Saturday, May 11, 2013

የግምሩክ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትሉ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ በዛሬው እለት በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

(EMF) – በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ እና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ በዛሬው እለት በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሁለቱ በሙስና የታሰሩት ባለውልጣናት የግምሩክ ዳይሬክተር እና ምክትል ዳይሬክተሮች ናቸው። አቶ መላኩ ፈንታ ትውልድ እና ዕድገታቸው በጎንደር ከተማ ሲሆን፤ ስብሰባ ሄደው አያውቁም እንጂ፤ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ናቸው። ባለፉት አመታት የኢህአዴግ ታማኝ አገልጋይ በመሆን የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር ደኤታ ሆነው አገልግለዋል። አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ደግሞ የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፤ በሙያ ችሎታ ሳይሆን በህወሃት አባልነታቸው ስልጣን እንዳገኙ ተደርጎ ሲነገር ነበር የቆየው።
(Left to right) Gebrewahed Deputy director and  Director Melaku Fenta
(Left to right) Gebrewahed Deputy director and Director Melaku Fenta
ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የሙስና ምንጮች ተብለው ከተጠቀሱት 3 ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋናነት ሲጠቀስ ቆይቷል። ይህ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ታክስ በነጋዴው ላይ በመጨመር ህብረተሰቡን ሲያማርር የቆየ ሲሆን፤ ሌሎችን በሙስና በመክሰስ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከ6 ወራት እስከ 25 አመት በሚቆይ እስር እንዲፈረድባቸው ማድረጋቸው ይታወሳል። ከነዚህ ውስጥ በርግጥ በጥፋት የታሰሩ ቢኖሩም፤ ምንም ያላጠፉ እና የኢህአዴግን አስተዳደር ያልደገፉ፤ መዋጮ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያላደረጉ ሰዎች ሆን ተብሎ ከፍተኛ ታክስ ተጨምሮባቸው፤ መክፈል ባለመቻላቸው ጭምር ለእስር የተዳረጉ አሉበት።

እስካለፈ አመት ድረስ የግምሩክ ባለስልጣን ከ3 ሺህ በላይ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነበር። አሁን የተሰማው አዲስ ወሬ እና ዜና ግን በተለይ የንግዱን ህብረተሰብ ያስገረመ ነገር ሆኗል። በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ እና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እንዲሁም ከነሱ ጋር በመተባበር ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ 15 የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
እንደደረሰን ዘገባ ከሆነ የግለሰቦቹ ቤት፣ ቢሮ ተበርብሯል። በስልክ እና በኢሜይል ሲያደርጉ የነበረው ግንኙነት ጭምር በህወሃቱ አቶ ደብረጽዮን የኤሌክትሮኒክስ ስለላ ስር ወድቆ ነበር። እናም መቆየት ደግ ነው “ኢህአዴግ ልጆቹን መብላት ጀመረ” የሚያሰኝ ወቅት ላይ ተደረሰ።
http://ethioforum.org/

No comments:

Post a Comment