Sunday, March 2, 2014
በአንድ ጎሳ እና ቋንቋ አመራር ስር ወድቋል በሚልና በዘረኝነት ሰራተኞቹን ፍዳቸውን እያሳየ ነው በሚል የሚተቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የበረራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ። እንደ ሽግግር ምክርቤቱ ዘገባ የስልጣን መልቀቂያው ጉዳይ ግልጽ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ሌሎች ምንጮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ስዊዘርላንድ በረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ካረፈ በኋላ በአየር መንገዱ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ። ምንጮቹ የአየር መንገዱ አብራሪዎች በቂ እውቀት እና ችሎታ እያላቸው ከውጪ አብራሪዎችን በማስመጣት ለኢትዮጵያውያኑ እድገት እና የበረራ ፍቃድ መከልከል እንዲሁም አላስፈላጊ የሆነ መንግስታዊ የደህንነት ወከባ እና የአይነ ቁራኛ ጥበቃ በአብራሪዎች ላይ ከመደረጉም በላይ የስራ መብቶቻቸው እና የሰብአዊ መብቶቻቸው በዘረኝነት ላይ የተመረኮዘው የአየር መንገዱ ማንጅመንት እንደማያከብርላቸው እነዚሁ ምንጮቹ አክለው የሚገልጹ ሲሆን፤ በወያኔ ፈጠራ ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራን “የአእምሮ በሽተኛ ነው” በሚል የተወራው ወሬም በአየር መንገዱ የሚበሩ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት እየሆነው እንደሆነም ምንጮች ይናገራሉ። Source ze-Habesh
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment