Monday, January 20, 2014

ሰበር ዜና በወንድም አብዱረዛቅ አክመል ላይ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉ ታወቀ፡፡

ሰበር ዜና
በወንድም አብዱረዛቅ አክመል ላይ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉ ታወቀ፡፡ ከውድ ኮሚቴዎቻችንን፤ወኪሎቻንን ፤ወንድሞቻችን እና  ዳኢዎቻችን ጋር በግፍ ያለወንጀሉ ከ 17 ወራት በላይ በግፍ በሂጅራ ኮምፓውንድ(ቂሌንጦ) የሚገኘው ወንድማችን አብድረዛቅ አአክመል ከሳምንት በፊት ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ሲሆን ፍርድ ቤቱም ለጥር 12 ተለዋጭ ቀጠሮሰጥቶ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡  


በዛሬው እለትም ወንድማችን በቀነ ቀጠሮው መሰረት ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በወንድም አብዱረዛቅ አክመል ላይ የጥፋተኝነት ብይን በማስተላለፍ የመከላከያ ምስክሮችን የካቲት 22 እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ወሳኔ ማስተላለፉን ምንጮች ለ“FOH” ገልጸዋል፡፡
ወንድም አብዱረዛቅ አክመል የአዕምሮ ህመም ስላለበት የዋስ መብቱ እንዲጠበቅለት እና ጉዳዩ ለብቻው ተለይቶ እንዲታይለት ጠበቆቹ ከዚህ ቀደም ደጋግመው የጠየቁ  ቢሆንም ከአማኑኤል ሆስፒታል የአዕምሮ ህመም እንዳለበት የሚያስረዳ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ አዞ የነበረ ሲሆን ሆስፒታሉም የአዕምሮ ህመም የለበትም ሲል ደብዳቤ በመፃፍ ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲቀጥልበት ብይን መስጠቱ እና የሱ ብቻ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከሌሎች ኮሚቴዎቻችን ተለይቶ ብቻውን እየቀረበ እንደሚገኝ በ “FOH” መገለጹ ይታወሳል፡፡


ድል ፍትህ ለተጠማው ኢትዬጵያ ሙስሊም!!!

No comments:

Post a Comment