ፣ በሶስቱም ስራዎች ላይ መጠነኛ ንጽጽር ለማድረግ አስችሎኛል።
ዶ/ር መረራ ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ ያለውን የአገራችንን ፖለቲካ ግሩም በሆነ መንገድ አቅርበዋል፤ መጽሃፉ ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች የተካተቱበት በመሆኑ ፣ በቋንቋና በዓርትዖት በኩል የሚታይበትን ጉልህ ችግር አይተን እንዳላየን እንድናልፈው ያስገድደናል። መጽሀፉ በጥሩ ዓርታዒ እንደገና ቢታረምና ቢታተም “ የተዋጣላቸው” ከሚባሉት የአገራችን መጽሀፎች ተርታ የመመደቡ እድል ከፍተኛ ነው። ዶ/ር መረራ የአገራችንን ህልውና እየተፈታተነ የመጣውን፣ በ1960ዎቹ ተዘርቶ በእነ አቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ተኮትኮቶ ያደገውን የብሄር ፖለቲካ መነሻ ፣ ያመጣውን ግሳንግስ እና የግሳንግሱን ማራገፊያ መፍትሄ አስቀምጠዋል። መፍትሄ ብለው ያስቀመጡትም በመጽሀፉ የመጨረሻ ገጽ እንደሚከተለው ሰፍሯል፣ “ …ለታሪክም ለህዝብም አስቀምጬ (ማለፍ) የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ ፣ አብዛኛው የትግራይ ሊሂቃን “ ስልጣን ወይም ሞት” ብሎ ስልጣን ላይ የሙጥኝ እስካለ ድረስ ፣ አብዛኛው የአማራ ሊህቃን በአጼዎች ዘመን የነበረውን የበላይነትን መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ የኦሮሞ ሊህቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠና የምትወጣ አይመስለኝም። በሌላ ቋንቋ ለነዚህ መሰረታዊ በሽታዎቻችን መድሃኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈጽሞ የምታገኝ አይመስለኝም።” ( ገጽ 264)። ምንም እንኳ “አብዛኛው” የሚለው ቃል አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችል ቢሰማኝም ፣ ዶ/ሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በትኩረት ሊታይ እንደሚገባው ሳላስታውስ አላልፍም፤ በተለይ” እነዚህ የሶስቱ ብሄሮች ሊህቃን ህልማቸውን እንዲተው ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሚለው ጥያቄ ለእኔ ቁልፍ ይመስለኛል። ዶ/ር መረራ በዚህ ዙሪያ የተብራራ መልስ ቢሰጡ ኖሮ መጽሃፋቸውን የበለጠ ሙሉ ማደረግ ይችሉ ነበር እላለሁ።
የኢንጂነር ሃይሉ መጽሀፍ የአገራችንን የፖለቲካ ችግር ከግለሰቦች ባህሪ ጋይ ያያዘው በመሆኑ ብዙም ክብደት የሚሰጠው ሆኖ አላገኘሁትም፤ ንድፈሃሳባዊ ትንተናዎች ይጎድሉታል፣ የተዓማኒነት ችግሮችም አሉበት( በተለይ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ስለነበረው የሽምግልና ሂደትና ከዚያ በሁዋላ ስለተፈጠሩት ኩነቶች) ፤ ለተተኪው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት ስለመኖሩም በእጅጉ እጠራጠራለሁ፤ በእርግጥ ኢ/ር ሃይሉ ብዙ ውጣውረዶችን አልፈው እስካሁን በህይወት ለመቆየት መቻላቸው እድለኛ ሰው እንደሆኑ በመጽሃፋ ለማየት ችለናል፣ አገራቸውን የሚወዱ ሰው መሆናቸውንም አስገንዝቦናል። ኢ/ር ሃይሉ የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን መንገድ በመከተል መጽሀፉን በሌላ ሰው በማስጻፋቸው ስለጸሃፊነት ችሎታቸው አስተያየት ለመስጠት አያስችልም ።
የዶ/ር ብርሀኑ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” የሚለው ርዕስ ዘጊ ወይም ለማንበብ የማይጋብዝ ነው፤ በትምህርቱ አለም የዘለቁና የጥናትና ምርምር ወረቀቶችን ለማንበብ ፍላጎት ያላቸው ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር፣ እንደ እኔ አይነቱ ተራ አንባቢ በርዕሱ ማልሎ መጽሀፉን ለማንበብ ስለመነሳሳቱ እጠራጠራለሁ። መጽሀፉ ውጫዊ ገጽታው ባያማልልም ውስጣዊ ይዘቱ ግን ድንቅ ነው። እንደምንም የጀመርኩትን መጽሀፍ እየተጨነቁና እየፈራሁ፣ እያዘንኩና ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ፣ እግረ-መንገዴንም የጸፊውን እይታ፣ የትንታኔ እና የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታ እያደነቁኩ ጨርሸዋለሁ። መጽሀፉን እንደጨረስኩ የተናደድኩበት ነገር ቢኖር ጻሃፊው የኢትዮጵያን ችግሮች እንዲያ አድርገው ካቀረቡ በሁዋላ መፍትሄውን በይደር በመተዋቸው ነው።
ከዚህ ቀደም የአገራችንን ሁለተናዊ ችግሮች ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተፈጥሮና የህዝብ ብዛትን በአንድነት አጣምሮ፣ በአገራችን ህልውና ላይ የደቀኑትን ፈተናዎች ቅልብጭ አድርጎ ያሳየ ከገብረህይወት ባይከዳኝ “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” በሁዋላ የተጻፈ መጽሀፍ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ይህን ስል ሌሎች ድንቅ የፖለቲካ መጽሃፎች አልተጻፉም እያልኩ አይደለም፤ የዶ/ር ብርሃኑን መጽሀፍ ለየት የሚያደርገው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮችን ለይተው በማውጣት እርስበርስ ያላቸውን ትስስር ከግሩም ትንተና ጋር ሁሉም ሊረዳውና ሊጠቀምበት በሚችለው መንገድ ማቅረባቸው ነው ። (የምጣኔ ሀብት ትምህርት ( economics) የማይገባው ሰው እንኳ ቢሆን፣ መጽሀፉን አንብቦ ስለአገራችን ኢኮኖሚ ለመረዳት አይሳነውም።) መጽሃፉ የባራክ ኦባማን The Audacity of Hope እንዳስታወሰኝ ብገልጽ ያጋነንኩ አይመስለኝም፣ አጋነኸዋል የምትሉኝ ካላችሁም ” አንብቡትና ሞግቱኝ።
የዚህ መጽሀፍ ትልቁ መልእክት፣ ለእኔ እንደገባኝ፣ “የአገራችን ችግር ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገንባት ይፈታል” የሚለው አስተሳሰብ እንደሚታሰበው ቀላል አለመሆኑንና ከአሁኑ መፍትሄ ካልተበጀለት በሁዋላ ላይ ይዞት የሚመጣው ችግር ቀላል አለመሆኑን ማሳየት ነው ። የብሄር ፖለቲካው በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ፣ በአገራችን ልማትን ለማምጣት የሚገጥሙ ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ችግሮች፣ ከአካባቢ ውድመትና ከህዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ በመጽሀፉ በዝርዝር ቀርቧል። በአሁኑ ጊዜ በአገራችን እየታየ ያለውን የገቢ አለመመጣጠንም 1500 ብር የሚያወጣውን የአንድ መለኪያ ውስኪ ግብዣ በምሳሌነት በማንሳት በደቡብ አፍሪካ እንደታየው በአገራችንም ለወደፊቱ ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ጣጣ ጸሀፊው በደንብ አሳይተውናል።
መጽሀፉ የውጩ ፖለቲካ በአገራችን ፖለቲካ ላይ የሚያሳርፈውን ተጽዕኖ እንዲሁም የአለማቀፉ የንግድ ስርዓት በኢትዮጵያ እድገት ላይ ያለውን ተጽእኖ ቢያካትት ኖሮ የበለጠ ድንቅ ይሆን እንደነበር አስባለሁ ። ከዚያ በተረፈ ግን መፍትሄዎቹ በሌላ ክፍል እንደሚቀርቡ መገለጹ በመጽሀፉ ላይ በቂ ክርክር እንዳይነሳ ያደረገው ይመስለኛል። በመጽሀፉ በቀረቡት ችግሮች እና ትንተናዎች ላይ ተቃውሞ የሚኖረው ሰው ይኖራል ብየ አላስብም፣ ተቃውሞ የሚነሳው ችግሮችን ለመፍታት በሚቀርቡት የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ እንደሚሆን በመገመት ቀጣዩ መጽሃፍ አወያይ ( አካራካሪ) ይሆናል እላለሁ።
ስለአገራቸው እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ሁሉ መጽሀፉን እንዲያነቡት እመክራለሁ ( የዶ/ር መረራንም ጨምሮ)። በተለይ በሰላማዊው የትግል ሜዳ ለመፋለም የሚያስቡ ጀማሪም ሆኑ ነባር ፖለቲከኞች የብርሀኑን መጽሀፍ በማንበብና በምርጫ ክርክር ወቅት ይዞ በመቅረብ ( የመፍትሄው መጽሀፍ ቶሎ እንደሚደረስ በመገመት) ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፤ ስልጣኑን ይረከባሉ ብዬ ባላስብም።

በተቀነባበረ የመብራት ሀይል ሙስና ኢትዮጵያ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ተደረገ

በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት ዶ/ር ደብረ ጸዮን ገብረሚካኤል ስለአቶ ደበበ ምህረት ከሃላፊነት መነሳት ” እሱም የሚመሰገነውን ያክል ጉድለትም እንደነበረበት ይረዳል። ከሃላፊነቱ ሲነሳም አልደነገጠም።” በማለት መናገራቸው ይታወቃል። ምንም እንኳ ዶ/ር ደብረጺዮን አቶ ደበበ በብቃት ችግር እንደተነሱ አድርገው ለመገናኛ ብዙሀን ቢገልጹም፣ አቶ ምህረት ደበበ ግን በህወሃት ባለስልጣናት ስውር እጅ ሲቀነባበር የነበረውንና ኢትዮጵያን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ያደረገውን ከፍተኛ ሙስና ሲቃወሙ እንደነበር ለጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበው እና ለኢሳት የደረሰው የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ያስረዳል።
በ1999 እና በ2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ካወጣቸው አለም አቀፍ ጨረታዎች ጋር ተያይዞ በጨረታዎቹ ሂደት ላይ ግልጽነትና ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መከሰቱንና ይህም የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ በማድረግ የምርመራ ውጤቱን በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትት መለስ ዜናዊ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮግራምን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛሉ በማለት የሥርጭት (Distribution) ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ሁለት ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን ለማውጣት ዝግጅት ጀመረ። ጨረታዎቹ በኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎችና በጨረታ ገምጋሚ የኮሚቴ አባላት ይሁንታ አግኝተው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በሁዋላ የመጀመሪያው ጨረታ በ1999 ዓ.ም፣ ሁለተኛው ጨረታ ደግሞ በ2000 ዓ.ም እንዲወጡ ተደረገ፡፡የጨረታዎቹን መውጣት ተከትሎም መረጃው የደረሳቸው ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተለያየ ጊዜ ተደረጉትን ጨረታዎችም “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” የተሰኘ የሕንድ ኩባንያ አሸናፊ መሆኑ በወቅቱ በይፋ ተነገረ።
ኩባንያው የጨረታው አሸናፊ ተብሎ ይለይ እንጅ ባቀረበው ሰነድ ላይ የገለጸው የትራንስፎርመር ዓይነት ኮርፖሬሽኑ በጨረታው ሰነድ ላይ ሊገዛው ካሰበው ዓይነት ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ሳይገኝ ቀረ፡፡ ይህ አልተጠበቀ ክስተት ደግሞ በግዥ ሂደቱ ውስጥ ገና ከጅምሩ የሙስና ወንጀል ድርጊት የተጠነሰሰ መሆኑን አመላከተ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ያስቀመጠው የትራንስፎርመር ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚል ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ ባቀረበው የውል ማቅረብያ ሰነድ (ኦፈር) ላይ “ትራንስፎርመር ዊዝ ኮንሰርቫቶር ዩኒት” የተባለ ነው።
“ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” ያቀረባቸው ሰነዶች ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ያወጣውን መስፈረት እንደማያሟሉ ሲታወቅ ፣ የነበረው የመፍትሄ አማራጭ ጨረታዎቹን አሸንፏል ተብሎ የተለየው ኩባንያ ያቀረበው ትራንስፎርመር በኮርፖሬሽኑ የጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው መስፈርት (ሰፔስፊኬሽን) አያሟላም በሚል በአሰራሩ መሰረት በቴክኒክ ግምገማ ውድቅ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ላይ አቶ ምሀረት ደበበ ተቃውሞ ያሰማሉ፤ ይሁን እንጅ የኮሚቴ አባላቱ ተቃውሞውን ወደ ጎን በመተውና አዲስ ቃለ ጉበኤ በመያዝ ኩባንያው ትክክለኛ የትራንስፎርመ ዓይነት ይዘው ለውድድር ከቀረቡ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር እንዲወዳደር በማድረግ በህገወጥ መንገድ ቀጣዩን የ ፋይናንስ ግምገማ ሥርዓት እንዲያልፍ አድረጉ፡፡ በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑን ወክለው በጨረታው የተሳተፉ አካላትም ሆነ ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ኩባንያ ባለቤት በኪራይ ሰብሳቢነት ስሌት ያልተገባ ጥቅም ለመቀራመት እየተንደረደሩ መሆኑን የሚያሳይ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበላቸው።
የጨረታው ሂደት ቀጥሎ ኮርፖሬሽኑ እና የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ በሚቀርቡ የትራንስፎርመሮች መጠንና በገንዘብ ጉዳይ ላይ ውል የሚዋዋሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ። ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቸውን ሁለቱን ጨረታዎች የተመለከተ የውል ሰነድ ተዘጋጅቶም በሁለቱም ወገኖች ተፈረመ። የጨረታዎቹ አሸናፊ ነው የተባለው “ጉድላክ
እስቲል ቲዩብስ ሊምትድ” ኩባንያም ትራንስፎርመሮቹን በሰፕላየርስ ክሬዲት (supplier credit) እንደሚያቀርብ ተስማማ፡፡ በውሉ መሰረት ኩባንያው በአንደኛው ጨረታ ብዛታቸው 1950 የሆኑ የስርጭት ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ8 411,946 የአሜሪካ ዶላር፤ በሌላኛው ጨረታ ደግሞ ብዛታቸው 3520 የሆኑ ትራንሰስፎርመሮችን ከነወለዱ በ17,695,686 የአሜሪካ ዶላር፤ በድምሩ ብዛታቸው 5470 የሆኑ ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ 26 107 632 የአሜርካ ዶላር ለማቅረብ ስምምነቱ ተፈረመ።፡
የሁለቱ ጨረታዎች የመጀመሪያ ውሎች በዚህ መልክ በኮርፖሬሽኑና በጨረታው አሸናፊ ኩባንያ መካከል ይፈረሙ እንጅ በኩባንያው በኩል ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው መዘግየት የሚጠበቁ ውጤቶች ሊታዩ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ኩባንያው ገንዘቡን በራሱ ማቅረብ እንዳማይችልም ግልጽ እየሆነ መጣ፡፡ ይህን የተረዱ የጨረታው ኮሚቴ አባላትና የኩባንያው ባለቤት መፍትሄ ይሆናል ብለው ያሰቡትን አማራጭ ማፈላለግ ጀመሩ፡፡ አውጥተው ካወረዱ በኋላም ሌላ አዲስ ውል ቢኖር የፋይናንስ ችግሩን ይቀርፋል በሚል ሀሳብ ተስማሙ፡፡ በአዲሱ ሀሳብ ላይ ተቃውሞአቸውን የገለጹት አቶ ምህረት ደበበ እራሳቸውን ለማግለል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቀጥታ በውሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በጠ/ሚሩ ጽ/ቤት በኩል ትዕዛዝ ደረሳቸው። ኩባንያው መጀመሪያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈራረመው ውል በአዲሱ ውል እንዲተካም ተደረገ፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የተፈረመው የዚህ የአዲሱ ውል ዋና ፍሬ ሀሳብም የመጀመሪያው ውል ተቀይሮ ግዥውን ፋይናንስ
የሚያደርግ ሌላ ሶስተኛ ወገን በውሉ ውስጥ እንዲገባ ማድረግ የሚል ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ቢዝነስ እንደሚሰራ የሚነገርለት “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር” ግዥውን በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍ ተባባሪ (ፋይናንሲንግ አሶሺዬት)፣ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ደግሞ የትራንስፎርመሮቹ ገዢ በመሆን የሶስትዮሽ ውል እንደገና እንዲፈረም ተደረገ፡፡
ይሁን እንጅ ሌላ አዲስ ውል በሕንድ ኩባንያዎች መካከል መፈረሙም ታወቀ፡፡ ዉሉ በ“ጉድላክ እስቲል
ቲዩብስ”፤በ“ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” እና ሌላ በሕንድ አገር ከሚገኘ የትራንስፎርመር አምራች የሆነ “ናሽናል ኤሌክትሪክ ኢክዩፕመንት ኮርፖሬሽን” በተሰኘው ኩባንያ መካከል የተፈረመ የሦስትዮሽ ውል ነበር፡፡ ኩባንያዎቹ ይህን ውል ሲፈራረሙ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም እና የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚዎች የነበሩ ግለሰቦች በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ቢሆንም ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ መሆኑ ግን በምርመራው ተደርሶበታል፡፡ ከምርመራው ውጤት ለመረዳት እንደተቻለው ይህ ሁሉ አካሄድና ቀና ደፋ ደግሞ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለውን ኩባንያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሦስትዮሽ ከተፈራረመው ውል ማውጣት ነውና ይህም ተሳካለቸው፡፡ ስለሆነም “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” የተባለው ኩባንያ ከፋይናንሲንግ አሶሺዬት ወደ አቅራቢነት የውል ተቀባይ ወገን ተቀየረ፡፡
የኮርፖሽኑ የቀድሞው የስራ ሃላፊ አቶ ምህረት ደበበ ከኮርፖሬሸኑ እውቅና ውጭ የተደረገው ውል ያለአግባብ መሆኑን በመገንዘብ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለ ኩባንያ ከውሉ መውጣት እንደማይገባውና ቀደም ሲል ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈረመው የሦስትዮሽ ውሉ ጽንቶ መቆየት አለበት በሚል ማሳሰቢያም ጭምር ለመስጠት ጥረት አድርጓል፡፡ ይሁን እንጅ በአቶ ምህረት ደበበ የተሰጠውን ማሳሰቢያ የሚሰማ ጆሮ አልተገኘም፡፡ ይልቁንም ምርመራው እንዳረጋገጠው
ተጠርጣሪ የኮርፖሬሽ የሥራ ኃላፊዎች “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ትራንስፎርመሮቹን የማቅረብ የሕግ መሰረትና አቅሙ
ሳይገመገም እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ይሁንታ ሳያገኝ በሚያዚያ ወር ም ለ“ሪዘርቭ ባንክ ኦፍ ኢንዲያ” በጻፉት ደብዳቤ
ኩባንያዎቹ ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ ለተፈራረሙት ውል ማረጋገጫ በመስጠት ኩባንያው ሕግን ባልተከተለ መንገድ የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ትራንስፎርመሮቹን የሚያቀርብ ኩባንያ ለመለየት የተጀመረው ድራማ በዚህ መልኩ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ የሚሆነው
ደግሞ የግዥ አፈጻጸም ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡ በዚህ የግዥ አፈጻጸም ተግባር ውስጥ በኮርፖሬሽኑ የሲስተምና የደንበኞች አገልግሎት ድጋፍ ክፍል ኃላፊ እና የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም ኢንጂነሪነግ ፕሮሰስ የስራ
ሂደት ተወካይ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊ በዋናነት ተሳታፊዎች ናቸው።
በአሁኑ ወቅት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የትራንስፎርመሮቹን ግዥ አፈጻጸም በተመለከተ “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ባለቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ለኮርፖሬሽኑ ያቀረበውን የአፈፃፀም ዋስትና ተከትሎ ዋስትናው ውሉ በሚያዘው ፎርማት (ቅፅ) መሰረት ያልተዘጋጀ መሆኑን እያወቁ ሕጉ ከሚያዘው አሰራር ውጭ ኩባንያው እንዲያልፍ ረድተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሁለቱም ጨረታዎች በቀረቡ የአፈፃፀም ዋስትናዎች ላይ “… በግዥው አፈጻጸም ውስጥ የባንክ ዋስትና ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በዋስትና ሰጪው ባንክ የገንዘብ መጠየቂያ ደብዳቤ በሕንድ መንግስት ባንክ የሚሰጥ ሆኖ ፓሪስ በሚገኘው የናቲክሲስ የማድሪድ ቅርንጫፍ ባንክ ተቀባይነት ካገኘበት ቀን በኋላ ብቻ ነው” የሚል ይዘት ያለው ቅድመ ሁኔታ የሰፈረ መሆኑን እያወቁ እንዲሁም የኩባንያው ባለቤት ግዴታውን በውሉ መሰረት ሳይፈፅም ቢቀር ኮርፖሬሽኑ ወዲያውኑ የአፈፃፀም ዋስትናውን መውረስ የሚያስችለው መሆኑን እየተረዱ ይህን ሁኔታ ለሚመለከተው የኮርፖሬሽኑ አካል ሳያሳውቁ እንደ ዋዛ አልፈውታል፡፡
“ኮብራ” የተባለው ኩባንያ በበኩሉ ትራንስፎርመሮቹን ለማቅረብ “ጉድላክ” ከተባለው ኩባንያ ላይ የተረከበውን ኃላፊነት
ሳይወጣ ጊዜ ነጎደ፡፡ ኮርፖሬሽኑም ትራንስፎርመሮቹ በወቅቱ መቅረብ እንዳልቻሉና ኩባንያው በውሉ መሰረት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳልሆነ መገንዘብ ችሏል፡፡ መገንዘብ ብቻም ሳይሆን ኩባንያው በዉሉ መሰረት ግዴታውን ሳይፈጽም ቢቀር የአፈፃፀም ዋስትናውን ለመውረስ የሚያስችለውን መብትም ለመጠቀም ሲባል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ
አቅርቧል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ያቀረበው የአፈፃፀም ዋስትና ውርስ ጥያቄ በባንኩ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡ ለዚህ በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአፈጻጸም ዋስትናው በቅድመ ሁኔታ የተገደበ መሆኑ ነው፡፡
በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑ የግዥ አፈጻጸም ዋስትናውን መውረስ የማይችልበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ለኪሳራ ከሚዳረግ ይልቅ የሚቀርብለትን የትራንስርፎርመር ዓይነት ለመቀበል አጣብቅኝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በእርግጥ ኮርፖሬሽኑ
ሊገዛ ያቀዳው የትራንስፎርመር ዓይነት ቀርቦለት፣ የአፈጻጸም ዋስትናውን መውረሱ ቀርቶ ትራንስፎርመሩን በተገኘ ጊዜ
ለመቀበል ቢችል እንኳ ባልከፋ ነበር፡፡ አሁን ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ያጣ እንደሚባለው ሆኗል፡፡ ወይ ገንዘቡን አሊያም
በጨረታ ሰነዱ የገለጸውን የትራንስፎርመሮች ዓይነት ለማግኘት አልቻለም። የምርመራው ውጤት እንዳመለከተው በድርጊቱ ውስጥ ተሳታፊዎች የነበሩ በቁጥር ሰባት የሚደርሱ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባልትን ጨምሮ የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያዎች ባለቤቶች በአንጻሩ የማይገባቸውን ጥቅም ለመቀራመት የወጠኑትን ውጥን ከዳር ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
እነዚህ በሁለቱም ጎራ በጨረታው ላይ የተካፈሉ አካላት የጨረታውን ሂደት ፍትሃዊነት በማሳጣትና ግባቸውን ያልተገባ ጥቅም መቀራመት አደርገው በመንቀሳቀስ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ውሎች ውስጥ ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ካሰባቸው የትራንስፎርመር ዓይነቶች ውጭ እንዲቀርብ ሁኔታዎችን የማድበስበስ ተግባራትን መፈፀም ቀጠሉ፤ ቀደም ሲል በሁለቱም የጨረታ ሰነዶች ላይ የሰፈረውና ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ያሰበው የትራንስፎርመሮች ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚለው ሲሆን ከዚህ መስፈርት ውጭ ከአቅራቢዎች ጎራ ሌላ ዓይነት መስፈርት ከመቅረቡም በተጨማሪ ኮርፖሬሽኑ አዲስ፣ ያላገለገሉ እና የቅርብ ስሪት የሆኑ የትራንስፎርመሮች ዓይነት እንዲቀርብለት ያስቀመጠውን መስፈርት ወይም ስፔስፊኬሽን ኩባንያዎቹ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ሳይካተት ታልፏል፡፡
እነዚህ ተግባራት ተደማምረው ሕገ-ወጥ የግዥ አሰራር የበላይነትን ይዞ የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የኩባንያዎቹ
ባለቤቶች የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ማሳለጫ መንገድ እንደሆናቸው የምርመራው ውጤት ያስረዳል፡፡ የኩባንያዎቹ ባለቤቶችም ከጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባላትና በጨረታው ተሳታፊ ከነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ያመቻቹትን ይህን ሕገ-ወጥ አካሄድ በመጠቀም ኮርፖሬሽኑ የማይፈልጋቸው የትራንስፎርመሮች ዓይነት ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማደረጋቸውንም ምርመራው ያሳየናል፡፡
በጨረታው ተሳታፊ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከትራንስፎርመሮቹ ጥራት ጋር በተያያዘ ጎልተው የታዩ ችግሮችን ለመሸፋፈን የተለያዩ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ትራንስፎርመሮቹ በሙያተኞች እንዲፈተሽ አድርገዋል፡፡ በውጤቱም የዛጉና የዘይት መንጠባጠብ የሚታይባቸው፣ የሲሊካ ጄል እና ከፍተኛ የመብረቅ መከላከያ የሌላቸው፣ የታፕ ቼንጀር ማስሪያ ብሎኖች የሌሏቸውና የተሰበሩ ትራንስፎርመሮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ትራንስፎርመሮቹ ኮርፖሬሽኑ ከሚፈልጋቸው ዓይነት ውጭ ከመሆናቸው በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው በተደረገው ምርመራ ግልጽ ሆኗል፡፡ ከዚህም በመነሳት በጨረታው ሂደት ውስጥ በዋናነት ተሳታፊ የነበሩ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ስራ አስፈፃሚ፣ የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚ እንዲሁም የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም የቴክኒክ ክፍል ቡድን መሪ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ለ“ጉድላክ” እና “ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ደብዳቤዎችን ፅፈው ነበር፡፡ ውስጥ ለኩባንያዎቹ የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ይዘት ትራንስፎርመሮቹ በውሉ መሰረት ያልቀረቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሲሆን በነዚህ ደብዳቤዎች መሰረት የሥራ ኃላፊዎቹ ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም ውግንና ያሳዩ ይመስላል፡፡
ይሁን እንጅ የምርመራ ውጤቱ እንደሚጠቁመው እነዚህ የሥራ ኃላፊዎች ለኮርፖሬሽኑ ያሳዩ የሚመስለው ውግንና ዘለቄታ አልነበረውም፡፡ ከ2001 ዓ.ም በኋላ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከኩባንያዎች ጋር በተጻጻፉት ደብዳቤዎች መሰረት ትራንስፎርመሮቹ እንዲቀየሩ ከማድረግ ይልቅ በኩባንያዎቹ የቀረበላቸውን የጥገና መርሃ ግብር ተቀብለውና
አፅድቀውት በመላክ ትራንስፎርመሮቹ ያለአግባብ እንዲጠገኑ አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የኢንጂነሪንግ ክፍል እና የአገር አቀፍ
ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የሳፕላይ ቼይን የሥራ ኃላፊዎች ትራንስፎርመሮቹ ብልሽት ያለባቸው ሆነው እያሉ
ሙሉ በሙሉ እንደተጠገኑና ስራ ላይ እንደዋሉ በመግለፅ፣ አንድ ጊዜ እንዲጠገኑ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንዲተኩ በሚል ያለ በቂ ሙያዊ ፍተሻ ተገቢ ያልሆነ የውሳኔ ሃሳብ በመስጠትና የውስጥ ማስታወሻዎችን በመጻጻፍ ትራንስፎርመሮቹ በአዲስ እንዳይተኩ በማድረግ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በግዥው ሂደት ውስጥ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘትና ለኩባንያዎቹ ባለቤቶች ለማስገኘት በማሰብ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ተካፋይነት በሚፈፀም ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በድርጊቱ ውስጥም በስልጣን ያለአግባብ መገልገል፣ የመንግስት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ድርጊቶች የተፈጸሙ መሆናቸው ታይቷል፡፡ በዚህ አግባብ በተፈጸሙ ብልሹ አሰራሮች ሳቢያ በአገር ጥቅም ላይ ከ26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱም ተጠቅሷል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሰባት የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአራት የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ላይ ተገቢውን ማስረጃዎች አሰባስቦ በሁለት የክስ መዝገቦችና በስድስት ክሶች በማጠናቀር ጉዳዩን ለመጀመሪያ ጊዜ ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቀርቧል፡፡ የአቶ ምህረት ደበበ የስልጣን ዝውውር የጀርባ ፍጥጫ ሌላው የግምገማ ታሪክ ይህን ሲመስል፣ በተፈጠረው አለመግባባት ስራውን በአግባቡ እንድመራው በወጣው ህግ እና ደንብ መመራት አልቻልኩም ሲሉ ያቀረቡት መልቀቂያ ጥያቄ በዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ተቀባይነት አግኝቶ ምንም በቂ ሃላፊነት ወደ ሌላው የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል።
አቶ ምህረት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ እና የሙስናውን ድራማ ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆኑት የህወሀት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ሳይውሉ፣ በመካከለና የአመራር ቦታ ላይ ያሉ የተወሰኑ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
በቅርቡ አንድ የህንድ ኩባንያ የኤልክትሪክ ኮርፖሬሽንን ማኔጅመንት ለመምራት ውል መዋዋሉ ይታወቃል።

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ታሰረበኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መታሰሩን የዘሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ። አርቲስቱ የታሰረው በካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እስር ቤት እንደሚቆይም ይጠበቃል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መታሰሩን የዘሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ። አርቲስቱ የታሰረው በካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እስር ቤት እንደሚቆይም ይጠበቃል፡፡
የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአርቲስቱን የክስ መዝገብ በመጥቀስ እንደዘገቡት ዳንኤል የታሰረበት ምክንያት አንዲት ባለትዳር ሴትን ከሌላ ወንድ ጋር ስትሳሳሚ ፎቶ አንስቼሻለሁ ይህንንም ፎቶ በፌስ ቡክ አለቀዋለሁ ብሎ በስልክና በአካል በማስፈራራቱ ነው፡፡ አርቲስቱ ከዚህችው ወ/ሮ ፊልም እሰራለሁ ብሎ 500 ሺ ብር እንደተቀበለና በማጭበርበር ክስ እንደቀረበበት በተለያዩ ሚዲያዎች በዘገቡ ይታወቃል፡፡( ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ቅዳሜ ለንባብ የበቃው ቁም ነገር መፅሄት ሁለቱንም ወገኖች ማነጋገሩ ይታወቃል) ሰለጉዳዩ ተከታትለን እናቀርባለን።
ዘ-ሐበሻ

Monday, December 30, 2013

በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) የተሰጠ መግለጫ

ታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. (December 30, 2013)የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሥራ ከመስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 9, 2009) ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ዕለታዊ የሱዳን ጋዜጣ ሱዳን ትሪቢውን (Sudan Tribune) በመስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. (September 18, 2009) መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ ያንገበገባቸው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩት ዜጎቻችንም ራሳቸውን በተለያዩ “ኮሚቴዎች” እና “ግብረ ሃይሎች” በማደራጀት ለጉዳዩ ክፈተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ፓርቲያችን (ሰማያዊ)፣ ለነዚህ ሀገር ወዳድ ዜጎች ያለውን ከፍተኛ አክብሮት ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሥውር የሥልጣን ማራዘሚያ ደባዎችን እየሸረበ እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ወያኔ ራሱ ያቋቋመው “የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ኮሚቴ” አባላት ራሳቸው በተለያዩ ቃለ-ምልልሶች እንዳጋለጡት፣ ወያኔ በአባቶቻችን ደም ተላቁጦ ለተቦካውና የበርካታ ሰማዕታትን ህይወት ላስከፈለው የኢትዮጵያ ድንበርና የግዛት ሉዓላዊነት ግዴለሽነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊ ግዛትና ድንበር “በጫካ ውሎችና ስምምነቶች” እያመካኘ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የሃገር ክህደትና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ለማስተባበል በመገንዘብ፣ የወያኔ-ኢህአዲግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ ላይ በመስከረም 2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አንድ የማደናገሪያ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከዚህም የማደናገሪያ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉትን ሦስት(3) አበይት ጉዳዮች መገንዘብ ይቻላል። እነርሱም፦
1ኛ. የኢትዮጵያና ሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ (Ethio-Sudan Political Committee) ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ አካል መኖሩንና የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) በፖለቲካው ኮሚቴ ሥር እንደሚሠራ አረጋግጧል፤ የዚህ የኮሚቴ መዋቀርና የአሰራር ሂደቱም ለረጅም ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ተደብቆ የቆየ እንደሆነና፣ ወያኔ-ኢህአዲግም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ክትትል መጋለጡን ሲያውቅ ተጨንቆ ያወጣው ምስጢር ነበር።
2ኛ. የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) ከጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 15, 2009) እስከ ግንቦት 2002 ዓ.ም.(May 2010) ድረስ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይስና ቅኝት እንደሚያደርግም ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ ሲጋለጥ ያወጣው ሌላው ምስጢር ሲሆን፣ (ሱዳን ትሪቢውን ያወጣውን ዜና የሚያጎለምስ) እና የሱዳን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበሩን ለማካለል የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስተጋባ ነው።
3ኛ. የድንበር ክለላው ከግንቦት 2002 ዓ.ም. ( May 2010) በኋላ እንደሚደረግና ከዚህም ጋር አያይዞ ወያኔ-ኢህአዲግ ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት አምነው የተቀበሉት የድንበር ክልል እንዳለ አስምስሎ ለማቅረብም ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ወያኔ-ኢህአዲግ አሁን የሚያካሂደው “የድንበር-ክለላ ሂደት” ዳግም ድንበርን የመከለል ተግባር ( re-demarcation ) እንደሆነ መግለጹ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ይህ ማደናገሪያና ተራ ልፈፋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማወናበድና ግዛቱን በጫካ ውሎችና ስምምነቶች አማካይነት አሳልፎ ከመስጠት የዘለለ ኢምንት እውነታ የለውም፡፡ ይሄንን በተመለከተም ያጠኑት ሊቃውንትንና በግዛቱ ላይ የሚኖሩትን ዜጎች ምስክርነት ሊያገኝ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡
የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት “ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የተቀበሉት የድንበር ክልል” የሚለው ሀተታ፤ ሜጀር (ሻለቃ) ጉዊን የተባለው የእንግሊዝ ጦር መኮንን በ1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) “አስምሬአለሁ” የሚለውን የወሰን ክልል ነው። ይሁንና አንድ በእንግሊዝ የቅኝ-ገዥነት አባዜ የሰከረ ሻለቃ ያሰመረውን መስመር መሠረት አድርጎ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉዓላዊነትን የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን “ለሱዳን ይገባታል” ብሎ መሟገቱ የፖለቲካ ቅጥፈት እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም፡፡ የሚከተሉትም ታሪካዊ ዳራዎች የወያኔን ሙግት ውድቅ ያደርጉታል፦
1ኛ.ሻለቃ ጉዊን መሬቱን አካልያለሁ ሲልና በወረቀት ሲያሰምር፤ በኢትዮጵያ በኩል አንድም ተወካይ ስለአልነበረ የጉዊን የድንበር ማካለል ተግባር ከቅኝ ገዢዎች ማንአለብኝነት ተለይቶ የማይታይና የውል አፈጻጸም ሥርዓት የማይከተል በመሆኑ የተነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡
2ኛ. የ1896 ዓ.ም.(እ.አ.አ.) የአድዋ ጦርነት ድል በቅኝ ገዥዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ መደናገጥ ምክንያት 1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) አካባቢ እንግሊዝና ጣሊያን በጋራ በመመሳጠር የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያን ድንበር ለመግፋት የፈፀሙት ሴራ ስለሆነ፣ የሻለቃ ጉዊን ተልዕኮም ከዚያ ሴራ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ስለሆነም ተቀባይነት የለውም፡፡
3ኛ. ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊትም ይሁን ከዚያ በኋላ፣ ይህ ሻለቃ ጉዊን ከለለው የሚባለው መሬት ምን ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይባስ ብሎም፣ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ግዛት አሁን ሱዳን ተብሎ ከሚጠራው ሃገር በጣም ወደ ውስጥ የገባ ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የግዛት ጥያቄ ሲነሳ የይገባኛል ታሪካዊ መሠረት ያላት ኢትዮጵያ መሆኗን ለማስተባበል አዳጋች ነው፡፡
4.አሁን የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት በመጋቢት 22/2006 ዓ.ም ገደማ March 30, 2014 ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መርሆው ያላደረገው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ግን አንዳችም መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያገኝ የተለመደ አፈናውን ገፍቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ በእልፍ-አዕላፍ ድንበር ጠባቂ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረውን ዳር ድንበር፣ ወያኔ በተለመደ “የደጃዝማቾች ፈረስ መጠጫና ጉግዝ መጫወቻ ነው” በሚል ንፍገት አሳልፎ ለሱዳን ሊሰጠው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰፊ ውሃ-ገብና ለም ሉዓላዊ መሬት፣ የታሪክ ማስረጃዎችንና የኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነት በማናናቅ ለባዕዳን ሊሠጥ አይችልም፡፡
ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎችና በዓለም-አቀፍ የአሠራር ደንብ መሠረት፤ ወያኔ-ኢህአዲግ ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የድንበር ክለላ ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። ከዚህም ባሻገር፤ ከዋናው ባለጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ይሁን የድንበር ክለላ ተግባር ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም።
ከዚህም ሌላ፣ ወያኔ-ኢህአዲግ የተወሰኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ቆርሶ በመስጠት ሥልጣኑን በጎረቤት አገር ሱዳን ለማስባረክ ብሎ የሚያደርገው ሽር-ጉድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም፡፡ ውጤቱም “ታግዬላቸዋለሁ የሚላቸውን ብሄሮችና ብሔረሰቦች” ከማዳከምና ብሎም ለማፈራረስ የተጠቀመበተ ዘዴ የቅኝ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ያሰመሩትን የድንበር መስመር በመቀበልና የቅኝ ገዢ ጠበብትን እንደ ምስክር በመጠቀም ነው። ይህም ተግባሩ፣ቀድሞውንም በቋፍ የነበረውን የወያኔ-ኢህአዲግን መንግሥት የፖለቲካ ቅቡልነት የሚያሳጣው መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ አልፎ-ተርፎም በዚህ ተግባሩም ዛሬም የቅጥረኛ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ህዝቡ እንዲያውቀው እንፈልጋለን፡፡
ይህ የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን ተግባር የሃገራችን ኢትዮጵያን ዓለም-አቀፍአዊ ክብር የሚጎዳ ስለሆነ ከተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም፣ ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ዝርዝር መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ይህን ሳያደርግ ቢቀር ግን፣ ፓርቲያችን የተጣለበትን የአባቶቻችንን ክብርና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መቼም ቢሆን ያለምንም ማወላወል የምንወጣ መሆናችንን ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ኅዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡
ሰላም፣ ተስፋ፣ ፍትህና እኩልነት በዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በተከበሩባት ኢትዮጵያ ዕውን ይሆናል!!!

ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡ

UDJ
ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡየአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ «በመድረክ ዙሪያም ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን፣ አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት፣ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ፓርቲው ከመድረክና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የጀመረውን ውህደት እልባት እንዲያበጅለት መመሪያ ሰጥቷል» ስንል መዘገባችን ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ አስተያየት ያደረጉት አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ድርጅታቸው ከአሁን በኋላ በግንባርነት እንደማይሰራ ገልጸዋል።

ድርጅቶች ልዩነቶቻቸዉን አጣበው ወደ ዉህደት በመምጣት፣ በጋራ ትግሉን ወደፊት ማራምድ እንዳለባቸው የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደትን ጥቅም አጠንክረው አስምረዉበታል። ለመኢአድ፣ ለመድረክ፣ ለሰማያዊ ፓርቲ፣ ለአረና እንዲሁም በአቶ ልደቱ አያሌዉ ይመራ ለነበረዉ ለኢዴፓም ጥሪ አቅርበዋል።
ዉህደት ማድረግ ካልተቻለ ግን፣ አንድነት ለድርጅቶች እዉቅና ሰጥቶ መተባበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ (እንደ በጋራ ሰልፍ መጠራት የመሳሰሉ) ትብብር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል የሚገልጽ እድምታ ያለው ንግግር ነበር ኢንጂነር ግዛቸው ያቀረቡት።
መኢአድና አረና ከአንድነት ፓርቲ ጋር የመዋሃድ ፍላጎት እንዳላቸው ከዚህ በፊት ማሳወቃቸው፣ በዚህም ረገድ አንዳንድ ንግግሮች እየተደረጉ እንደነበረ ይታወቃል።
የመድረክ አባል ድርጅቶች ከአንድነት ጋር ለበርካታ አመታት አብረው የሰሩ እንደመሆናቸው የጠነከረ መቀራረብ ሊኖራቸው እንደሚችል ቢታወቅም፣ በዉህደቱ አንጻር ግን ምን ያህል ከአንድነት ጋር ለመዋሃድ እንደሚፈልጉ፣ ምን ያህል ያላቸውን መሰረታዊ የፖለቲካ ልዩነቶች ለማጥበብ እንደሚችሉ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም።
ሰማያዊ ፓርቲ ለጊዜዉ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት አዝማሚያ ያለው አይመስልም። ነገር ግን በአንድነት ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ተጨባጭ ለዉጦችን በመመልከት የአቋም ለዉጥ ሊያደርግ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።
የዉህደቱ ጥሪ ለኢዴፓ መቅረቡ ብዙዎችን ሊያነጋገር የሚችል አዲስ ዜና ነው። በአንድነት አካባቢ ከኢዴፓ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት መታየቱ፣ በቅርቡ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ አቶ ልደቱ አያሌው ላቀረቡት በጋራ የመስራት ጥሪ፣ ምላሽ ተደረጎ ሊወስድ የሚችልበት ሁኔታም ሳይሆን እንደማይቀር ነዉ።
ኢንጂነር ግዛቸው ለተቃዋሚ ድርጅቶች የዉህደት ጥሪ በማቅረብ ብቻ አልተወሰኑም። ገዢዊ ፓርቲ ኢሕአዴግ የከረረ አቋሙን ቀይሮ ለእርቅና ሰላም እንዲዘጋጅም አሳስበዋል።

Sunday, December 29, 2013

ኢትዮጵያዊኑ ከሳውዲ ፖሊስ ሲጋጩ ለ3 ሠአታት በኢትዮጵያ ቆንስላ ላይ ተቃውሞአቸውን አሠምተዋል

ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከተለያዩ የሣውዲ አካባቢዎች በመሠባሠብ መጠለያ ጣቢያ የገቡ ስደተኞች፤ የኢትዮጵያ ቆንስላ ከፍተኛ እንግልት እንዳደረሰባቸው በመግለጽ ባሰሙት ተቃውሞ ከሳውዲ ፖሊስ ጋር ተጋጩ፡፡ እጃቸውን ለፖሊስ እንደሰጡና በ10 አውቶቡሶች ተጭነው ሹማሲ ወደተሠኘው የመጠለያ ጣቢያ እንደገቡ የገለፁት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከገቡበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ቀናት በኢትዮጵያ ቆንፅላ ዳተኝነት የጉዞ ሰነድ በጊዜ ሣይዘጋጅልን ለእንግልት ተዳርገናል ብለዋል፡፡ ያለ ጉዞ ሰነድ መንገላታታቸውን በመወቃም እሁድ እለት በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ለ3 ሰዓታት ያህል ብሶታቸውን እንዳሰሙ ስደተኞቹ ተናግረዋል፡፡ የሃገሪቱ ፖሊስ አመፅ አስነስተዋል ያላቸውን ስደተኞች ለመደብደብ ሌሊት ወደ ጣቢያው እንደገባ ስደተኞቹ ጠቅሰው፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሠባቸውና በፖሊስ ጥይት የተመቱ እንዳሉም ገልፀዋል፡፡ ኤምባሲው ወደ ሃገር ቤት ትመለሣላችሁ ብሎ ባቀረበው ጥሪ ወደ መጠለያ ጣቢያው እንደገቡ የተናገረች አንዲት ስደተኛ ለኤምባሲው ሰራተኞች ብንደውልም ድብደደባው ካለቀ በኋላ ነው የደረሱት ብላለች፡፡
በድብደባው እንደተጎዳ የተናገረ ሌላው ስደተኛ በበኩሉ፤ የኤምባሲው ሰራተኞች ዘግይተው ከመድረሳቸውም በተጨማሪ እንደቆሠልን እያዩ፣ ወደ ህክምና ቦታ ለመውሠድም ሆነ እርዳታ ለማድረግ አልሞከሩም ሲል አማሯል፡፡ ከተቃውሞና ከግጭቱ በኋላ፤ ለሴቶችና ለህፃናት ቅድሚያ በመስጠት የመመለሻ ሰነድ ተዘጋጅቶ እየተሰጣቸው መሆኑን የተናገሩት ስደተኞች፤ በድብደባ የተጐዱትን ጨምሮ በርካታ ወንዶች አሁንም በመጠለያ ጣቢያው እየተንገላቱ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲን አነጋግረን በጉዳዩ ላይ በሠጡን ምላሽ፤ በወቅቱ በሚዲያዎች የተነገረውን ያህል ባይሆንም፣ “ወደ አውቶቢስ ግቡ አንገባም” የሚል ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ጠቅሰው፤ አንዲት ሴት ከመጐዳቷ ውጪ በሌሎች ላይ የደረሠ ጉዳት እንደሌለ ሣውዲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ጠይቀው መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡ ከ145ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን ያስታወሱት አምባሣደር ዲና፤ አሁንም በመደበኛ በረራዎች በአማካይ እስከ 300 ሠው እየተመለሠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ሱዳን ያለውን ውዝግብ ተከትሎ በሃገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መንግስት ከሌሎች የኢጋድ አባል አገራት ጋር በመሆን የ24 ሠአት ክትትል እያደረገ መሆኑን ቃል አቀባዩ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡

Abune Mathias arrested and released

Ethiopian Review:-The TPLF-installed illegal patriarch in Ethiopia, Abune Mathias, has been temporarily placed under arrest and was released after being interrogated for 72 hours by Tsegaye Berhe, National Security Adviser to the Prime Minister, and other security officials, according to Ethiopian Review sources in Addis Ababa.Leaders of the TPLF junta are apparently upset with statements that have been uttered by Abune Mathias over the past 3 weeks that were critical of the tribal regime. In one particular meeting, Abune Mathias was heard saying that much of the problems facing the church are caused by the ruling party.The Ethiopian Orthodox Church’s
administration in Addis Ababa is currently paralyzed by a growing leadership crisis. Many church leaders are in open revolt and have refused to take orders from the Holy Synod.
Abune Mathias arrested and released

ሰበር ዜና፣ በዓረና-ትግራይ ስብሰባ መታወቅያ የሌለው እንዳይገባ ተከለከለ December 29, 2013 by Abraha Desta በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ እንገኛለን። የህዝብ ስብሰባው ለመጀመር አዳርሹ ሲከፈት ህዝብ በስብሰባው ለመሳተፍ መግባት ሲጀምር አስተዳዳሪዎቹ ደንግጠው ‘በስብሰባው መሳተፍ የሚችል ሰው የቀበሌ መታወቅያ ያለው’ ብቻ መሆን እንዳለበት አወጁ። መታወቅያው እየመዘገቡ ለማስገባት ወሰኑ። ህዝቡ ተቃወመ። የዓረና አመራር አባላትም ድርጊቱ ተቃወሙ። መታወቅያ የሌለው እንዳይገባ ስለተወሰነ ብዙ ሰው ተቃውሞ ስላነሳና መግባት ስለፈለገ የአዳራሹ መግብያ በር ተዘጋ። አሁን የተፈቀደልን አዳራሽ ዝግ ነው። ዓረና ስብሰባው በአዳራሹ በር ባለው ሜዳ ለማካሄድ ወስኗል። ባደራሹ በር አከባቢ ብዙ ህዝብ አለ። ካድሬዎቹ ህዝቡ ለመበተን እየፈተኑ ነው። via:http://ecadforum.com

Saturday, December 28, 2013

Ethiopians in South Sudan seek help Ethiopian emigrants that reside in the Unity State of South Sudan are stating that they are found in war zone and are at risk.

Ethiopians in South Sudan seek help
ESAT News
December 28, 2013

Ethiopian emigrants that reside in the Unity State of South Sudan are stating that they are found in war zone and are at risk.

Six Ethiopians working in the State’s main road construction said they have been hiding inside heavy machineries for the past two days. They said two Ethiopians have been killed while three were wounded.

Although the total number of Ethiopians that have been killed so far is unknown, according to the Voice of America (VoA) Amharic service, 30 Ethiopians have been killed until the December 26, 2013.

The Ethiopian migrants have told ESAT that their government has not reached out to them so far. They said they are puzzled that when the government of Kenya and Uganda have evacuated their citizens from South Sudan, the Ethiopian government did not do.

Four Ethiopian women who have been raped in the Jonglei State of South Sudan have received medical treatment in the United Nations Hospital in Juba.

Meanwhile, According to the Inter-Governmental Authority on Development (IGAD), spearheaded by leaders of seven East African countries, South Sudanese President SalvaKiir expressed hiscommitment to cease fire in the recently war-ravaged country. Uhuru Kenyatta, the Kenyan President, said, “Let it be known we in IGAD will not accept the unconstitutional overthrow of a duly and democratically elected government in South Sudan.”
More than 1,000 people have been killed in fighting between the government and rebels since 15 December when violent clashes began in the capital, Juba.

HORN OF AFRICA: Humanitarian Situation Deteriorates as New Year comes and goes

HORN OF AFRICA: Humanitarian Situation Deteriorates as New Year comes and goes

HRLHA FineDecember 28, 2013
HRLHA’s 2014 New Year Message
Dear friends,
Time does seem to pass ever more quickly. Has it really been a year since the HRLHA office last shared its thoughts on the occasion of the 2013 New Year? The fact is our attention is totally consumed by the job we are doing. For those who are languishing in prisons simply because they hold different political views from those of the ruling party of Ethiopia, for those Ethiopians and others who escaped from fear of persecution and are in refugee camps or live on the streets of the countries they took asylum in looking for their daily slice of bread, even a minute is too long. Soon we all will be joining together to welcome a new year with another new hope to do better. We must recognize the fact that doing better doesn’t happen simply because we wish it to be true. Rather, first we need to take our time and assess this year’s achievements or losses and compare them against the promises we made as this year began. In short, it is a time for “self-analysis”.
We can safely say the outgoing year has been the most turbulent year for defenders of human rights in the Horn of Africa and elsewhere. The struggles of the people which have been inflamed for over two years in North Africa didn’t come to an end and continued to reverberate in the Middle East and in North Africa. The people were attempting to rid themselves of dictatorial regimes and create a better democracy. Fearing that unrest would spread into the sub-Saharan countries, the governments of this region have been very busy in the past two or more years to silence any type of civilian movements in their respective countries. For example, in Ethiopia any individual or group who didn’t support the policy of the governing party was/were automatically labeled as terrorists. Muslim community members who opposed the involvement of the government in their religious affairs, farmers who resisted eviction from their ancestral lands, university students who demanded the improvement of university teaching and learning environments on their campuses were labeled as terrorists and imprisoned, tortured and sometimes killed- thousands escaped to neighboring countries. In general, the prolonged political unrests in, Ethiopia, Somalia, Sudan, S. Sudan and others made these regions unsafe places for citizens to live; they have produced the largest numbers of refugees ever seen in the past decades. Thousands have fled their homelands to seek safety in neighboring countries, including in Yemen, and Middle East Arab Countries out of a fear of persecution and imprisonment.
The Human Rights League of the Horn of Africa and other human rights organizations have repeatedly reported on the humanitarian crises in the Horn of Africa in the outgoing year.
Even though we faced human and financial challenges in the outgoing year and much work remains to be done, I would like to take this opportunity to recognize some significant human rights achievements recorded in 2013 by the HRLHA. Many violations of human rights were compiled and disseminated- written and oral presentations on human rights violations in Ethiopia included – were made at United Nations Human Rights Council session of 2013. Another major accomplishment which I would like to mention is we managed to open HRLHA’s Regional branch office in Uganda/Kampala in October 2013, an event that we strongly believe will help to strengthen the involvement of HRLHA in communities of the region and enhance the efforts of the agency in getting effective results.
Finally, I wish a stable, peaceful, joyful and healthy New Year for all of HRLHA’s members, supporters, staff, volunteers, and friends in the Horn of Africa Countries and elsewhere. I hope the coming New Year will bring democracy, and respect for all forms of freedoms and human rights. Let all people be free from tyranny and suffering at the hands of their dictator governments.
“We fight for Human Rights!”
With Regards,
Garoma B. Wakessa
Executive Director

Friday, December 27, 2013

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በነጭ ሳር ግቢ የሚማሩ ከ25 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ታወቀ

    ኢሳት ዜና :-ተማሪዎቹ የታሰሩት ካለፈው አርብ ጀምሮ ሲሆን፣ እስካሁንም በእነርሱ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት አለመቆሙ ታውቋል። በግቢው ውስጥ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት መጸዳጃ የተበላሸ መሆን፣ የምግብ ጥራት መጓደል፣ የውሀ እጥረት፣ የመብራት ለረጅም ጊዜ መቋረጥ፣ የትምህርት ስርአቱ በተገቢው መልኩ አለመከናወን፣ የመጽሀፍት እጥረት፣ የኮምፒዩተር አለመኖር እና በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የጤና መቃወስ ተማሪዎች ተቃውሞ እንዲያነሱ ግድ ብሎአቸዋል።
ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ  የዩኒቨርስቲው የመማሪያ ክፍሎች መስታውቶች የሰባበሩ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ፖሊሶችን በመጥራት እርምጃ እንዲወሰድባቸው አድርገዋል። በርካታ ተማሪዎች ወከባና እስሩን በመፍራት ወደ የቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውም ታውቋል።
የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ” የሌላ ብሄር ተወላጆች ንብረታችሁን እያወደሙ ነው የሚል ቅስቀሳ  በማካሄድ” ተማሪዎችና የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማጋጨት ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ዩኒቨርስቲው በእስር ላይ የሚገኙትን ተማሪዎች ለማባረር በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል።  የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአስተዳዳራዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተለያዩ ጊዜዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

የጁነዲን ባለቤት በድርድር ተፈቱ !!/ከኢየሩሳሌም አርአያ/

የቀድሞ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አመራር አባልና ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በውስጥ በተደረገ ድርድር ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን የቅርብ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ። 
  « ከሳኡዲ ኤንባሲ ገንዘብ ተቀብለው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል» በሚል በሽብርተኝነት ወንጀል እንዲከሰሱ የተደረጉትና ለአንድ አመት የታሰሩት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሕወሐት መሪዎች በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ እንዲፈቱ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ይህ ሊሆን የቻለው በስደት ከሚገኙት አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር በተደረገ ምስጢራዊ ድርድር ላይ “መንግስት ከዚህ ቀደም በወሰዳቸው እርምጃዎች፣ ፖለቲካዊ ምስጢራዊ ጉዳዮችና ገዢውን ፓርቲ የሚመለከቱ ማንኛውም ነገሮች በየትኛውም ቦታ ላለማጋለጥ፣ ላለመናገር፣..” ከጁነዲን ጋር ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ባለቤታቸው እንዲፈቱ መደረጉን አስታውቀዋል። 
በሙስና የተጨማለቁት አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ደ/ፂዮንና ፀጋዬ በርሄ ከጁነዲን ጋር እንደተደራደሩ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። መጀመሪያም ወ/ሮ ሃቢባ የሰሩት ወንጀል ኖሮ አይደለም የታሰሩት ያሉት ምንጮቹ አቶ ጁነዲን ከስልጣን ለማንሳት ሲባል ብቻ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል። ጁነዲን ባለቤታቸው ከታሰሩ በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ እንዲያውም ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ሚሚ ስብሃቱ በምታዘጋጀው ራዲዮ ጣቢያ « ጁነዲን መታሰር አለባቸው፤ መንግስት እስከ አሁን እርምጃ የማይወስደው ለምንድነው?..ባለቤታቸው አሸባሪ ናት» በማለት የፍ/ቤትን ነፃነት ጭምር በሚጋፋ መልኩ ቅስቀሳ ይካሄድ እንደነበረ ምንጮቹ አስታውሰዋል። አቶ ጁነዲን ከአገር ከወጡ በኋላ እውነቱን እያወቁ መደራደራቸውና ባለቤታቸውን በማስፈታት ሌሎች ንጹሃን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ በተዘዋዋሪ በመፍረድ የኢህአዴግና ካንጋሮው ፍ/ቤት ተባባሪ መሆናቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል ምንጮቹ። አቶ ጁነዲን ምናልባትም « ባለቤቴ በፍ/ቤት ነፃ ተባለች» በሚል በኢትዮጲያ የፍትህና የፍ/ቤት ነፃነት እንዳለ አስመስለው ሊናገሩ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የለም ያሉት ምንጮቹ አክለውም ጁነዲን ምንም አሉ ምን በስልጣን እያሉ ለፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው እንደማይቀር መታወቅ አለበት ብለዋል።
source: harartubes.com

በደቡብ ሱዳን እስከ ሐሙስ፣ ታኅሣስ 17 / 2006 ዓ.ም ባለው ጊዜም ቢያንስ የሰላሣ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ

ደቡብ ሱዳን፤ ማላካል ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከበደና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙት ከሃገሪቱ ነፃ መውጣት ጋር ተያይዞ የአካባቢው ሃገሮች ዜጎቻቸው ያለድንበር፣ ጉምሩክና ሌላም ቁጥጥር እየገቡ የአዲሲቱን ሃገር ምጣኔ ኃብት እንዲያጎብቱ ለማገዝ አስበው በወሰዱት እርምጃ እንደነበር ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልፀዋል፡፡
በተለይ ሰሞኑን የአፐር ናይል ግዛት ዋና ከተማ ማላካል በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር ከወደቀች ወዲህ ኢትዮጵያዊያኑ ብዙ በደልና እንግልት እንደደረሰባቸው፤ በሴቶችም በወንዶችም ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም፣ እስከ ሐሙስ፣ ታኅሣስ 17 / 2006 ዓ.ም ባለው ጊዜም ቢያንስ የሰላሣ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት መጥፋቱን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁባ እንደነበሩ መስማታቸውን፤ እንዲሁም ጁባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደውለው ያሉበትን ሁኔታ መናገራቸውንና ምንም የመፍትሔ ምላሽ አለማግኘታቸውን እነዚሁ በጭንቀት ላይ ነን የሚሉ የአፐር ናይል ስቴት ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ


ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያየኢትዮጵያ መንግሥትም እንዲደርስላቸውና ከዚያ በአፋጣኝ እንዲያወጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
voa

Thursday, December 26, 2013

የድብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግፍ ተባረሩ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲና የጤና ነክ ተማሪዎች ለውዝግብ የተዳረጉት በሚሰጠው ድግሪ ሲያሜ እንደሆነ ከቦታው የደረሰን ማስረጃ ያስረዳል፡፡ ከ1ኛ እስከ 4ተኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች ሲመደቡ ዲግሪያቸው የጤና ሳይንስ መኮንን (Public Health Officer) እንደሚባል እንደተነገራቸው ገልፀው ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው አሁን የህብረተሰብ ጤና (Public Health) ብቻ የሚል ስያሜ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጉዳዩን በማሳወቅ ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን “‹የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ› የሚለው እናንተን አይመጥንም” እንደተባሉ ገልጸዋል፡፡

Debre_Markosደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲና የጤና ነክ ተማሪዎች ለውዝግብ የተዳረጉት በሚሰጠው ድግሪ ሲያሜ እንደሆነ ከቦታው የደረሰን ማስረጃ ያስረዳል፡፡ ከ1ኛ እስከ 4ተኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች ሲመደቡ ዲግሪያቸው የጤና ሳይንስ መኮንን (Public Health Officer) እንደሚባል እንደተነገራቸው ገልፀው ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው አሁን የህብረተሰብ ጤና (Public Health) ብቻ የሚል ስያሜ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጉዳዩን በማሳወቅ ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን “‹የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ› የሚለው እናንተን አይመጥንም” እንደተባሉ ገልጸዋል፡፡

በመልሱ ያልረኩት የዲፓርትመንቱ ተማሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከህዳር 28 ጀምሮ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው የዩኒቨርስቲው ኃላፊዎችና ለፕሬዚደንቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም “ብትማሩ ተማሩ ባትማሩ ግቢውን ለቃችሁ ትወጣላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረባቸው አሳውቀዋል፡፡ ታህሣስ 05 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰበሰበው የዩኒቨርስቲው ሴኔት 173 ተማሪዎች ከግቢ እንዲባረሩ ወስኗል፡፡
ከሰኞ ታህሣስ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ መታወቂያቸውን በፖሊስ ተቀምተው ከግቢው እንዲባረሩ የተደረጉት 173 ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት ሜዳ ላይ ተበትነው እንደሚገኙና ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ በምሬት ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን ለማረጋገጥ የጤና ዲፓርትመንት ኃላፊ ወደ ሆኑት አቶ ዱቤ ጃራ ስልክ ደውለን የተባለው ነገር መከሰቱን ጠቅሰው ነገር ግን “ውሳኔው በአግባቡ ነው የተላለፈው፤ ይህ ስያሜ ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ የነበረ ነው፤ ካሪኩለሙ ላይ ያለው የህብረተሰብ ጤና (Public Health) እንጂ የህብረተሰብ ጤና መኮንን (Public Health Officer) አይደለም” ብለዋል፡፡
አቶ ዱቤ በተደጋጋሚ የዲግሪው ስያሜ “አዲስ የተሰጠ ስያሜ አይደለም” ካሉ በኋላ በተጨማሪም “ተማሪዎቹ ያለ ትምህርት ለ11 ቀናት ግቢ ውስጥ መቀመጣቸው ተገቢ ስላልሆነ ከግቢ እንዲወጡ ተደርጓል” ብለዋል፡፡ በተያያዘ ጉዳይ ከጊቢው የተባረሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈቀደ አንድ ተማሪ “መጠለያ፣ ልብስና ምግብ” እጅግ እንደቸገራቸው ገልፆ በተለይ ሴት ተማሪዎቹ መጠለያ እንዲሰጣቸው ለምስራቅ ጎጃም ዞን የሴቶች ጉዳይ ቢያመለክቱም “ዩኒቨርሲቲው ያባረራቸውን ብንረዳ እንጠየቃለን፤ ስለዚህ ልንረዳቸው አንችልም ማለታቸው ታውቋል፡
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው

Ethiopia Swamped by Tidal Wave of Returned Migrants ADDIS ABABA, Dec 25 2013 (IPS) – The return of 120,000 young undocumented migrant workers from Saudi Arabia to Ethiopia has sparked fears that the influx will worsen the country’s high youth unemployment and put pressure on access to increasingly scarce land.

ETHIOPIA-SAUDI-IMMIGRANTS-LABOUR-RIGHTS

ADDIS ABABA, Dec 25 2013 (IPS) – The return of 120,000 young undocumented migrant workers from Saudi Arabia to Ethiopia has sparked fears that the influx will worsen the country’s high youth unemployment and put pressure on access to increasingly scarce land.
As a result, a growing number of young Ethiopians are choosing to migrate to Sudan to circumvent an indefinite travel ban slapped by the Ethiopian government last month on Ethiopian workers traveling to Middle Eastern countries.
Esther Negash, 28, is from a family of nine that lives on a four-hectare farm dedicated to growing maize in the Tigray region of northern Ethiopia. She has been out of work since leaving school 10 years ago.
Negash’s family recently decided to use their savings to fund her migration to Khartoum in search of employment.
665003303001_2840188667001_2013111551848266734-20“In the last two months, there have been many people returning from Saudi Arabia. This makes things worse for people like me who cannot find work,” she told IPS.
“The rains were short this year and we did not have a good harvest. My family is large, if we don’t get a good harvest then it is very difficult. We heard about work opportunities in Sudan and thought this was our only solution.”
A large number of Ethiopians migrate every year in search of brighter economic prospects, with the Middle East being the dominant destination.
“I was forced to work seven days a week, 20 hours a day. I was not allowed to leave the house. It was hell.” — A 23-year-old woman who just returned from Riyadh 
Saudi Arabia’s crackdown on undocumented foreign workers began after a seven-month amnesty period expired on Nov. 3. Since then, 120,000 Ethiopian migrants have been repatriated to Ethiopia after being corralled in a deportation camp for two months, where conditions are reportedly abject.
Many Ethiopians have reported human rights violations at the hands of their employers as well as while under the control of security forces inside the camps.
IPS spoke to a 23-year-old woman who had just arrived in Ethiopia after working as a domestic in Riyadh for two years. Her account is similar to many other experiences narrated by returnees.
“My employer would sexually abuse me and beat me. I was forced to work seven days a week, 20 hours a day. I was not allowed to leave the house. It was hell,” she said.
“They did not pay me for one year even though I worked also for their relatives. I am so tired and so sad. [But] I am so happy to be back in Ethiopia,” she told IPS.
Despite the many terrible experiences recounted by Ethiopian returnees, poverty and limited economic prospects will continue to force Ethiopian workers to migrate to countries like Sudan and overseas, says the International Labour Organisation, which is working to make regular migration methods more attractive for Ethiopians instead of using unaccountable and illegal brokers to facilitate their migration.
“After the ban, people will try any means possible to work abroad due to a lack of employment opportunities in their home country,” George Okutho, director of the ILO Country Office for Ethiopia and Somalia, told IPS.
“These returnees travelled to Saudi Arabia looking for economic opportunities with a greener pasture mindset in the hope that they could send their family remittances to raise living standards at home. However, most of the time migrant workers are acting on misinformation about the prospects and country of destination,” he said.
A lack of education and skills make Ethiopian migrants especially vulnerable to working in dangerous and exploitative working conditions, both at home and abroad, said Okutho.
“The problem is many of Ethiopia’s migrant workers are uneducated and ill-eqipped even for the domestic work they seek outside the country,” he said. “The result is that even if they go to the Middle East or Sudan, they can earn a little more than when at home, but because they are untrained they end up working in very extreme and difficult circumstances without knowing their rights. “
The Ethiopian government’s planning and logistical capacity has been overwhelmed by the rapidly rising number of returnees. An initial expectation of 23,000 returnees jumped to 120,000 in one month.
“We are engaged with the Saudi government and we are working hard to return Ethiopians stranded in Saudi Arabia,” Dina Mufti, foreign affairs spokesperson, told IPS.
“The number of Ethiopians working illegally is much higher than we anticipated. The Ethiopian government recognises that these people will need employment and so we are trying to create opportunities to assist these people, many of them young, and rehabilitate them back into their communities,” she said.
Dwindling land access in Ethiopia is a critical issue for 80 percent of the population who make a living as small farmers. In the mountainous region of Tigray, the average land availability per household is 3.5 ha.
As life expectancy increases, the potential for subdividing farm plots reduces, leaving many of Ethiopia’s youth food insecure and unemployed.
In the last year, a large number of young people have joined regular protests staged in the country’s main cities to demonstrate their dissatisfaction with high unemployment and inflation.
665003303001_2540786089001_20137122496519734-20The inundation of over 120,000 people has the potential to further disenfranchise youth in Ethiopia, where the majority of the population of 91 million earn less than two dollars a day.
Hewete Haile, 18, lives outside Sero Tabia, a small town where youth unemployment is spiraling. Out of 2,200 households, 560 young people between 17 and 35 are unemployed, without access to land or income.
Outside the Sudanese embassy in Addis Ababa, Haile is queuing with several hundred other young girls, mostly from remote rural villages, in hopes of obtaining a visa to allow her to look for work in Khartoum.
Hewete’s friends say a domestic in Khartoum is paid eight dollars a day compared to four dollars in Addis Ababa.
“I would not be leaving my country if there was a way for me to work and make a good income here in my country,” she told IPS.
“If Sudan does not work out then I will travel from there to the Middle East. I know what happened in Saudi Arabia. I would not be leaving Ethiopia if I could get work here, but it is getting more difficult all the time,” she said.
Source: IPS

Tuesday, December 24, 2013

አ.አ ውስጥ ለጾታ ግንኙነት የገዛትን ሴት ገድሏት ተያዘ

http://www.youtube.com/watch?v=L6ggYrbuXIY

እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ተቃዋሚዎች ከ‹‹ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን›› እያሉ ነው – ‹‹ከእናንተ ጋራ መሣርያችኹ ቢኖርና በመሣርያችኹ ብትመኩም ከእኛ ጋራ ደግሞ እግዚአብሔር አለ፤ አንፈራም፤ ከዚህ በኋላ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/

እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ተቃዋሚዎች ከ‹‹ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን›› እያሉ ነው – ‹‹ከእናንተ ጋራ መሣርያችኹ ቢኖርና በመሣርያችኹ ብትመኩም ከእኛ ጋራ ደግሞ እግዚአብሔር አለ፤ አንፈራም፤ ከዚህ በኋላ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/

  • የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፣ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጋራ ስልታዊ ግንኙነት መጀመራቸው የሚነገርላቸውና ለአፃዌ ኆኅትነት እንኳ ሳይበቁ በደ/ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እልቅና ለመሾም ‹‹መቶ ሺሕ ብር እከፍላለኹ›› በሚል ልጆቻቸውን ለረኀብ የዳረጉት መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (ብይዱ ይመር)ስ እነማን ናቸው?

  • የካህናቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የምእመናን ተወካዮችን ከ92 – 97 በመቶ ድጋፍ ያረጋገጠው የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይት ዛሬ ይጠናቀቃል፤ የጥናቱን ትግበራ የሚቆጣጠርበአፈጻጸምም እየተከታተለ የሚያርምና የሚያስተካክል ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም ተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡
  • ‹‹ይህ መዋቅር አደረጃጀት ስለ መታሰቡ፣ ቅንብር ስለ መደረጉ በቤቱ ስም አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን የልማት አርበኛ ናቸው፡፡ በየመንደሩ ያለው አሉባልታ ይህ ነው አይባልም፤ እዚህ ስናየው ግን የተለየ ነው፡፡ የጥናት ዘገባው ቀጥሎ እንድናየው እንጂ ሁከት አያስፈልግም፡፡ ጀርባዬም ፊቴም አንድ ከኾነ በሕግ ለመተዳደር ምን ያስፈራኛል? አስቀድሞ ይህ እንዲህ ይኾናል እያሉ መደንበር ምን ያስመለክታል? ወጡም ሊጡም እያሉ ያሉት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ነው ይህ ኹሉ ጭፋሮ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት ያለበት ቅ/ሲኖዶስ ይውጣ ያለውን ሕግ መደገፍ ተገቢ ነው!!›› /የደብር አስተዳዳሪ/
  • ‹‹አንድ ድጓ ከዲግሪ ጋራ ይወዳደራል ካላችኹ መቼ ነው እውን ኾኖ የምናየው? እውን ይኾናል ወይ? አምስት እንትንየምንላቸው ካልኾኑ በቀር ይህን የሚቃወም አይኖርምና ቶሎ ይተግበር፡፡ ብፁዕ አባታችን ከዚህ የበለጠ ምን ይጠበቃል? ይሄ ነገር ቶሎ የማይተገበር ከኾነና ወደ ኋላ የምታዘገዩት ከኾነ የልብ ልብ እንዲያገኙ ታደርጓቸዋላችኹ፤ እናንተም ተጠያቂዎች ትኾናላችኹ፡፡›› /የመምህራን ተወካይ/
  • ‹‹የማይነካው ተነካ፤ የዘመናት ጸሎቴ ነበር፤ ፍጻሜውም ዛሬ ዛሬ. . .ይለኛል፤ እንግዲህ ጸሎተ ስምዖንን ነው የምጸልየው፤ ጌታዬ የቤተ ክርስቲያንን መዳን አሳይተኸኛልና ባሪያኽን አሰናብተኝ እለዋለኹ፡፡›› /የምእመናን ተወካይ/
ተጨማሪ መረጃውን ይከታተሉ
haratewahido

አንጀታቸው እጥፍ ያለ፣ በርሃብ የከሱና የጠቋቆሩ፣ የሚለብሱት የሌላቸው 102 ልጆች እስር ቤት ገብተው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፈልገው እሰሩን ቢሉም ጭራሽ ፖሊስ ከቦታው እንዲሄዱ አባረራቸው፡፡

አንጀታቸው እጥፍ ያለ፣ በርሃብ የከሱና የጠቋቆሩ፣ የሚለብሱት የሌላቸው 102 ልጆች እስር ቤት ገብተው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፈልገው እሰሩን ቢሉም ጭራሽ ፖሊስ ከቦታው እንዲሄዱ አባረራቸው፡፡ ነፍሳቸውን ለማዳን ሮጡ፡፡ ጥለውት የሮጡትን ልብስ እና በእንደ ብርድ ልብስ የሚጠቀሙበትን ከሰው ያገኙትን ልብስ ሰብስበው ፖሊሶቹ አቃጠሉባቸው፡፡ በዛ አጥንትን በሚሰብር ብርድ እንዲሁ ራቁታቸውን አድረው ጦም ውለው ነው እንግዲህ እኔ የደረስኩት፡፡ ምንስ ባደርግ የተሰመማኝ ሀዘን ከውስጤ ይወጣል፡፡ አማራጭ የለኝም፡፡ ዞሬ የሄድኩበት እና ቆሞ የሚጠብቀኝ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡ ሄለን እና ነጅብ በመለቀው ቪዲዬ ላይ ታዩዋቸዋላችሁ እነሱን ይዤ ለ100 ሰው ምግብ ላገኝ የምችልበትን አካባቢ እና ሆቴል ፍለጋ ዳከርኩ፡፡…ይህ ከትላንት ወዲያ ቅዳሜ ዲሰምበር 21/2013 ነው፡፡ ትላንት ምሳ አሰርቼ የምችለውን ያል ልብስ ገዝቼ ለማዳረስ ሞከርኩኝ፡፡ በቪዲዮው ላይ የምታዩትም ይህን የማዳረስ ሰራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ ከስውዲን፣ ጽዮን ሀብተሚካኤል፣ ንግስት ፍሬው ሰላም ብሩክ፣ ሰለሞን መንግስቱ ከዋሽንግተን፣ ዮሀንስ ዘርፉ ከሀገረ እንግሊዝ፣ ሰላም ብሩክ ከሳዑዲያ እና ቲጂ ላቭ ሀበሻ በሚል የምትጠቀመው እህቴ ከኩዌት የየበኩላቸውን አስተዋጽዖ አበረከቱ፡፡ ለሁሉም በወገኖቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እነዚህ ሰወገኖቼ ከ50 ጀምሮ ሁሉም አቅማቸው እስከቻለው በላኩልንኝ ዛሬ ዲሰምበር 23 ድረስ አልብሰናል አብልተናል፡፡ ነገን ማን ያውቃል ነገ ራሱ ያውቃል ….



ሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ዜናዊ (ከእየሩሳሌም አርአያ) ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር። የፋብሪካ ስራውን በግንቦት 1983ዓ.ም ማግስት የለቀቀው የአቶ መለስ ወንድም ኒቆዲሞስ ከአሜሪካ በ25ሺህ ዶላር የተገዛች አዲስ አውቶማቲክ ማርሽ አውቶሞቢል እንዲይዝ ተደረገ።

ኒቆዲሞስ ዜናዊ  የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር።
 የፋብሪካ ስራውን በግንቦት 1983ዓ.ም ማግስት የለቀቀው የአቶ መለስ ወንድም ኒቆዲሞስ ከአሜሪካ በ25ሺህ ዶላር የተገዛች አዲስ አውቶማቲክ ማርሽ አውቶሞቢል እንዲይዝ ተደረገ። ተራ ወዛደር የነበረ ሰው 25ሺህ ዶላር የሚያወጣ መኪና ሊገዛበት የሚችል የገንዘብ አቅም እንደሌለው ግልፅ ቢሆንም ነገር ግን ይህን ያክል የገንዘብ መጠን በማውጣት ለኒቆዲሞስ የተበረከተለት ስጦታ ወንድሙ አቶ መለስ ዜናዊ የሚመሩት ሕወሐት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፤ ኒቆዲሞስ አካል ጉዳተኛ ነው በሚል ሰበብ አውቶሞቢሉ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልበት ነበር አገር ውስጥ የገባው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ “ወጋህታ” የተባለች በትግርኛ ቋንቋ በአገር ውስጥ ትታተም የነበረች የነፃው ፕሬስ ጋዜጣ ከጉምሩክ ለኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ መኪናው እንዲገባ የተሰጠውን፣ በስሙ ተፅፎ ከነመኪናው ሻንሲ ቁጥር ጭምር የተገለፀበትን ደረሰኝ ማስረጃ በማውጣት ጋዜጣዋ አጋልጣለች። ከዜና ዘገባው ጋር በተያያዘ በወቅቱ በተለያዩ ጋዜጦችና ሌሎች ወገኖች ከተነሱት አስተያየት አዘል ጥያቄዎች ተከታዩ ዋናው ነበር፤ « ..ኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ አውቶሞቢል እንዲገባለት የተደረገው ከበላይ አካል በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ነው። የገንዘብ ምንጩ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እንደሆኑ ግልፅ ነው።
 ከመኪናው ግዢ እስከ ጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ፍቃድ ድረስ ሙስና ተፈፅሟል። ኒቆዲሞስ ይህን ህገ-ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ሲደረግ የአገሪቱ መሪ አቶ መለስ ወንድም በመሆኑ ነው። ስለዚህም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ አቶ መለስ ከሙስናው ጋር በተያያዘ ሊጠየቁ ግድ ነው። ለምሳሌ በሙስና እንዲከሰሱ ከተደረጉት ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስዬ አብርሃ የቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ወይም ማመሳከሪያ ነው። አቶ ስዬ ለወንድማቸው ምህረተአብ አብርሃ ሰባት መኪኖች ያለቀረጥ እንዲገቡ አድርገዋል የሚለው ክስ ይጠቀሳል። አንድ መኪና ሆነ ሰባት አሊያም ሰባት መቶ..ቀረጥ እስካልተከፈለባቸው ድረስ ሙስና ለመሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም የኒቆዲሞስ ጉዳይ ሙስና መሆኑ ግልፅ ነው። ከተፈፀመው ቀረጥ ያለመክፈል ክስ ጋር ኒቆዲሞስና ወንድሙ አቶ መለስ በሙስና ሊከሰሱ ይገባ ነበር። » የሚሉ ነጥቦች ነበሩ ከተለያዩ ወገኖች ይነሱ የነበረው። ይህ ጉዳይ በተለይ በስፋት አነጋጋሪ ሆኖ የነበረው በዘጠናዎቹ የመጀመሪያ አመታት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተከታዩ ነው። ኒቆዲሞስ ዜናዊ ከተራ ወዝአድርነት ወጥቶ በአንድ ግዜ ሚሊየነር የሆነበት ሚስጥሩ በ1988 ዓ.ም አንድ የኤርትራና ጣልያን ዘር ያለው ግለሰብ ከሮም አዲስ አበባ ይመጣል። ከዚያም ከኒቆዲሞስ ዜናዊ በጋራ « ጃክሮስ ኢትዮጲያ » የተባለ ድርጅት ያቋቁማሉ። 
ኒቆዲሞስ የጃክሮስ ግማሽ (50%) ባለድርሻ ሆኖ ነበር ድርጅቱ የተመሰረተው። “ጃክሮስ” በተቋቋመ ማግስት የመንግስት ሚዲያ የሆኑትን የኢትዮጲያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም ፋና ራዲዮ በማስታወቂያ ተቆጣጠረው። በተጨማሪ የአማረ አረጋዊ « ሪፖርተር » ጋዜጣ ማስታወቂያ በተጋነነ መልኩ ከማውጣት ባለፈ ስለ ድርጅቱ (ጃክሮስ) ሰፊ የዜና ዘገባና ትንታኔ በመስራት ተከታታይ ሽፋን መስጠት ያዘ። በጋዜጣውና በመንግስት መገናኛ ይቀርቡ የነበሩት ማስታወቂያዎችና ዘገባዎች ፥ « ..ጃክሮስ ኢትዮጲያ, በአገራችን የመጀመሪያው የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚያካሂድ፤ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቪላዎችን በመገንባት ለደንበኞቹ በአጭር ግዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ ነው፤ ለግንባታ ከሚጠቀማቸው ቁሳ-ቁሶች መካከል በተለይ ለቪላው ማሳማሪያ የሚጠቀማቸው ከውጭ አገር የመጡና ዘመናዊ ናቸው፤ እንደ ደንበኛው ፍላጎትና ምርጫ የሚገነባው በቂ የዋስትና ሽፋን በድርጅቱ የሚሰጠው ሲሆን፣ ጃክሮስን የተለየ የሚያደርገው የሚገነቡት ቪላዎች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁና የውጭ አገር ዘመናዊ ቪላዎች አይነት መሆናቸው ጭምር ነው። ደንበኛው ሙሉ ክፍያ የሚከፍል ከሆነ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ መኖሪያውን አጠናቆ ያስረክባል፤ ከደንበኛው ጋር በሚደረግ ስምምነት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል፤ ይህ ማለት የረጅም አመት ክፍያ ድርጅቱ ይሰጣል።…» የሚሉት በተጋነነ መልክ ይቀርቡ ከነበሩት ይጠቀሳሉ። ድርጅቱ እንደ ሽፋን የተጠቀመበትና የተጠቀሱት ሚዲያዎች ያራግቡ የነበረበት አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር።
 በ1988ዓ.ም የአትላንታ ኦሎምፒክ የሚካሄድበት አመት ነበር። እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ የሚሳተፉበት፣ እነ ፋጡማ ሮባና ደራርቱ ቱሉ የተካተቱበት ጭምር ነበር። ሁሉም ኢትዮጲያዊ ማለት ይቻላል ከወራቶች ቀደም ብሎ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠብቅ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ጃክሮስ” ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ኢላማ አድርጎ የተነሳው የአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱን ቤት በነፃ እገነባለሁ በሚል ነበር። በቀድሞ ወረዳ 12 ቀበሌ 07 የሚገኘውን የዋሚ ቢራቱ መኖሪያ በሁለት ወር ውስጥ ሰርቶ እንደጨረሰ ተናገረ። ቀደም ሲል የነበረውን የዋሚ ቤት በማደስ የሰራውና በከፍተኛ ደረጃ የተራገበለት መኖሪያ በቲቪ መስኮት የታየውና ተጨባጩ እውነታ ለየቅል ነበሩ። ለቤቱ ግንባታ ተብሎ ዙሪያውን የዋለው ለተለያዩ ቁሳቁሶች ማሸጊያነት (ለምሳሌ ከውጭ የሚገቡ ፍሪጆችና ቴፕ..ወዘተ ጉዳት እንዳይገጥማቸው ከውስጥ በማሸጊያነት ) የሚውለው ፎም ነበር። ከዚያ በቀለም እንዲያሸበርቅ ከተደረገ በኋላ « 2 ሚሊዮን ብር በማውጣት ጃክሮስ ለዋሚ ቢራቱ ቤት ገንብቶ አስረከበ..» ተብሎ በጋዜጣውና በሚዲያ አስነገረ። አንጋፋው አትሌት በወቅቱ ከአሜሪካ ለመጣውና ቀበሌ 11 ለሚኖረው እስክንድር አሰፋ ስለቤቱ ሲናገር በሃዘን ጭምር ነበር፤ « የበፊቱ መኖሪያዬ ይሻለኝ ነበር። እንኳን 2 ሚሊዮን ብር 1ሺህ ብር አልወጣበትም። እኔን መነገጃ ማድረጋቸው ለምን እንደሆነ አልገባኝም።» ነበር ያለው ዋሚ።
 በእርግጥም እነኒቆዲሞስ በዋሚ ነግደዋል። ከአሜሪካ የመጡ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ጃክሮስን አምነው 70ሚሊዮን አስረከቡ። ሌሎች ወገኖችም ቀለጡ። አንድ አመት ቢጠብቁ ምንም ነገር የለም። ከአሜሪካ የመጡ ወገኖች ከብዙ መንከራተት በኋላ የደረሰባቸውን በደል በኢ.ቲ.ቪ “አይናችን” ፕሮግራም ቀርበው « ለአመታት ሰሃን አጥበን፣ ደም ተፍተን ሰርተን ያጠራቀምነውን ገንዘብ በአደባባይ ተዘረፍን። ህግና መንግስት ባለበት አገር እንዴት እንዘረፋለን?..መንግስት ይፍረደን!.» በማለት በእንባ እየተራጩ አቤቱታቸውን አሰሙ። እነ ኒቆዲሞስ ከህብረት ኢንሹራንስ ጋር የዋስትና ውል አለን ብለው ያሉትም በጭራሽ ከተገለፀው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የህብረት ኢንሹራንስ ዋና ሃላፊ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በወቅቱ አጋለጡ። ኤርትራዊው የጃክሮስ ባለድርሻ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰር ተደረገ። የሚገርመው ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል መሆኑ እየታወቀ፣ ጉዳዩ በማእከላዊ ምርመራ መያዝ ሲገባው ወይም የጃክሮስ ቢሮ ይገኝበት በነበረው ቦሌ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ መታየት ሲገባው…ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት በሌለው ወረዳ 12 የፖሊስ ጣቢያ ጉዳዩ መያዙና መታሰሩ እንቆቅልሽ ነበር። ሶስት ቀን ብቻ ከታሰረ በኋላ ፍ/ቤት ሳይቀርብ “በ2ሺህ ብር ዋስ” ተፈታ።
 በተፈታ ማግስት በቦሌ እንዲወጣ ተደረገ። ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ኒቆዲሞስ ነበር። የተዘረፉት ወገኖች በድጋሚ ወደ ኢ.ቲ.ቪ ቢሄዱም መስተናገድ አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነበር። የዘረፋው ጉዳይ በነፃው ፕሬስ በየግዜው ቢነሳም ሰሚ ግን አልነበረም። ነሐሴ 1993ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኛ ሴኮቱሬ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አስገራሚ ነበር። ሴኮ « ከወንድሞ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ነገር አለ፤ ስለጉዳዩ የሚሉት ነገር ይኖራል?» ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ « በመጀመሪያ ደረጃ ወንድሜን ያገኘሁት ከአስር አመት በኋላ በእናታችን የቀብር ስነስርአት ላይ ነው። አዲስ አበባ እንደገባን ካገኘሁት በኋላ አግኝቼው አላውቅም። የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ እነደሰማሁ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር» አሉ። የአቶ መለስ ምላሽ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነበር፤ “አግኝቼው አላውቅም” ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ “ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር” አሉ። ሌላው ነጥብ ወንድማቸው ኒቆዲሞስ በዘረፋ ወንጀል ተሰማርቶ እንደነበር ማመናቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል።
 ኒቆዲሞስ ዜናዊ በአቋራጭ ዘርፎ ሚሊየነር ሆነ። እጅግ አምባገነን ባህርይ የተጠናወተው ሰው ነው። ማን እንዳስታጠቀው የማይታወቅ ማካሮቭ ሽጉጥ አለው። በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው “ሃረግ” መዝናኛ ያዘወትር ነበር። በሴተኛ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየመዘዘ ፍዳቸውን ያሳይ ነበር። ማንም አይጠይቀውም። ሲጠቃለል፥ ከጥቂት ወራት በፊት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ዙሪያ በኢ.ቲ.ቪ አንድ ፕሮግራም ተሰርቶ ነበር። «ጠላ ሻጭ» ወዘተ ተብለው የቀረቡት ከአቶ መለስ ጋር በአባት የሚገናኙ ናቸው። ኒቆዲሞስና መለስ ግን የአንድ እናትና አባት ልጆች ናቸው። ስለሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ለምን እሱ በፕሮግራሙ አልተካተተም?…ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። ዘርፎ ሃብታም እንደሆነ በማስረጃ ስለተጋለጠና ህብረተሰቡ ጉዳዩን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው።
source: harartubes.com