
ሲኖዶሱ ቦሌ መድኃኔ ዓለም የቆመው የፓትርያርኩ ሐውልት እንዲፈርስ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ የተሰቀለው የፓትርያርኩ ፎቶም እንዲወርድ ዛሬ ጠዋት ወሰኗል፡፡ እንዴት እዚህ ውሳኔ ላይ ሲኖዶሱ እንደደረሰ በዝርዝር የቀረበ ማብራሪያ ይፋ አልሆነም::
ይህ መልካም ጅምር ይመስላል:: መንግሥተ ሰማያቱ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ብሎ የተናገረውን ሰው ዓይነት መሆኑ ነው መሰለኝ:: የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ቅዱስነቱ ቀርቶበት በጸጸት እንዲህ ደህናና የአምላክን መስመር ለመያዝ መፈለጉ ጥሩ ጅምር ነው ካዘለቀው:: የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የፖለቲካ መሣሪያነቱን ቀነስ አርጎ የእግዚአብሄርን ቃል መከተሉ እሰየው የሚያስኝ ነው::
የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ወደ ልቡ እየተመለሰ ይሆን? የወደፊቱን ደግሞ እንናያለን::
No comments:
Post a Comment