Sunday, May 12, 2013

ዶ/ር አድሃኖም ስለሃገር ጥቅም ይከበር ብለው ያሉት ደስ ሲል


ዓቢቹ ነጋ 
የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከጫካ ከመጡት የወያኔ ጀሌወች በትምህርትም ሆነ በአስተሳሰብ የተሻሉና በደም ያልተጨማለቁ ናቸው ሲባል ብዙ ሰምተናል። በመሆኑም ያስታርቂነትና የመልካም አስትዳደር ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ይሆናል አያሉ ብዙ ሰውች ገምተው ነበር። አስተዋይና የምሁርነት ባህሪ እንዳላቸውም ይነገራል።Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus is currently the Minister of Foreign Affairs of Ethiopia
አዲሱን ሥልጣን እንደያዙ የሰከነ ፖለቲካና በሎጂክ የተደገፈ የውጭ ፖሊሲ ነድፈው በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ የሚአቀራርብ የፖለቲክ መርሃ ግብር ያሳዩ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር። በቅርቡ በውጭ ሃገር ጉብኝታቸው ጊዜ ዲያስፖራውንና የዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭን አስመልክቶ በዩቲውብ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ በጥሞና አዳምጠነዋል ። የንግግራቸው አንኵኣር መልእክት አንድና አንድ ነው። ኢትዮጵያኖች የሃገር ጥቅምን ፤የኢኮኖሚ እድገትን፤ የማህበራዊ ስራዓትና ብልጽግናን ከሚጎዳ ተግባር  እንዲታቀቡ ለዘብ ባል መልኩ አሳስበውናል።
አክለውም  በፖለቲካ ልዩነቶች አኣንዱ በግራ ሌላው በቀኝ መሰለፍ ይችላል ብለዋል አውቁ የፖለቲካ ዶክተር። የህ ካንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አና ምሁር የሚጠበቅ የዲፕሎማሲ ቍዋንቍዋ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ዲያስፖራው በየጊዜው በሰላማዊ ሰልፍ፣ በጽሁፋ፤ በመግለጫ፤ በመገናኛ ብዙሃን ወዘተ ወያኔን የሚነግረውና የሚቃወመውም ለዚሁ ዓላማ መሆኑ ይታወቅ።  በዚህ ብዙ ጠብ አይኖርም።
ነገር ግን በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በቦንዱ ሽያጭ፤በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚና በልማት ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ የሚአሰማው ለምን ይሆን ብለው ዶክተሩ እራሳቻውን መጠየቅ ይኖርባቸዋል።የህክምና ሙያዎን አልረሱት ከሆነ ለአንድ በሽተኛ ወይም ታካሚ መድሃኒት ከመታዘዙ በፊት ለበሽታውና ለህመሙ መንስዔ የሆኑት ጉዳዮችን መጀመሪያ ማጠናትና ግድ ይላል።  የበሽታውን አይነትና በሽታው የተከሰተበት ምክንያት ከታወቀ በህዋላ ህክምናው ይሰጣል። እንደህክምና ጠበብትነትዎ መልሱን ማፈላለግና ታካሚዉን መርዳት የርሶ ፋንታ እንጂ የታካሚዉ አይሆንም። በርግጥ ህክምናው የተሳካ እንዲሆን በሽተኛውም መተባበር የኖርበታል።
በሃገርቤትም ሆነ በውጭ ተስዶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ ነፃነት፤  ኣንደነት፤  ፍቅር፤ ሰላምና ብልጽግና ሁሉም ቀናኢ መሆኑ በውል የሚአውቁት  ይመስለናል።  በተደላደል ሃገር እየኖረ፤ ሶስት ጊዘ በቀን እየተመገበ፣ በመኪና እየተንደላቀቀ ፤በጥሩ ቪላ  ቤት እየኖረ ፤የተፈጥሮ መብቶቹ ማለት የመጸፍ፤  የመናገር፤ የመቃወም፤ የመሰብሰብ፤  የመሰለፍ፤ በፈለገበት አካባቢ እየተዘዋወረ መኖርና መሰራት እየቻለ በወያኔ ጨምላቃ ፖለቲካ የሚነንጋገረውና የሚቃወመው ለምን ይመስለዎታል። እትበቱ የተቀበረችበት ዉድ ሃገሩ ኢትዮጵያ በገንዛ ልጆችዋ እየተጠቃችና እየፈራረሰች መሆኑን ስለተረዳ ጨርሳ ሳትወድም ከውድቀትዋና ከመፈራረስዋ በፊት ህዝቤንና ሃገሬን ልታደግ ብሎ እንጅ የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጉዳት ከመነሳሳት የመነጨ ስሜት እንዳልሆነ ዶክተሩ ሊገነዘቡት ይገባል። ኢትዮጵያዊው ለሃገሩ ቀናኢ ለመሆኑ የድሮ ታሪኩና ያሁን ተግባሩ ምስክር ናቸው። የተማሩት ድክተር አድሃኖም ይህን የኖረ እውነታ ያጡታል ተብሎ አይገመትም።
በህክምና ሙያ አንደተመረቁ ይነገርልዎቀታል። ዳያስፖራው ለዚህ ኣድናቆቱን የሚነፍግዎ አይሆንም።በአንፃሩ አብዛኛው ዳያስፖራ በተላያየ ሙያ ከፍተኛ ትምህርት፤እውቀትና ልምድ ያካበተ መሆኑን የሚዘነጉት እንደማይሆን ተስፋአለን። የዕድሜዎን ክልል ስናሰላስል በኀይለሥላሤ ዘመን እንደተማሩ እንገምታለን። እስኪ በዚያን ጊዜ የነበረውን የትምህርት ደረጃና በርስዎ መንግስት ጊዜ ያለውን የትምህርት ጥራት አነጰጵረው ፍርድ ይስጡ።
ሐገርም በተስቦ፤ በኤድስ፤ በሳንባ ነቀርሳ ፤በወባ  በሽታወች አይታመም እንጂ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ስነምግባር አካሄድ ትታመማለች። ኢኮኖሚው ሖዋላቀር ሲሆን ፤ የሃገር ብልጽግና ባለበት ሲረግጥ ፤ አንዳድ ግዜም ወደ ሁዋላ ሲሄድ፤ የህዝብ ኑሮ ሲጎሳቆል፣ ስራጥነትና ቦዘኔነት ሲሰፍን፤ ዜጎች በሃገራቸው አንደሁልተኛ ዜጋ ሲቆጠሩ፤ በማንኛም የሃገሪቱ ክፍሎች አየተዘዋወሩ መስራትና መኖር ሲከለከሉ፤ ህዝብ መፈናቀል አፈናና እንግልት ሲበዛበት ወይ ወደ ዓመፅ ያመራል ውይ የስራ እድልና አንፃራዊ ሰላም አገኛለሁ ብሎ ወደ አመነበት ሃገር ይሰደዳል። በሃገራችን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በቁንጮነት የሚመሩት በየኣመቱ ወደ አረብ ሃገራት፣ አፍሪካ፣ አዎሮፓ፣ አሜሪካ፤ ካናዳ፤  አውስትራሊያ፣ አስያ የመሰደደውን የህዝብ ቁጥር በውል የሚአውቁት ይመስለናል። በተባበሩት መንግስታት ግምት 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ አሃጉራት ተበትነው እነደሚገኙ ይዘግባል። በርግጥ እርስዎና ግብራበሮችወ የሃገርን አንጡራ ሃብት እየዘረፋችሁ በተልያዩ የዓለም አቀፍ ባንኮች ካሸሻችሁት ንብረት ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ ኢምንት መስሎ ይታየዎት ይሆናል። አገር የሚገነባውን ኢኮኖሚ የሚፈጥረውን ህዝብ ማጣት ግን እጅግ የከፋ ጥፋት ነው። ይህ ለምን አንደሆነ የሚረዱት ይመስለናል።
ዶ/ር አድሃኖም የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔ የሆኑትን ላእላይና ታህታይ (Basic and Super Structure) ምክንያቶችን መጠየቅና ማወቅ ተገቢ ይመስለናል። ከሙያዎም ሆነ ከሃላፊነትዎ አንጻር ጉዳዩን መመርመርና መረዳት ይጠበቅብዎታል። ለማስታወስ ያህል የሚከተሉትን በጥሞና ይመለክቱና የትኛው ነው የሃገርን ጥቅም የሚጎዳ ሃገርን የሚአጠፋ ስራ እየሰራ ያለው ብለው ይጥይቁ። አስር ሽህ ኪሎሜትር በድሪም ላይነር መጙዝ ሳያስፈልግዎ መልሱን አዲስ አበባ ላይ ያገኙታል።
በመጀመሪያ ሁሉም የሃገርን ትቅም ማስቀደምና ማስጠበቅ እንዳለበት እንስማማለን። ከሁሉም በላይ ግን ይህ ሃላፊነት ሃገሪቱንና ህዝብን እናስተዳድራለን በሚሉት መሪወችና ሃልፊወች ላይ አጅግ የገዘፈ መሆኑን  ያለመጠራጠር መቀበል ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ላይ በጉልበት ነግሳችሁ የምታስተዳድሩትንና የምትገዙትን ህዝብና የሃገር ጥቅም የከዳችሁ የመጀመሪወችሁ ተጠያቂ  አርስዎና ግብራአበሮችዎ ናችሁ።  የመጀመሪያው ሃገር ሻጭና የህዝብ ጥቅም  ነጣቂ ማነው ቢባል መልሱን ከጉያው ያገኙታል። ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ፀረ ህዝብና ፀረ ሃገር ድርጊታችሁን እንመለከት።
ለረዥም ዘመናት ነፃነቷዋንና አንድነቷዋን ጠብቃ የኖረችውን ሃገር አካልዋን ገንጥሎ ወደብ አልባ ያደረገ  ወያኔ ወይስ ዲያስፖራ። በግራ ወይም በቀኝ አስተሳሰብ ከርስዎና ከቡድንዎ የተለየውንና የተቃወመውን ሁሉ የሚአስር፣ የሚገል የሚአሳድድ ማነው ወያኔ ወይስ ዲያኣስፖራ።
እርስዎ በኤርትሪዊነትዎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ  1.9 GPA አግኝተው መግባት ሲፈቀድልዎ አማራዉና ሌላው ህብረተሰብ 2.2 GPA ካላመጣ የዩኒቨርሲቲ በራፍዋን ይረግጥም ነበር። ታዲያ ይህ አማራ ነው ሲጨቁን የኖረ። ይህነው ነፍጠኝነት። ለኀይለሥላሤ መንግሥስት ዕድሜ መለመን የነበረባችሁ አናንተ መሆን አልነበርባችሁም።
ከሃገሪቱ የቀላልና የከባድ ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ 45% በአስመራ አልነበረምን። ከፒአሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር፤ከመርካቶ እስክ ኮተቤ፤ከብሄራዊ ቲአትር እስከ ደብረዚይት ይምግብ ቢቶችን፤የአልባሳትና የወርቅ መሸጫ ሱቆችን፤ ቡናና ሻሂ ቢቶችን፤ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በአብዛኛው በኤሪትራዊያንና በወያኔ የተያዙ አይደሉምን። ማነው ኤርትራኖች ናቸው ትግሬዎች ናቸው ብሎ የጠየቀ። ይህ ሁኔታ በኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ ጊዘ የነበር ሃቅ ነው። በርስዎና በወንበዴው ድርጅትዎ አማካይነት አማራውን፣ ኦረሞውን፣ ጉራጌውን፣ ቤንሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ከምባታውን፤ሃድያውን፤ ሲዳማውን ወዘተ በጎሳው እያሳደዳችሁ የምታፈናቅሉና በሃገሩ ሰርቶ አንዳይኖር የምታደርጉ የመንግሥስት ቀማኞች አይደላችሁምን። ከዚህ የበለጠ የሃገር ትቅምን፤አንድነትንና እድገትን የሚጎዳ ነገር ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራው ይህን ሰርቶአል ካሉ ከነማስረጃዉ ያቅርቡልንና እንተማመን።እኛ እስከምናዉቀዉ ዲያስፖራ ያደረገው ይህን እኩይ ተግባራችሁን የተቃዉሟል። ዲያስፖራው  አገርን ከጥፋትና ከዉድመት ለማዳን የሚንቀሳቀስ ይመስለናል ።
አማራው ኦረሞው ወዘተ ልዩ ተጠቃሚ አንደሆነ አድርጋችሁ በመንግሥት ፕሮፖጋንዳ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ፣ በቡድን፤ እንዲሁም መዋቅርና መመሪያ ዘርግታችሁ የጥላቻ ዘር የምትዘሩና የምታናፍሱ አናንተ አይደላችሁም። በመንግሥት አዋጅና መመሪያ የሃገርን ጥቅም እያፈረሰ አገር ማስገንጠሉ አንሶ መሬት እየቆረሰ ለሱዳንና ለሶማሊያ በእጅመንሻነት የሚሰጥ ማን ሆነና ነው ዲያስፖራዉ የሚወቀሰዉ። ነፃነት ባለበት ሃገር ስለሚኖር እኩይ ተግባራችሁን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይቃወማል ለዓለም ህዝብም ያስረዳል። ይህ የሃገርን ጥቅም ማጥፋት ነው የሚባል ከሆነ ዲያስፖራው በጸጋና  በኩራት የሚቀበለው ወቀሳ ይሆናል።ይሄ ሁሉ ሃቅ ማይከብድዎት ቢሆን የተሸከሙት የዶክትሬትና የመንግስት ስልጣንና ህሊናዎ እንዴት አይወቅስዎትም ።
ተፋቅሮ ፤ ተጋብቶ፤ተዋልዶ በአንድነት የኖረውን ህዝብ በዘር ሃረጉ በቁዋንቁው እየለያችሁ ለማተራመስ ድፍት ቀና የምትሉ እርስዎና ግብረአበሮችዎ አይደላችሁም እንዴ። ክዚህ የበለጠ የአገረ ጥቅምን ማፈራረስ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራውማ ተው ይህ ትክክል አይደለም አገረ ይበተናል፤ የአገር ጥቅም ይጎዳል እያለ ይጮሃል ።  የማንኛው ተግባር ነው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳው። ፍርዱን ለርስዎና ለቡድንዎ ከመተው ሌላ አምራጭ የለም።
በቤንሻንጉል፤በጉራፈርዳ፥ በአፋር፥ በኦረሞ ወዘት በመሳሰሉት ክልሎች እና አካባቢወች አማራውን፤ኦረሞውን፣ ጉራጌውን አፋሩን፣ አኝዋኩን እየነጠላችሁ የምታፈናቅሉ፣ ንብረቱን በመንግስት መምሪያና ልዩ ትእዛዝ የምትቀሙ ህጋዊ ቀማኞች አርስዎና ቡድንዎ አይደሉምን። የሃጋሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ይዛችሁ ኣብዛኛውን የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቁኣማትን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደራጃ ይዛችሁ ይህን ሁሉ ግፍና ኢሰበአዊ ድርጊት በንፁሃንና ሰላማዊ ዜጎችና በሃገሪቱ ላይ የምታዘንቡት ምን ለማትረፍ ነው። እርስዎና ግብረአበሮችዎ የምትፈጽሙት ወንጀልና ግፍ ሞልቶ ከፈሰሰ ውሎ አድሮኣል። አገሪቱ በግፋ ጨቅይታ ልትፈራርስ ተቃርባለች።የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚፈታተን ተግባር አየፈጸማችሁ ዲያስፖርውን የሃገር ጥቅም አፍራሽ አድርጋችሁ ራሳችሁን እንደጲላጦስ ከደሙ ነፃነን ልትሉ ትፈልጋላችሁ። እንደርስዎ ያለ ተማርሁ የሚል ሰው ሎጂክና ፕሪንሲፕለ ትቶ ደም ከውሃ ይወፍራል አያል ዘር የማጽዳት ዘመቻ ሲካሄድ ጀሮዳባልበስ አያለ የሚጎዝ ምንዓይነት ህሊና ነው።
ኤርትራን ያስገነጠላችሁ አናንተ በሁአላም ከኤርትርዊያን ጋር ጦርነት ከፍታችሁ ህዝቡን ያስጨፈጨፋችሁ አናንተ።  እምቢ ላገሬ  እምቢ ለነፃነቴ ብሎ የዘመተውን አማራ ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ጉርጋጌ፤ ሲድማ፣ ከምባታ ወዘተ ከፊትለፊት አሰልፋችሁ ከ 70-100,000 ሕዝብ አላስጨረሳችሁም አንዴ። ሕዝቡ በደሙ ያስቀራትን ባድመን መልሳችሁ ለሻብያ አልሰጣችሁምን። በዛንጊዜ ኤርትራኖችን ከኢትዮጵያ ምድር ንብረታቸውን ቀምታችሁ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ወደ አስመራ አልመለሳችሁምን።
አሁን ደግሞ አነዚህኑ ኤርትራኖች ከአስመራ ወደ ኢትዮጵይ አንዲመለሱ አድርጋችሁ በመንግሥት መስሪያ ቤት አንዲመለሱ፣ ንብረታቸው ከነወለዱ አንዲመለስ አላደረጋችሁምን። ማነው በኢትዮጵያ ህዝብና ንብረት ላይ አየቀለደ የሚገኘው። ይህ ሁሉ ተግባር የሃገር ጥቅምን መጉዳት አይደለምን። ለነገሩ በአመራር ላይ ያላችሁት አብዛኞቻችሁ ኤርትራኖች ስልሆናችሁ የኢትዮጵያን ጥቅም ታስተብቃላችሁ ተብሎ አይጠበቅም። ዲያስፖራው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳ ነገር እንዳይሰራ ታስጠነነቅቃላችሁ። የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብያደርቅ ማለት ይህ ነዉ።
በስልጣን ወንበር ከትቆናጠጣችሁ በሁአላ እንደ መንግሥት ሀገ መንሥት ኣወጣችሁ። ማንም ሳይጠይቃችሁና ሳያስገድዳችሁ እናምንበታለን ብላችሁ ያወጣችሁትን ሀገመንግሥት አንድ አራተኛወን እንኹዋን በተግባር አልፈፀማችሁም ። በሃገራችን ታሪክ ኢትዮጵያ ያለህግ የምትተዳደርው ክ1991 ዓማተ ምህረት ጀምሮ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለህግ ተገዥ የነበረን ህዝብ ወደኾላ አየወሰዱ በህግ አልባ ስርዓት ከማስተዳደር የበለጠ ወራዳ ስራና ሕገአራዊትነት ምን ሊኖር ይችላል።ከዚህ የበለጠ የሃገረንና የህዝበን ጥቅም የሚጎዳና የሚአፈርስ ምን ነገር ይኖራል ።
በቅርቡ ወደ ሃገርቤት ጎራ ብዬ ሃገሪቱን በሰፊው አይቸ ተምልሻለሁ። እርግጥ ነው ሕንጻ ተቆልልዋል መንገድ ተሰረቶአል፤ የዝቅተኛና የከፍተኛ ትምህርት ቤቶችና  ተቐማት እንዳሸን ፈልተዋል፤ ጤና ጣቢአወች ተሰርተዋል፤ የመብራትና የስልክ መስመሮች ተዘርግተዋል፤ የውሃ ቡአንቡወችና የስልክ መስመሮች ጨምረዋል። ይህን ስናይ እሰየው እንላለን። የሚገርመው የሚጠጣ ውሃ የለም፣ ህዝቡ የኤሌክትሪክ መብራት አጦ በሻማ ያመሻል፣ ተማሪወች ከከፍተኛ ትምህርት ተቅዋማት ተመርቀው በቅጡ ስማቸውን መጻፍ አይችሉም ተመርቀውም ቦዘኔ ናቸው፤ምርት ተመርቶ ህዝብ ፆሙን ያድራል። ሁልጊዜ በግብረሰናይ ድርጅቶች እርዳታ ከመጠየቅ አልወጣም።ጤና ጣቢወች ተሰርተው ባልሙያወች የሉም ህዝቡ በበሽታ ይሰቃያል።
ሖስፒታሎቻችሁ የመፀዳጃ ቤት ይመስላሉ።እንዲአውም በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች በሃገር ቤት ካሉት ሆስፒታሎቻችሁ በንጽህና ሳይሻሉ አይቀሩም። የጎዳና ተዳዳሪው ቁጥር በየቀኑ ይጨምራል አሁንማ የመንግሥት ሰራተኛውም ተረጂ ሆንዋል። የዛሬ ሃይ ዓመት 85% የሆነው ህዝባችን በቀን ከ$1 ዶላር በታች በሆነ ገቢ ይኖር ከነበረበት ዛሬም የተቀየረ ነገር የለም። የትላይ ነው የ 11% ኢኮኖሚ እድገቱ። መቸም ምሁሩና ዶክተሩ አድሃኖም ይህን እውነታ በቀላሉ የመረዳት አቅም ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ግዴታም ስላለባችሁ ይህን ሃቅ ያስተባብላሉ ብለን አንጠብቀም።
የሃገር ቅርስና ታሪክ የሃይማኖት ትቁዋማትን፤ ባህልንና ታሪክን ማጥፋት የሃገርን ጥቅምና ማንነት ማጥፋት አይደለምን። ማነው የእስላሙን ህብረተሰብ ከኦርቶዶክሱ ጋር የሚአናቁር። ሌላዉ ቢቀር ከዛሬ ሽሕ ዓመት በፊት ባሕረ ነጋሽ ወይም ነጋሺ የሰራውን እንኩአን ማሰብ እንዴት ያቅታችሁኣል። ማነው አማራውንና ኦርቶዶክሱን እንዳይንሰራራ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብሎ በኦፊሲየልና በመገናኝ ብዙሐን ወጦ በዝና መልክ እያወራ ያለው። ከዚህ የበለጠ የሃገረ ጥቅምንና አንድነት ማጥፋት የበለጠ ምን ይኖራል ይላሉ። አገር ከፈረሰ እኮ አማራውና ኦሮሞው ብቻ አይደለመ የሚጠፋው እንናንተም ጭምር መሆኑ እንዴት አይታያችሁም። የሌሎች ጉአደኞችዎ አርቆ የማሰብ አድማስ የተወሰነ ቢሆን እንደርስዎ ያለ ምሁር እንዴት አደጋዉ አይታየዉም።  ይህን ከመሰለ  የሃገር ጥቅምን ማወደም የበለጠ ምንሊኖር ይችላልና ነው ዲያስፖራውን የምትወቅሱት።
በሃገርቤትና በውጭ ሃገር ያለው ተቃዋሚና ህዝብ በተደጋጋሚ የሚአቀርበው ጥያቄ  የብሔራዊ እርቅንና ሠላምን የአንድነት መንግሥት እናቕቁም እያለ ሲለፍ ይኸው ሃያ ሁለት ዓመት አስቆጠረ። ይህን የተቀደሰ ሃሳብ በእምቢተኝነቱ ፀንቶ የሚገኘው ማነው ። ሃገርን ለአንድነትና ለትብብር የጠራ ተቃዋሚን ዲያስፖራ እንደሽብርተኛ የሚቆጥር  መንግሥትና ዶክትሬት ምን ዓይነት ጭንቅላትና መሪ ነው። ዶር አድሃኖም አሁንም ጊዜ አለ አልመሸም ማስተካከል ይቻላል። ከርስዎና ከግብረአበሮችዎ የሚፈለገው ቅን ልቦናና ለሃገር ጥቅም አስቦ መንቀሳቀስ ነው። ለጥፋቱ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም ሃላፊነት ወስዶ ለማስተካከል መስራት ይኖርበታል። ሐላፊነቱ መንግሥት ነኝ በሚለዉ ላይ የከበደ ነዉ።
ሕዝብና ኢግዚአብሔር ሁሉጊዜ ይቅር ባዮችናቸዉ። የሃገር ጥቅም ማጥፋቱን አቁማችሁ የሃገር አንድነትና ጥቅም ማስጠበቅን ቅድሚያ ሰጣችሁ ከሕዝብ ጋር ታረቁ።  ካልሆነ ሃገር አገር ሲአርጅ አሜኪላ ይወልዳል እያልን ተቃውሞኣችንን እንቀጥላለን። ለዶ/ር አድሃኖም ካልነቁ መንጋቱን የሚኣበስር መልክተኛ አንልክባቸዋለን።
ቸር ይግጠመን
ዓቢቹ ነጋ ነኝ

No comments:

Post a Comment