ዳዊት ታዬ /ሪፖርተር
የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በያዘው መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት ያላቸው የግል ባንኮች አካውንታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ታገዱ፡፡

ከአንዳንድ የግል ባንኮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ያላቸውን አካውንት እንዳያንቀሳቅሱ የተገለጸላቸው፣ አካውንታቸው ባለበት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ዕርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሰኞ መስከረም 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበራቸውን አካውንት ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑ እንደተገለጸላቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የግል ባንኮች ኃላፊዎች እንደጠቆሙት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕርምጃ ያልተጠበቀ እንደሆነባቸው ነው፡፡ ‹‹ሆኖም የእኛን የተወዳዳሪዎቹን አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢያንስ ምክንያቱን ሊገልጽ ይገባ ነበር፤›› ይላሉ፡፡ የግል ባንኮቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት የከፈቱበት ዋነኛ ዓላማ አንዳንድ ክፍያዎችን በቀጥታ ከዚያ ለመክፈል እንዲያስችላቸው እንጂ ሌላ ዓላማ የሌለው መሆኑን የግል ባንኮች ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡
አንድ ባንክ በሌላ ባንክ ውስጥ አካውንት ሊከፍት የሚችለው በሥራ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸምና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ነው በማለት የሚያስረዱት የግል ባንኮች ኃላፊዎች፣ ይህ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለመደ አሠራር ቢሆንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደዚህ ዕርምጃ መግባቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት 19 ባንኮች በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ሦስቱ የመንግሥት 16ቱ ደግሞ የግል ናቸው፡፡ የግሎቹም ሆነ የመንግሥት ባንኮች በጥምረት የሚያስተሳስራቸው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰደውን ዕርምጃ በማኅበራቸው በኩል ለመነጋገር ሐሳብ ያላቸው መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ ወሰነ ማለት ግን በአካውንታቸው ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያግዳል ማለት እንዳልሆነ ተጠቅሷል፡፡
አንዳንዶቹ የግል ባንኮች አካውንቱ ለምን እንዲታገድ እንደተደረገ ላቀረቡት ጥያቄ ማብራሪያ ባለማግኘታቸው በሁኔታው ማዘናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዳንድ ኃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ካለመሳካቱም በላይ፣ በሞባይል ስልካቸው በጽሑፍና በድምፅ የተላለፈላቸውን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7492የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ዕርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሰኞ መስከረም 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበራቸውን አካውንት ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑ እንደተገለጸላቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የግል ባንኮች ኃላፊዎች እንደጠቆሙት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕርምጃ ያልተጠበቀ እንደሆነባቸው ነው፡፡ ‹‹ሆኖም የእኛን የተወዳዳሪዎቹን አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢያንስ ምክንያቱን ሊገልጽ ይገባ ነበር፤›› ይላሉ፡፡ የግል ባንኮቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት የከፈቱበት ዋነኛ ዓላማ አንዳንድ ክፍያዎችን በቀጥታ ከዚያ ለመክፈል እንዲያስችላቸው እንጂ ሌላ ዓላማ የሌለው መሆኑን የግል ባንኮች ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡
አንድ ባንክ በሌላ ባንክ ውስጥ አካውንት ሊከፍት የሚችለው በሥራ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸምና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ነው በማለት የሚያስረዱት የግል ባንኮች ኃላፊዎች፣ ይህ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለመደ አሠራር ቢሆንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደዚህ ዕርምጃ መግባቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት 19 ባንኮች በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ሦስቱ የመንግሥት 16ቱ ደግሞ የግል ናቸው፡፡ የግሎቹም ሆነ የመንግሥት ባንኮች በጥምረት የሚያስተሳስራቸው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰደውን ዕርምጃ በማኅበራቸው በኩል ለመነጋገር ሐሳብ ያላቸው መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ ወሰነ ማለት ግን በአካውንታቸው ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያግዳል ማለት እንዳልሆነ ተጠቅሷል፡፡
አንዳንዶቹ የግል ባንኮች አካውንቱ ለምን እንዲታገድ እንደተደረገ ላቀረቡት ጥያቄ ማብራሪያ ባለማግኘታቸው በሁኔታው ማዘናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዳንድ ኃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ካለመሳካቱም በላይ፣ በሞባይል ስልካቸው በጽሑፍና በድምፅ የተላለፈላቸውን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment