Sunday, March 9, 2014

ሰበር ዜና ለነጻነት የሮጡት ታሰሩ ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ‹‹ለነጻነት እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ተሳታፊውን ሲያነቃቁ ውለዋል፡፡ በሩጫው ላይ ከተነሱ ጥያቄዎችና መፈክሮች መካከል ርዕዮትና ሌሎች የህሌና እስረኞች ይፈቱ፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪነት ከሆነ አሸባሪዎች ነን፣ ውሃ ናፈቀን፣ መብራት ናፈቀን፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ፣ ውሸት ሰለቸንና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ከመነሻው የጀመረው የተቃውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሲከታተሏቸው የዋት ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች ሩጫውን ጨርሰው ሲገቡ አስረዋቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሩጫው ተሳታፊዎች ታስረው ይገኛሉ፡

No comments:

Post a Comment