Wednesday, May 8, 2013

ሮቤል ከቦስተኑ የሽብር ጥቃት ጋር ግንኙነት የለውም’ – ጠበቃ ደረጀ ደምሴ

በቦስተን ማራቶን ላይ ከተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የቆየውና ክሥ የተመሠረተበት ወላጆቹ ትውልድ ኢትዮጵያ የሆኑት ሮቤል ፊሊጶስ የተከሰሰበት ጉዳይ ቀደም ሲል ይነገር የነበረውን ያህል እንዳልሆነና ወደፊት በሚካሄደው የፍርድ ሂደትም አወታዊ ውጤት እንደሚጠብቁ ጠበቃው ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አስታወቁ፡፡
አቶ ደረጀ ደምሴ – የሮቤል ፊሊጶስ ጠበቃ
ቦስተን ማሣቹሴትስ የሚገኙት የሮቤል ፊሊጶስ ጠበቃ አቶ ደረጀ ደምሴ ሲናገሩ ሮቤል በፃርናየቭ ወንድማማቾች ከተፈፀመው አድራጎት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብለዋል፡፡
ሮቤል ፊሊጶስ በመቶ ሺህ ዶላር ዋስትና እንዲለቀቅ ጉዳዩን የያዘው ፌደራል ፍርድ ቤት ትናንት የወሰነ ሲሆን ጉዳዩ በሚታይበት ጊዜም ከቤተሰቦቹ ጋር በቤት ውስጥ እሥር እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
ሮቤል ፊሊጶስ
ሮቤል ፊሊጶስ
ጉዳዩ ፌደራል በመሆኑ የፍርዱ ሂደት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ሊዘልቅ እንደሚችል ጠበቃው አቶ ደረጀ ደምሴ ጠቁመው ለፊታችን ግንቦት ዘጠኝ መቀጠሩን ገልፀዋል፡
 ተጨማሪና ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ፡፡

No comments:

Post a Comment