ትላንት የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡20 ላይ መካኒሣ አቦ ማዞሪያ ከይልማ ሆቴል ዝቅ ብሎ ከአዋሽ ባነንክ በስተጀርባ ባሉ መንደሮች አንድ የወያኔ ፌዴራል ፖሊስ በክላሽንኮብ አውቶማቲክ ጠመንጃ የአራት ልጆች እናት የሆነቸውን የቤት እመቤትት ከልጆችዋ አባት ጋር ደጋግሞ በመተኮስ ገድሎአቸዋል፡፡ በጣም የሚሳዝነው ደግሞ ገዳዬን ጎይቶም ሐጎስን ለማስመለጥ ቁጥር ስፍር የሌለው የፖሊስ ኃይል በስፍራው እንዲሰማራ የተደረገ ቢሆንም በአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ ብርታት ሳይወዱ በግዱ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ለይስሙላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የዘውት ሄደዋል፡፡
የሟቹቹም አስከሬን እስከ 12፡፡00 ድረስ ከወደቀበት ሳይነሳ ት/ቤት የዋሉ የሟቾች ልጆች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የወላጆቻቸው አስከሬን መሬት ላይ በደም ተዐማልቆ በቤታቸው ወለል ላይ ተጋድሞ ሲጠብቃቸው ሕፃናቱ በድንጋጤ ራሳቸውን ስተው በመውደቃቸው ክፉኛ ስለተጎዱ ማምሻውን በአካባቢው ሕዝብ ርዳታ ወደ ሀኪም ቤት ተወስደዋል፡፡ በጣም የሚያስደንቀው ነግር ግድያው ወደተፈፀመበት ቤት ማንም እንዳይገባ ተክልክሎ ውሎ የሟች ልጆች ከት/ቤት ሲመለሱ ለጊዜው እንኳን ለማረጋጋት ሳይሞከር በስፍራው የነበሩ የገዳይ ባለደረባ ፌዴራል ፖሊሶች የሕፃናቱ አዕምሮ እንዲታወክ ቀጥ ብሎው እነዲገቡ ያደሩጉት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡
ሟች በከባ መኪና ሾፌርነት የሚተዳደር ሲሆን ከመስክ በተመለሰ ማግስት ነው በወያኔ ቅልብ በግፍ የተገደለው፡፡ የሞቴት ባልና ሚስት ከክፍለሃገር ወደ አዲስ አበባ መጥተው የሚኖሩ ሲሆኑ ከጎረቤት በስተቀር አዲስ አበባ ውስጥ የቅርብ ዘመድ እንደሌላቸው ተረጋግጧል፡፡ አራት ሕፃናት ልጆች ያለ አሳዳጊ መቅረታቸውና ወላጆቻቸውም በግፍ መገደላቸው ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች የሚያሳይ ነው፡፡ ጎበዝ! ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው?

No comments:
Post a Comment