Thursday, March 6, 2014

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ

ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድርና የኦህዴድ የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ።
አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው ነው ዛሬ ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት።
አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም ነው የተወለዱት አቶ አለማየሁ።
የኦህዴድ ማዕከላዊ  ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም ፥ ላለፉት 24  ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች  ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር  ታጋይ ነበሩ ብሏል።
በ1981 ዓመተ ምህረት የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል።
ከ1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል።
2002 ዓ.ም ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው ፥ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሰርተዋል።

No comments:

Post a Comment