Monday, September 30, 2013

ቆይ ግን እኔ የምኒሊክ 'አድናቂ' ነኝ እንዴ? ባጋጣሚ ስለ አፄ ምኒሊክ ጥሩም መጥፎም ፅፌ አላውቅም። ግን ብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የምኒሊክ አገዛዝ እንደምደግፍ አድርገው ለህዝብ ይነግራሉ። የፌስቡክ ጓደኛዬ ዳንኤል ብርሃነም "የምኒሊክ ቲፈዞነትህ ለማስቀጠል ከፈለክ የሱ ወራሾች የሆኑ 'አንድነቶች' (ፓርቲው መሆኑ ነው) አሉልህ፤ ከነሱ ጋር ተቀላቀል" የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠኝ። የህወሓት ደጋፊዎች ከምኒሊክ ጋር የሚያገናኙኝ ምናልባት ህወሓት ስለምቃወም ይሆን? ወይስ እንደነሱ 'ሸዋ አማራ ጠላታችን ነው' ብዬ አለመፃፌን ነው? ህወሓትን መቃወም ከምኒሊክ አገዛዝ ጋር ምን ያገናኘዋል? ግን'ኮ ህወሓቶች በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙት ስትራተጂ 'ከፋፍለህ ግዛ' ነው። 'እኛና እነሱ' ብለው ይከፋፍላሉ። በዚህ መሰረት 'ህወሓት ከተቃወምክ የሸዋ ፖለቲከኞች ትደግፋለህ ማለት ነው' ይሉሃል። ቆይ የሸዋ ፖለቲከኞች ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም ማለት ነው? በዚህ አጋጣሚ ስለ ምኒሊክ ስርዓት ያለኝ አመለካካት ላካፍላቹ። (ፖለቲከኛ ጠንቃቃ መሆን አለበት ይባላል፤ ግን እኔ ፖለቲከኛ ነኝ እንዴ? የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆነ ሁሉ ፖለቲከኛ ነው ብዬ አላምንም)። በኔ መነፅር የምኒሊክ ስርዓት እንደማንኛውም ዘውዳዊ አገዛዝ ነው። በንጉሳዊ ስርዓት 'ዙፋኑ ይመለከተናል' የሚሉ መሳፍንት ሁሉ ዘውዱን ለመጫንና ግዛቶችን ለማስፋፋት ጥረት ያደርጋሉ። ለግል ስልጣናቸውና ግዛታቸው የሚያግዛቸው ተግባር ሁሉ ያደርጋሉ። ከህዝቦች ነፃነት በላይ ስልጣናቸው ያስቀድማሉና። ሁሉም ለስልጣንቸው አደጋ የሚደቅን ግለሰብ ምህረት የላቸውም (የፈለገ ዘመድ ቢሆን)። በዚህ ልክም ሀገራዊ ራእይ የነበራቸውም አይጠፉም። ሁሉም መሳፍንትና ነገስታት ዘውዱን ለመጫን ብዙ ግፍ ፈፅመዋል። ያለፈ የንጉሳውያን ታሪክ እያስታወሱ መወቃቀስ ላሁኗ ኢትዮዽያ አይጠቅምም የሚል እምነት አለኝ። 'ዮሃንስ እንዲህ አለን፣ ምኒሊክ እንዲህ አደረገን' እየተባባልን ግዜያችን ባናጠፋ (ለዚህም ነው ስለነዚህ ታሪክ መፃፍ የማልፈልገው)። አንዳንድ የሚፃፉ ነገሮች ግን ይገርሙኛል። 'ምኒሊክ ለትግራይ እንዲህ አለ፣ ለኦሮሞዎች እንዲህ አደረገ' ሲባል . .. እና ምን? ምኒሊክ የሰራው ነገር ለስልጣኑ ሲል ነው። ዮሃንስም እንዲሁ፣ ቴድሮስም እንዲሁ። ለስልጣናቸው ሲሉ መጥፎ የሰሩትን ያህል ጥሩ ነገርም ሰርተው ይሆናል። በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት መዓት ችግሮች ሰርተው ይሆናል። ግን ምኒሊክ ለሰራው ነገር አሁን ላሉ የሸዋ አርሶ አደሮች፣ ዮሃንስ ለሰራው የአሁኑ ተምቤኖች፣ ቴድሮስ ለሰራው የአሁኑ ጎንደሬዎች፣ ህወሓት ለሰራው የአሁኑ ትግራዮች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም። ምኒሊክ የዮሃንስን ዘውድ ለመያዝ የተጠቀመው ስልት (ጥሩም መጥፎም) በመጥቀስ የሸዋ ሰዎች ለትግራይ ሰዎች መጥፎና ጠላቶች ማረጋገጫ አድርገን መፃፍ ተገቢ አይደለም። አፄ ቴድሮስ የጎጃም መሳንፍት ጠራርጎ ሲያባርር አንድም ለስልጣኑ አልያም ደግሞ ለሌላ ጥሩ ነገር ነበር እንበለው። በዚህ ጉዳይ እርግጠኞች መሆን አንችልም። መከራከር ቢቻልም። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን፤ ቴድሮስ መሳፍንቱን ሲያባርር መሳፍንቱ ትግሬ ወይ ኦሮሞ ወይ አማራ ወይ ሌላ ሰለነበሩ አይደለም። ዮሃንስም የቴድሮስን ዙፋን ለመጨበጥ የተለያዩ ስልቶች ተጠቅሞ ይሆናል። ለምን አደረገው ብለን ብንጠይቅ ... ለስልጣኑና ለሌላም ሊሆን ይችላል። አንድ ሓቅ ግን አለ። ዮሃንስ ቴድሮስን ስልጣን መቀማት የፈለገው ቴድሮስ ጎንደሬ ስለነበር (ወይ ትግራዊ ስላልነበረ) ግን አይደለም። በተመሳሳይ መልኩ ምኒሊክም እንደማንኛውም ንግስና ፈላጊ የዮሃንስ ዙፋን ለመውረስ የተለያዩ ስልቶች ተጠቅሞ ይሆናል (የተጠቀመው ስልት ጥሩ ወይ መጥፎ ሊሆን ይችላል፣ እንደ አመለካከታችን ይለያያል)። ግን ምኒሊክ ይሄን ነገር ሲያደርግ ስልጣኑንና ፖለቲካዊ ዓላማውን እያሰበ እንጂ ብሄር እየቆጠረ አይመስለኝም። ምክንያቱም ነገስታት ለንግስናቸው ሲሉ የራሳቸው ብሄር ተወላጆችም ሲገድሉ ነበር። በዚህ መሰረት ቴድሮስ ከትግራይ ቢሆን ኑሮ ዮሃንስ የዙፋን ተቀናቃኝ አይሆንም ነበር ማለት አንችልም። የትግራይ መሳፍንት'ኮ እርስበርሳቸው ተፋጅተዋል። ዮሃንስ ከሸዋ ቢሆን ኑሮ ምኒልክ ለዮሃንስ ጥሩ ይሆን ነበር ብትሉኝ አላምናችሁም። ቆይ! በላይ ዘለቀ በሃይለስላሴ የተገደለው ትግሬ ስለነበረ ነው እንዴ? ደርግ የሃይለስላሴን ስርዓት የተቃወመው ትግሬ ስለነበረ ነው እንዴ? ህወሓት ኢዲዩን ያጠፋው ኢዲዩ የሸዋ ስለነበር ነው እንዴ? አይደለም። እኔም ህወሓት የምቃወመው ህወሓት ከትግራይ ስለሆነ ወይ ስላልሆነ አይደለም፤ የምኒሊክ ስርዓት ናፋቂ ስለሆንኩም አይደለም። ከህወሓት አገዛዝ የተሻለ ሌላ ስርዓት ማየት ስለምፈልግ ነው። ስልጣን ወደ ህዝብ ወርዶ ማየት ስላማረኝ ነው። ሁሌ ህዝብና ፖለቲከኞች ለያይተን ማየት ይኖርብናል። ምኒሊክ ለዮሃንስ የስልጣን ተፎካካሪ (የስልጣን ጠላት) ስለነበረ የትግራይና የሸዋ ሰዎች ጠላት መሆን አለባቸው በሚል ሓሳብ አልስማማም። ምኒሊክ ሌላ የሸዋ ህዝብ ሌላ፤ ህወሓት ሌላ የትግራይ ህዝብ ሌላ።

Abraha Desta

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)

Temesgen Desalegn
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በምርጫ 2002ቱ ማግስትም ድርጅቱ አቦይን ‹‹በክብር›› እንዲሸኝ ሲደረግ፣ ፀጋዬ በርሄን ደግሞ ‹‹አማካሪ››  በሚል ሽፋን ከመቀሌ ወደ ቤተ-መንግስት (ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ) አዛውሮ በቅርብ እይታ ስር በማዋሉ ሁለቱንም ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡ በግልባጩ አዜብ መስፍንና ‹የመለስ ታማኞች› የሚባሉት እነአባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስ የፖሊት ቢሮውን ተቀላቅለዋል፡፡ ሁነቱም ከእነአቦይ ጋር በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩ ባለስልጣናትን በማስከፋቱ በድርጅቱ ውስጥ ብቻ የሚታወቅ (አደባባይ ያልወጣ) ልዩነት ፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል (በነገራችን ላይ ኦህዴድ የማዳከሙ ሴራ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ ከመለስ ህልፈትም በኋላ ቀጥሏል፤ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት የግንባሩ አባል ድርጅቶች፣ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ብአዴን በ‹ክብር›  ካሰናበተው ሁለት ዓመት ያለፈውን መሪውን አዲሱ ለገሰን ወደ ቦታው መልሶ ራሱን ሲያጠናክር፣ በተቃራኒው ኦህዴድ አንጋፋ አመራሮቹን፡- አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳና ግርማ ብሩን ከስራ አስፈፃሚነታቸው እንዲያነሳ ተገድዷል፡፡ ይህንን ነው መተካካት የሚሉትም፡፡
ህወሓት
የመለስን ህልፈት ተከትሎ በውስጡ ያደፈጠው ቅራኔ ፈንቅሎ በመውጣቱ ህወሓትን የ‹መቀሌው› እና የ‹አዲስ አበባው› በሚል ለሁለት ከፍሎት ነበር፤ ይህ ግን የመቀሌው-በአዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባው-በመቀሌ ደጋፊ አልነበረውም እንደማለት አይደለም (የመቀሌውን አዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሀጎስ… መርተውታል፤ የአዲስ አበባውን ደግሞ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ዘውረውታል)፡፡ ይህ አጋጣሚም ከእነ አዜብ ቡድን ጋር ትብብር የፈጠረውን ብአዴንን ለጊዜያዊ ድል አብቅቶት ነበር (በ93ቱ ክፍፍልም የብአዴን ድጋፍ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጣ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱ ይታወሳል)፡፡ አቦይ ስብሃት ነጋ በትግርኛ ቋንቋ በሚታተመው ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ ‹‹ህዝቢ ትግራይ ዘቃልሶ ኣቃሊሱ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ይግብኦ›› (የትግራይ ህዝብ የሚያታግለው፣ ታግሎም የሚጠቅመው ወያኔያዊ ድርጅት ይገባዋል)  በሚል ርዕስ በፃፉት ፅሁፍ ችግሩን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡-
‹‹አባይ ወልዱም ባለፈው የህወሓት ጉባኤ ላይ በተደጋጋሚ ‹ህወሓት ውስጥ ማጠለሻሸትና (የሥልጣን) ሽኩቻ በስፋት እየተስተዋለ ነው›  በማለት ሁኔታውን ገልፆታል፡፡ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ ደግሞ የለም፡፡ እንዲህ ያለ በኃይል አሰላለፍ ደረጃ ሊታይ የሚችል የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አቅም ከማዳከምና መርሀ-ግብሩን ከማሰናከል አልፎ ተርፎም ድርጅቱን ለአስከፊ ውድቀት ሊጥል ከሚችል አደገኛ ሁኔታ የበለጠ አደጋ ያለ አይመስለኝም፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሐሴ 2005 ዓ.ም
ከኃይለማርያም ጀርባ
ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንባሩ ሊቀ-መንበር በመሆኑ ጉዳይ ላይ ብአዴንም ሆነ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ቅሬታ አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እርሱም ሆነ ‹ደቡብን እወክላለሁ› የሚለው ድርጅቱ ለአሸናፊ ኃይል ከማገልገል አልፈው የፖለቲካ አመፅ ሊያስነሱ እንደማይችሉ ይታወቃልና፡፡ ይሁንና በወቅቱ ኃይለማርያም ሰልፉን በ‹መለስ ባርኔጣ› ከሚንቀሳቀሰው ከመቀሌው ህወሓትና ብአዴን ጋር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝበማስተካከሉ የኃይል ሚዛኑ በአንፃራዊነት ወደእነርሱ እንዲያጋድል አድርጓል፡፡ በግልባጩ ለእነ አቦይ እና ደጋፊዎቻቸው የመሸነፍ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እንግዲህ እስከ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ድረስ ‹መልከ-ኢህአዴግ› በዚህ መልኩ ነበር የቀጠለው፡፡
 ‹መፈንቅለ-ህወሓት›
ብአዴኖች፣ ከመቀሌው ህወሓት ጋር የፈጠሩትን ግንባር፣ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ካገኙት ድጋፍ ጋር በማዋሀድ፡- የአዲስ አበባውን ህወሓት የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ፣ የደህንነት ሀላፊው ጌታቸው አሰፋን እና አንጋፋ የህወሓት ታማኝ ጄነራሎችን ከመንግስታዊውም ሆነ ከፓርቲው ኃላፊነታቸው በማንሳት በአሸናፊነት ለመወጣት ስልታዊ እንቅስቃሴ አድርገው እንደነበር ለድርጅቱ ቅርብ ከሆነ ሰው አረጋግጫለሁ፡፡ በባህርዳሩ ጉባኤ ላይም መላኩ ፈንቴ ‹አላሰራ አሉኝ› ብሎ በአደባባይ እንዲያጋልጣቸው ከተደረጉት የንግድ ደርጅቶችና ሀብታም ነጋዴዎች አብዛኞቹ ከአዲስ አበባው ህወሓት ጋር የተሳሰሩ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ነው ‹መፈንቅለ-ህወሓት› ለማለት የተገደድኩት፡፡ ሴራው የከሸፈው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል፤ የመጀመሪያው በሰውየው ህልፈት ማግስት (ተተኪው ጠቅላይ ሚንስትር ገና ባልተመረጠበት) እነአባይ ፀሀዬ ሶስት ሜጀር ጄነራል እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎች (አብዛኞቹ የህወሓት ሰዎች ናቸው) መሾማቸው ኃይላቸውን ሲያጠናክርላቸው፣ በአንፃሩ የመቀሌውን ህወሓትና ብአዴንን በሠራዊቱ ውስጥ የነበራቸውን ተፅእኖ ከማዳከሙም በላይ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫቸውንም ገትቶታል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በደህንነት
መስሪያ ቤቱ አቀናባሪነት በ‹ፀረ ሙስና› ሽፋን የተከፈተው ዘመቻ ነው፤ እነበረከትንም ስልታቸውን መልሰው እንዲያጤኑ ያስገደዳቸው ይህ አይነቱ አስደንጋጭ እርምጃ ይመስለኛል፡፡
የህወሓት ‹ቆሌ›
የኢትዮጵያን ልማዳዊ ፖለቲካ ከነሴራው ጠንቅቀው ከተረዱት ጥቂት ሰዎች መሀል አቦይ ስብሃት ነጋ አንዱ መሆናቸው ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ አቦይ ህወሓትን ጠፍጥፎ በመስራቱም ሆነ በስልጣን ለማቆየት የመለስን ያህል (ሊበልጥም ይችላል) ለፍተዋል፡፡ ዛሬም ተፈጥሮ ላመጣባቸው እርጅና እጅ ሳይሰጡ በህወሓት ላይ የሚሴረውን-ለመበጣጠስና ለተቀናቃኞቻቸው-ጉድጓድ ለመቆፈር እንደማይሳናቸው አሳይተዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው ‹የህወሓት ቆሌ› የሚል ቅጥያ ያሰጣቸው፡፡
ከመለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው ጥብቅ የመተባበር መንፈስም ከጓዳዊነትም በላይ እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ ግና ይህ የጦፈ ፍቅራቸው ከ2000 ዓ.ም ወዲህ መደብዘዝ ጀምሮ ነበር፤ ልዩነታቸውም ቅስ በቀስ እየሰፋ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ አንዱ መለስ፣ ለአዜብ መስፍን እየሰጠ የነበረውን የፖለቲካ ጉልበት፣ አቦይ ‹ህወሓትን በሴት ቀሚስ እንደማሳደር› አድርገው መውሰዳቸው ነበር፡፡ ሌላው የሴቲቱ ኃይለኝነት የአቦይን የተሰሚነት ክልል ከመፈታተን አልፎ በአደባባይ ክብራቸውን እስከ መዳፈር መድረሱ ይመስለኛል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም ከመለስ ጋር ተገናኝተው መነጋገር አልቻሉም፤ ለህወሓት ቅርብ የሆኑ ወዳጄ እንደነገሩኝ መለስ ህይወቱ ሲያልፍ አቦይን ካገኛቸው ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፤ ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ማግኘት ባለመፈለጉ ነበር፤ ይህም ሆኖ አቦይ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም በልዩ ረዳቱ አማካኝነት ‹አስቸኳይ ጉዳይ ላይ ነው› እያስባለ መልሷቸዋል፤ በስራ አጋጣሚ ከቢሮ ውጪ ሲገናኙም ‹አጣዳፊ ስራ ስለተደራረበብኝ ነው፤ እኔ ራሴ አስጠራሀለሁ› እያለ ለሁለት ዓመት ያህል ሲርቃቸው ከቆየ በኋላ ነበር ድንገት ህይወቱ ያለፈው፡፡
አቦይ ወደ ህወሓት ተመልሰው በንቃት መሳተፍ የጀመሩት የመለስን ጤንነት ሲከታተሉ የነበሩ ሐኪሞች ‹ተስፋ የለውም› ባሉበት ማግስት ነበር፤ እንደምክንያት ያስቀመጡት ህወሓት ከድህረ-መለስ በኋላ፣ የብአዴንን የትከሻ ግፊያ መቋቋም አይችልም የሚል ስጋትን ነው፡፡ የሰውየው መጨረሻ ከታወቀ በኋላም የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ የታየው የኃይል ሚዛን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ በወቅቱም አቦይ ‹መፍትሄ› ብለው ያቀረቡት ‹ብአዴንና ከጎኑ የተሰለፉትን የህወሓት የአመራር አባላትን ማሸነፍ ስለማንችል፣ አንጃው (የእነ ስዬ ተወልደ ቡድን) ተመልሶ ያጠናክረን› የሚል ነበር፤ በስማቸውም ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ በፃፉት (ርዕሱ ከላይ በተጠቀሰው) ፅሁፍ ጉዳዩን እንዲህ በማለት ገልፀውት ነበር፡-
‹‹…ሁላችንም ህወሓት ውስጥ እያለን እኮ አንጃው ድርጅቱን ተቆጣጥሮት በትረ-መንግስቱንም ሊጨብጥ ተቃርቦ ነበር፡፡ በአንጃው የመዋጥ አደጋ ጊዜ ሁላችንም ተኝተን ነበር፡፡ እነዚያ የተሰናበቱት ሰዎች በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ ቢቆዩ ኖሮ ይተኙ ነበር ማለት ግን አይደለም፡፡ አሁን ላለው አመራር ይደግፉት ነበር ይሆን ማለቴ ነው እንጂ፡፡ …ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወጣ ሁሉ እንደአዲስ ተደራጅቶ አሁን ላለው ማ/ኮሚቴ እገዛ የሚያደርግበትን መንገድ ማፈላለግ አለበት፡፡…›› (‹ውራይና› ቁጥር 4  ነሀሴ 2005 ዓ.ም)
ሆኖም አባይ ፀሀዬ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉት ‹በጭራሽ አይሆንም! የእነርሱ መመለስ ያውከናል› የሚል አቋም በመያዛቸው ሃሳቡ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ከዚህ በኋላ የእነ አቦይና አባይ ቡድን ‹ህወሓትን ማዳኛ› ያለውን ሁለት ወሳኝ እርምጃ ወስዷል፤ ከህግ ውጪ ሶስት ሜጀር እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎችን ሲሾም፣ በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበረውን ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከየትኛውም አይነት ‹ኦፕሬሽን› እንዲገለል አደረገው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከሀላፊነቱ አነስቶታል፡፡ በዚህ በኩል ያገኙትን የፖለቲካ ጉልበት በመመንዘር ከህገ-መንግስቱም ሆነ ከተለምዶአዊው አሰራር በማፈንገጥ ተጨማሪ ሁለት ም/ጠቅላይ ሚንስትሮች እንዲሾሙ ጫና ፈጥረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ኃ/ማርያም ደሳለኝን በቅርብ ርቀት እንዲከተል አድርገዋል (በነገራችን ላይ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በመረጠበት ወቅት ወልደስላሴ ሲጠቆም፣ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቦ እንዳይመርጡት ያነሳሳበት የደህንነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ሲሆን፣ በአንፃሩ ጌታቸው የተጠቆመ ጊዜ ወልደስላሴ እና ገብረሃዋድ ተቃውሞውን ቢያስተባብሩም ታናሽ ወንድሙ በላይ አሰፋን ጨምሮ ከመመረጥ ማደናቀፍ አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወልደስለሴና ገብረሃውድ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ)፡፡
ሌላኛው የህወሓት ‹ጠባቂ መልአክ› አባይ ፀሀዬ ነው (በ2005 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት በታተመችው ‹አዲስ ታይምስ› መፅሄት ላይ አባይ፣ መለስ ያደረገውን ማድረግ የሚችል /ከንግግር ችሎታ በቀር/ አደገኛ ሰው መሆኑን መግለፄ ይታወሳል) ዘግይቶም ቢሆን ቡድኑን የበላይ ባደረገው የ‹ፖለቲካ ጨዋታ› እርሱም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ታይቷል፡፡ ደብረፅዮንም ቢሆን ከህወሓት ጋር ባሳለፈው ዘመን ‹ትጉህ ደቀ-መዝሙር› ስለነበር ያካበተው ልምድ ህወሓትን በታደገው ንቅናቄ ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ እነ አባይ ከባህርዳሩ ጉባኤ በኋላ ነው ‹ከመከላከል ወደ ማጥቃት› ተሸጋግረው ብአዴንንና የመቀሌውን ህወሓት በ‹ሙስና› ስም ሰለባ ያደረጉት፡፡ ይህንን እውነታም የሚያጠናክርልን አቦይ ስብሃት ‹‹ውራይና›› መፅሄት ስለ ጉዳዩ ጠይቋቸው የሰጡት ምላሽ ው፡-
‹‹አሁን በእስር የሚገኙት [እነመላኩ ፈንቴን ማለታቸው ነው] ሙሰኞች ብቻ አልነበሩም፡፡ የፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍንም ሲለውጡ የነበሩ ናቸው፤ ያስፈራሩም ነበር፤ ‹የስልጣን ሹዋሚም ሻሪም እኛ ነን› አስከማለትም ደርሰው ነበር፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 2 ሠኔ 2005 ዓ.ም)
የብአዴን የአመራር አባል የሆነ አንድ ሚንስትር ለእስር ሲዳረግ፣ ሌላ ሚንስትር ደግሞ ከኃላፊነቱ መነሳቱ ይታወቃል፡፡
 አዲሱ ግንባር
ብአዴን የአዲስ አበባው ህወሓት ክንደ-ብርቱ እየሆነ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብን ቡድን አውላላ ሜዳ ላይ ትቶ አብሮ ለመስራት ተደራድሯል፡፡ እነ አባይም ‹ከብአዴን ተሻርኮ ሊያስበላን ነበር› ያሉትን የመቀሌውን የህወሓት ኃይል ከሞላ ጎደል ሲያስገብሩት፣ የቡድኑ መሪን አዜብ መስፍንን ደግሞ ከኤፈርት ከማሰናበታቸውም በላይ የፓርላማ ወንበሯን የሰዋችለትን የአዲስ አበባ የከንቲባነት ምኞቷን አጨልመው፣ በመለስ ፋውንዴሽን ገድበዋታል (የመለስ ሙት ዓመት በተከበረበት ወቅት የትግሉን ዘመንና የመለስን ገድል በኢቲቪ ሲተርኩልን የነበሩት የታሪኩ ዋና ተዋንያን አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ሳሞራ የኑስ…ሲሆኑ፣ በህልፈቱ ሰሞን ግን መድረኩን ተቆጣጥረውት የነበሩት ብአዴኖች፣ እነኩማ ደመቅሳ እና ትግሉን በመፅሀፍትና በቴሌቪዥን የሚያውቁት እነ ሬድዋን ሁሴን መሆናቸውን ስናስታውስ የእነ አባይ ፀሀዬ ህወሓት ምን ያህል ተገፍቶ እንደነበረ እንረዳለን፡፡)
በአናቱም ብአዴን የበላይነቱን በጨበጠበት ወቅት እንደ ስጋት ቆጥሮት ‹ሊፐውዘው› አስቦ የነበረውን መከላከያም፣ ከድርድሩ በኋላ በሁለቱ ኃይሎች ስምምነት ለአምስት ቀናት ኪራይ ሰብሳቢነትን እና ሙሰናን በተመለከተ ብቻ ተገማግሞ እንዲታለፍ ተደርጓል፡፡ ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የታሰቡት ጄነራሎች ጉዳይም ‹ያልታሰበ አደጋ ሊያመጣ ይችላል› በሚል ለጊዜው ተዘሏል፡፡ ይሁንና ኤታማዦር ሹሙን ጄነራል ሳሞራ የኑስን በዚሁ ዓመት መጨረሻ በ‹ክብር› ሸኝቶ፣ ጄነራል አበባው ታደሰን የመተካት ዕቅድ መኖሩን ምንጮች ጠቁመዋል (ከዚህ በኋላ በጡረታ የሚሰናበቱ ጄነራሎች ‹መከላከያ ቴክኖሎጂ› /መቴክ/ በሚመራውና ወደፊት በሚያቋቁማቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በስራ-አስኪያጅነት ወይም በቦርድ አባልነት እንደሚመደቡ ቃል ተገብቶላቸዋል)
ከኃ/ማርያም ጀርባ ያደፈጠ-ስውር እጅ
በሁለቱም ቡድን ካሉ ምንጮቼ ‹‹ኃ/ማርያም ስራው ከብዶታል›› የሚል ቅሬታ እንደነበራቸው ሰምቻለሁ፤ ይሁንና መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው በረከት ስምዖንን የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር› አማካሪ በሚል ሹመት በጽ/ቤቱ ማስቀመጥን ነው፤ እርሱሁሉንም ነገር ከጀርባ ሆኖ እንዲያከናውን ወስነዋል፡፡ በረከት የተመረጠው ‹ከመለስ ጋር በቅርብ ስርቷል፣ መለስ ያነበበውን አንባቧል፣ የመለስን የዕለት ተዕለት ሥራ በቅርብ ተከታትሏልና መንገድ ይመራል› በሚል እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል (በነገራችን ላይ መለስ ሞት ባይቀድመው ኖሮ የወደፊት ዕቅዱ ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ጀምሮት የነበረውን ግንባታ አጠናቅቆ፣ ከ2007ቱ ምርጫ በኋላ ስልጣኑን፣ ከአሻንጉሊቶቹ ለአንዱ አስረክቦ፣ መኖሪያውንም ወደ አዲሱ ህንፃ አዛውሮ፣ በለቀቀው ቤት ውስጥ የሚያስገባውን ጠቅላይ ሚንስትር ከጀርባ ሆኖ መዘወር ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ህልፈቱን ተከትሎ ግንባታውም የተቋረጠው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ግንባታው ሊቀጥል እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ በረከት ስምዖን እንዲገባበት ታስቦ ይሆን? …አባይ ፀሀዬም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹አማክሪ› ሆኖ እንደሚሾም ‹ፎርቹን› ጋዜጣ በ‹ጎሲፕ› አምዱ አትቷል፡፡ መቼም ኃ/ማርያም ‹‹ሰርክ ‹እኔም አንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልለት›  እያልኩ እዘምርለታለሁ›› ያለን አምላኩ ካልታደገው በቀር፣ ከእነዚህ ጉልበታም ሰዎች በጤና መውጣቱን እንጃ!)
ህወሓትና ብአዴን ልዩነታቸው መፈታቱን ለማሳየት፣ በረከት ስምዖን ከአዲሱ ሹመት በኋላ በሃያ ሁለት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ አድርጎት የማያውቀውን መንግስትን ወክሎ (በግሉ ሄዶ ሊሆን ይችላል) በትግራይ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የስራ ጉብኝት አካሄዷል፡፡ ‹ድምፀ ወያኔ› የተባለው የክልሉ ሬዲዮ ጣቢያም ጉብኝቱን ሳምንት ሙሉ ሳይታክት ደጋግሞ አስተላልፎታል፡፡ሽራፊ-መረጃ
የአቦይ ስብሃት ነጋ ቡድን በኢህአዴግ ውስጥ ተከስቶ ከነበረው ክፍፍል በአሸናፊነት መውጣቱ ከተረጋገጠ በኋላ አዲስ ወሬ እየተሰማ ነው፡፡ ይኸውም ‹ህወሓት የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን በመልቀቁ፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚያስረክቡትን ወንበር አቦይ ስብሃት መያዝ አለባቸው› የሚል ነው፤ ምንም እንኳ ሃሳቡ ተፈፃሚነት ባይኖረውም፣ ምንጮቼ አቦይ ራሳቸው በዘወርዋራ መንገድ ያሰራጩት ወሬ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ አዜብ መስፍንም ቦታውን የመያዝ ፍላጎት ያላት ይመስለኛል፡፡ብዙ ሲባልለት የቆየው የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ከላይ ለማቅረብ በሞከርኩት መንገድ ግራና ቀኝ ሲዋልል፣ የመከፋፈል ተግዳሮትን ሲሻገርና እንደገና እየተመለሰ ሲሰባሰብ እዚህ ደርሷል፡፡ በዚህ ኮሮንኮቻማ ሂደት ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትሩ ሚና ‹እዚህ ግባ› የምንለው እንዳይመስለን ሆኗል፡፡ ኃይለማርያም መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን የፓርቲው ሊቀ-መንበርነትን የመሰለ ጠንካራ ፖለቲካዊ ስልጣን መያዙ ይህ ሰው የሚባለውን ያህል የዳር ተመልካች ሆኖስ ይቆያልን? ለሚለው ጥያቄ ቀጣይ ጊዜያቶች ብቻ መልስ ይኖራቸዋል፡፡ የጠቀስኳቸው የስርዓቱ ጉምቱ ሰዎች በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱም ቢሆን፣ ይህን የኃይል መገዳደር እያደረጉ ያሉት በስልጣን ሞኖፖሊ ላይ ተቀምጠው
መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እናም ባቀረብኳቸው ሂደቶች እያለፉም ይሁን አይሁን ለስልጣናቸው የሚያሰጋ ጠንካራ የታቃውሞ ስብስብ አለመኖሩን ማመናቸው ይመስለኛል፣ የኃይል ትንቅንቁን ‹ግዜው አይደለም› ብለው ለማራዘም ሳይጠነቀቁ በግላጭ እርስ በእርስ የተፋለሙት፡፡
የሆነው ሆኖ የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈለግም፡፡ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
September 29, 2013

Sunday, September 29, 2013

“መስቀል የሚያቃጥል (አይደለም)” ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ሲኖዶሡ ውሣኔ ይሰጣል - አቡነ እስጢፋኖስ

abune estifanos
በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ እስኪያስተላልፍ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የአዲስ አበባና የጅማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አሣሠቡ፡፡ “መስቀል ከሠማይ ወርዷል አልወረደም? ትክክለኛ ነው አይደለም?” የሚለውን ለመመለስ የግድ ቅዱስ ሲኖዶሡ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ አባላት እንዳሣወቁ ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ እንደተባለው ከሠማይ የወረደ አለመሆኑ ከተረጋገጠም የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ይጠየቁበታል ብለዋል-ብፁዕነታቸው፡፡
መስቀሉ ከሠማይ ወረደ በተባለ በ4ኛው ቀን ነሐሴ 27 ቀን 2005 ከሠአት በኋላ ወደ ስፍራው በማቅናት ተገቢውን የፀሎት ስርአት ከካህናቱና ከቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ጋር ካደረሡ በኋላ መስቀሉን ከወደቀበት መሬት አንስተው ወደ ቤተመቅደሡ እንዲገባ ማድረጋቸውን የገለፁት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ መስቀሉ ከሠማይ ስለመውረዱ በአይናችን አይተናል ካሉት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንደማንኛውም ሠው መስማታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
መስቀሉን ከወደቀበት መሬት ያነሱት ብፁዕነታቸው፤ “መስቀሉ ያቃጥላል፤ ብርሃናማ ነፀብራቅ አለው” የሚባለውን አለማስተዋላቸውን ጠቁመው፤ “መስቀል የሚያቃጥል ሣይሆን የድህነት ሃይል ነው ያለው፣ የሚያቃጥል ቢሆን ኖሮ ከመሬት ላይ ማንሣት ባልተቻለ ነበር” ብለዋል፡፡ ወረደ የተባለውን መስቀል ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ምዕመናን ለምን እንዳይመለከቱት ተከለከለ የሚል ጥያቄ ያነሣንላቸው ብፁዕነታቸው፤ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶሡ ተጣርቶ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑ ጉዳዩን በጥሞና እንዲያጤነው በማሠብ ነው” ብለዋል፡፡
 (ምንጭ: አዲስ አድማስ)

ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
udj 4 19
አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡
ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ አመራር ህዝቡ ለሰጠው አመርቂ ምላሽ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረቡ፣በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ ትግል ታላቅ የማበረታቻ እርሾ መሆኑን ያምናል፡፡ ከዚህም ሕዝቡ አመራር ካገኘ ለመብቱና ነፃነቱ ወደ ኋላ የማይል መሆኑንና በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖሩን ያረጋገጥንበት፣ ትዕይንት ሲሆን በተጨማሪ ሠላማዊ ትግል በጋራ አመራር ከተያዘ ውጤታማ መሆኑን አምነናል፡፡
udj 2 19ሆኖም ከዚህ ሕዝባዊ ንቅናቄ የተማርነው ሌላ ነገር ቢኖር በአገራችን ያለውን የአስተዳደርና የህግ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ መውደቁንና ገዢው ፓርቲ በየትኛውም ደረጃ በሕዝብ በሚነሱ ጥያቄዎች በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ የወደቀ መሆኑን ነው፡፡
የአዲስ አበባ መስተዳድርና የፌዴራሉ መንግሥት ለሰልፉ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ቢልም የተለያዩ አስተዳደራዊ ደንቃራዎችን በመፍጠርና የማናውቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በመፍጠር የቅስቀሳ ሥራችንን በማደናቀፍና ሕዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይወጣ በማድረግ በተግባር ሠልፍ የማይደረግባት አገር ለመፍጠር ሣይታክት ተግቶ ሰርቷል፡፡ ቀስቃሾችና አመራሮችን አስሯል መኪናዎችን አግቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ማለፍ የተሣካ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠራችን ከዚህ በመነሳት አንድነት ፓርቲና 33ቱ በጋራ በተጠናከረ መንገድ በመላው አገሪቱ ቀጣይና ተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄ የማድረግ አስፈላጊነትን ተምረንበታል፡፡
ስለሆነም በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ የሠላማዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ለእስከዛሬው በድጋሚ እያመሰገንን ለቀጣዩ የጋራ ሥራችን እንደተለመደው ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም

Friday, September 27, 2013

ስበር ዜና – አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ታሰሩ!

September 27, 2013
የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዛሬም ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ አብረዋቸው የታሰዩት አመራሮችና አባላት እንደሚከተለው እንዘረዝራለን !
በፖለስ የታሰሩ አመራሮችና አባላት በከፊል
Millions of voices for freedom - UDJ
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
የተከበሩ ግርማ ሰይፉ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ስዩም መንገሻ – የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ዳንኤል ተፈራ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አቶ አስራት ጣሴ – ዋና ጸሃፊ
አቶ ተክሌ በቀለ – የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ሽመልስ ሃብቴ – የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ

አቶ ሃብታሙ አያሌው – የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ
አቶ ብሩ በርመጂ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አበበ አካሉ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አለባቸው ነጋሽ – አባል
አቶ መካንንት ብርሃኑ – አባል
አቶ እንዳልካቸው ባዩ – አባል
አቶ ብስራት ተሰማ – አባል
አቶ ወንደሰን ክንፉ – አባል
አቶ ኃይሉ ግዛው – አባል
አቶ ደረጀ ጣሰው – አባል
አቶ ገዛህኝ – አባል
አቶ ባዩ ተስፋዬ – አባል
አቶ ወርቁ – አባል

የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ

original_al_amoudi_wearing_eprdf_tshirt_may_2005

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል።
በቅርቡ በወልድያ ከተማ የወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች ባነሱት አመጽ መንገድ ዘግተው ወደ ላሊበላ ፤ ሰቆጣ ፣ ደሴ እና አዲስ አበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት ጉዞዎች እንዲስተጓጎሉ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አመጹን አነሳስታችሁዋል የተባሉ 13 ታዳጊ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የደህነነት ሐይሎች አጣራነው ባሉት መረጃ አመጹን ሼክ አላሙዲን ከጀርባ ሆነው ደግፈውታል።
የኢህአዴግ አመራር እና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የጸረ ሽብር ግብረ ሐይል በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ውይይት ካደረጉበት በኃላ ፣ በባለሀብቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ባይቻልም በወዳጆቻቸው በኩል ምክር አንዲሰጣቸው በአቶ በረከት ስምኦን የሚመራ አንድ ቡድን መዋቀሩን ለማወቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ሼክ አላሙዲን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታክስ እና ከግንባታ ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የደህንነት መስሪያ ቤት በባለሀብቱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መረጃ እንዳገኘ ቢገልጽም፣ መረጃውን እንዴት እንዳገኘው አልታወቀም። አንዳንድ ወገኖች ግን የሼክ አላሙዲን ከህግ በላይ መሆን ያሳሳበው መንግስት፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ባለሀብቱን ለመምታት የፈጠረው ዘዴ ሊሆን ይችላል ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ሼክ አላሙዲንን ወይም ወኪሎቻቸውን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
ሼህ አሊ አላሙዲን ለኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይታወቃል።

Chinese Man has New Nose Grown on Forehead (BBC)

By Carrie Gracie
27 September 2013
The chinese guy





A man from China’s Fujian province has had a new nose grown on his forehead following a traffic accident last year.
The 22-year-old man suffered severe nasal trauma and his subsequent treatment caused his nasal cartilage to corrode. Surgeons came up with the idea of growing a nose on his forehead.
After nine months of growth, surgeons say that the the nose is in good shape and the transplant will be performed soon.

No Human Rights = No Development September 26, 2013 Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights Report on Ethiopia to the United Nations

OAKLAND CA- In a report submitted to the UN Human Rights Council’s Universal Periodic Review (UPR) on September 15, 2013, the Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network outlined the human rights and international law violations perpetrated by the government of Ethiopia in the name of country’s development strategy.
Drawing clear links between recorded testimonies on the ground and breaches of specific international covenants and articles in Ethiopia’s constitution, the joint submission to the UN Human Rights Council also responds to Ethiopia’s draft National Human Rights Action Plan for 2013-2015. “Rather than working to build a development strategy grounded in human rights, the Ethiopian government is attempting to hoodwink its human rights record, leaving unmentioned its villagization program and the Anti-Terrorism Proclamation-both used by the government as significant justifications for forced resettlement, arbitrary detentions, and politically motivated arrests,” said Anuradha Mittal, Executive Director of the Oakland Institute.
As previous Oakland Institute reports have chronicled, the Ethiopian government’s efforts to clear land for large-scale foreign investment has entailed widespread violations of human, social, economic, and political rights. Violations of citizen’s rights to self-determination, housing, land for subsistence production, and free political association–enshrined in the Ethiopian constitution, the Rural Land Administration and Land Use Proclamation, and in United Nations international covenants–are carried out in the name of development.
The joint UPR submission suggests that the ruling party’s ability to implement country’s unpopular villagization program rests in its monopoly on force and dominance over the allocation of humanitarian assistance. “Authoritarian governance and the methods used in implementing development projects have combined to violate human rights to livelihood and culture for land-based peoples, especially in the peripheral regions,” said Joseph Schechla, Coordinator of the Housing and Land Rights Network. “Involuntary resettlement, a form of forced evictions, accompanies deprivation of the right to food, including the right to feed oneself, particularly for agropastoralists. On the other hand, the ability to control information and stifle dissent has enabled the ruling party to present a positive face to the international community, which has dubbed Ethiopia a nation in “renaissance”, he continued.
The joint submission presents undeniable evidence that should compel the international community to advocate for a human rights centered development strategy that would benefit all Ethiopians.

Thursday, September 26, 2013

“አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው” – ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም “

“አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው” – ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

“ኢትዮጵያዊ አሸባሪ አለ ብዬ አላምንም”
“የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የምሆነው ፓርቲዎች ከተዋሐዱ ብቻ ነው”
“አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው”

ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ለሁለት ወራት በአሜሪካ ቆይታ አድርገው ተመልሰዋል፡፡ ስለቆይታቸው እንዲሁም በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች “በተለይ” ከሎሚ መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በሃገር ቤት የሚታተመውን የሎሚ መጽሄት ለማንበብ እድሉ ካልገጠማቸው በሚል የዶ/ር ያ ዕቆብን ቃለ ምልልስ እንደወረደ አስተናግደነዋል።
ሎሚ፡- እንኳን በሰላም ተመለሱ!
ዶ/ር ያዕቆብ፡- እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፡፡
ሎሚ፡- የአሜሪካ ቆይታዎ ምን ይመስል ነበር;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- አሜሪካ የሄድኩት ከፊል ቤተሰቤ እዛ ስለሚገኝ ነው፡፡ እነሱን ለመጠየቅና እነሱን ለማየት ነው የሔድኩት፡፡ በአሜሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያኖች እንደመኖራቸው መጠን ከእነሱ ጋር መገናኘቴ አልቀረም፡፡ ውይይቶችም የማድረግ አጋጣሚ ነበረኝ፡፡ በ”ቴሌ ኮንፍረንስ፣ ፓልቶፕ” አማካይነት በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጊያለሁ፡፡ እንደሚታወቀው እኔ በአሁኑ ወቅት የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ እራሴን ወክዬ ነው ከነዚህ ወገኖች ጋር ውይይት ያደረኩት፡፡ 
ሎሚ፡- በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ፡፡ ይሁንና ግን የአቋም ልዩነት አለ፡፡ በቅርቡ ኦነግ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ ኢህአፓም ቢሆን አመራሮቹን በማሰናበት መግለጫ አውጥቷል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሣቸውን ችግር ሳይፈቱ፣ ለሀገር ችግር የሚኖራቸው ፋይዳ ምን ዓይነት ይሆናል ብለው ያስባሉ?
ዶ/ር ያዕቆብ፡- ርግጥ ነው፤ ክፍፍሉ ለማንም እንደማይጠቅም ግልፅ ነው፡፡ ሁላቸውም ይረዱታል፡፡ በአገኘሁት አጋጣሚ ያነሣሁት ዋናው ነጥብ መተባበር አለብን፣ አንድ ላይ መስራት አለብን የሚል ነው፡፡ ከተቻለ መዋሐድ አለብን፡፡ በሀገር ደረጃና በአደራ መልክ ጭምር ሁሉም ለምን ፓርቲዎቹ አይተባበሩም; አብረው አይሰሩም; አይዋሃዱም; የሚል ጥያቄ ያነሳል፡፡ ዓላማችን ለሀገራችን ዴሞክራሲና ብልፅግና ማስፈን እስከሆነ ድረስ ምን ያለያየናል? የሚለው ጥያቄ ነው ወሳኙ፡፡ ከባህላችንም ይሁን ከፀባያችን ከየት እንደተገኘ ባላውቅም በሀገራችን አብሮ መስራት በጣም አስቸጋሪ ነገር ሆኗል፡፡ በፖለቲካዊ ብቻ ሣይሆን በማህበራዊ ሕይወት ጭምር፡፡ ይህ ነገር ደግሞ እዛም አለ፡፡ ይህ ተቀርፎ አንድ ላይ መሰባሰብ አለብን፤ ተቃዋሚዎች ተሰባስበን፣ ውጭም፣ ውስጥ ያለነው በአንድ ልብና ቃል ከቆምን ኢህአዴግን በምርጫ ማሸነፍ እንደሚቻል እንገነዘበዋለን ይላሉ፡፡ ቅንጅት ያሸነፈው እኮ በፓርቲዎቹ ውህደት ምክንያት ነው፡፡ እነሱ ፓርቲዎች ተዋህደው እስከሰሩ ድረስ በገንዘባችን፣በጉልበታችን ምንም ሣንቆጥብ እንረዳለን ነው እያሉ የሚናገሩት፡፡ እንደሚታወቀው ብዙ ድርጅቶች አሉ ግን በየፊናቸው መካሰስ፣ መወቃቀስ፣ መነቋቆር አለ፡፡ ለቆሙለት አላማ ገፍተው ከመሄድ ይልቅ በመጨቃጨቅ ጊዜያቸውን ያሣልፋሉ፡፡ አሁን እንደተባለው ኢህአፓ ለሁለት ተከፍሏል፤ እንዲሁም ኦነግ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ ሌሎችም ፓርቲዎች ከነዚህ ውጭ ያሉ ተከፋፈሉ ሲባል ነው የምንሰማው፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ይሄ ነገር የባህልም ይሁን የታሪክም የምን ውጤት እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ይሄ እንደውም ሶሲዮሎጂስቶች በሰፊው ሊያጤኑት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያት ከተባለ “ለምንድ ነው ኢትዮጵያውያኖች አብረን በጋራ መስራት የማንችለው;” ለዚህ ጥሩ ምሣሌ ላንሣ፤ በውጪ አንድ የጥብቅና ቢሮ 1800 ጠበቆች አሉት፡፡ እኛ ጋር አንድ ቢሮ ውስጥ ሁለት ጠበቆች አብረው መስራት አይችሉም፡፡ ርግጥ ነው በሀገራችን ሽርክናን ሕጉ አይፈቅድም፡፡ በጣም አስገራሚ ነው! ለምን እንደማይፈቅድ አይገባኝም፡፡ ይህም ሆኖ ሁለት ጠበቃ አብሮ የሚሰራ የለም፡፡ የሕግ ስራ ደግሞ አብሮ ውይይት ተደርጐ ተመክሮበት የሚሰራ ስራ ነው፡፡ ሆኖም ግን እኔ የማውቃቸውና አብረው የሚሰሩ ሁለት ሦስት የሚሆኑ ጠበቃዎች የሉም፡፡ የሀገራችን አንድ ትልቁ ድክመት መከፋፈሉ ነው፡፡ መከፋፈል ባይኖር ይህንን ሁሉ ተቃዋሚ አንድ ላይ ማሣለፍ ቢቻል ኢህአዴግን በምርጫ በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል፡፡ ሕዝቡ የተከፋፈሉ ፓርቲዎችን አይፈልግም፡፡ በ1997 ዓ.ም. ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ ነበር የሚለው፡፡ ውጭ ያሉትም ቢሆን ትልቁ ችግራቸው የትኛውን ፓርቲ እንደግፍ? ሰማያዊ? አንድነት? መኢአድ… የትኛውን እንደግፍ ነው የሚሉት፡፡ በተከፋፈለ ኃይል ግን የትም ቦታ ላይ ሊደረስ አይቻልም፡፡
ሎሚ፡- በቆይታዎ ከሰብዓዊ መብት ተቋማትና ከአሜሪካ መንግስት አንዳንድ ኃላፊዎች ጋር የመገናኘት አጋጣሚ ነበርዎት;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- አልነበረኝም፡፡ ሊያገናኘኝም የሚችል ሁኔታም አልነበረም፡፡ እንዳልኩህ እኔ የፖለቲካ ፓርቲን ወክዬ አይደለም የሄድኩት፡፡ ስለዚህ ምንም ሊያገናኘኝ የሚችል ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- ወደ አሜሪካ ከመሄድዎ በፊት ለጠ/ሚ ኃ/ማርያም አንድ ደብዳቤ አስገብተው ነበር፡፡ ጉዳዩም በቤንሻንጉል (ጉራፈርዳ) በተባለ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጐችን የሚመለከት ነበር፡፡ እናም ከአሜሪካ ሲመለሱ ክስ እንደሚመሰርቱ ገልፀው ነበር፡፡ የክሱን ይዘት ምንድን ነው? ተከሣሾቹስ እነማን ናቸው;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- መጀመሪያ ክስ ከመመስረቱ በፊት፣ ለተከሣሹ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ልትከሰስ ነው፣ ይሄንን ነገር አስተካል የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ ይሄንን አስመልክቶ ለጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሣለኝ በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በተባረሩት ኢትዮጵያውያን ምክንያት የእነሱን መብት ለማስከበር ክስ እንደምንመሰርት ማስጠንቀቂያ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ ደብዳቤ ፅፌላቸዋለሁ፡፡ ለዛ ደብዳቤ መልስ አላገኘንም፡፡ የዛን ደብዳቤ መልስ ለማግኘት ትንሽ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ጊዜም ሰጥተናቸው ነበር፡፡ በቀጣይ ደግሞ ክሱን ወደመመስረት ነው የምንሔደው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የነዚህ ሰዎች መፈናቀል ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡ በሰው ዘር ላይ የሚፈፀም ወንጀል “Crime against humanity” ነው፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ ነገሮችን ይይዛል፡፡ ማፈናቀልን፣ ሰዎችን መደብደብን፣ የመሳሰሉትን ይይዛል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ በተለይ በዘር ላይ ተመስርቶ ከተደረገ በአለም አቀፍ ደረጃ ሊያስጠይቅ የሚችል ወንጀል ነው፡፡ በአለም አቀፍ ፍ/ቤት ክስ ከመመስረት በፊት በሀገር ውስጥ ያለውን የፍትህ ሁኔታ ማስጨረስ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ክስ ለመመስረት የምንዘጋጀው፡፡ የክሱም ይዘት፣ ሰዎች ከቀያቸው ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ ይህ ጉዳይ በሚመለከታቸው ባለስልጣናት ላይ ክስ መመስረት ነው፡፡ክሱ ሲመሰረት ማመልከቻ እናስገባለን፤ ማመልከቻው ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ፣ አቃቤ ሕግ ካመነበት ወደ ፍርድ ቤት ሊሄድ ይችላል፡፡ ሌላው በተፈናቀሉ ጊዜ ብዙ ንብረቶቻቸው ተዘርፈዋል፤ ወድመዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ንብረቶቻቸውን ጥለው ነው የሄዱት፡፡ ዘር ሊያመርቱ አልቻሉም፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በፈለገበት አካባቢ የመዞርና፣ ኑሮ የመመስረት መብት አለው፡፡ በኢትዮጵያ ሕግ ብቻ ሣይሆን በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች አዋጅ የተከበረ ሕግ ነው፡፡ አንድ ዜጋ በሀገር ውስጥ በፈለገበት ቦታ ሄዶ የመኖርና፣ ንብረት የማፍራት መብት አለው፡፡ ይሄ ህግ ነው የተጣሰው፡፡ እነዚህ ሰዎች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የተዘረፈው ንብረታቸው እንዲመለስላቸው፣ ለደረሰባቸው ጉዳት ካሣ እንዲከፈላቸው እነኚህን ጥያቄዎች እናቀርባለን፡፡ ፍ/ቤቱ ይህን ተቀብሎ ሊያስተናግደን ከቻለ ጥሩ፤ ካልሆነ ግን ወደ አለም አቀፉ መድረክ መሄዳችን የማይቀር ነገር ነው፡፡ አሁን ክሱን በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን፡፡ ክስ መመስረት የማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብት ነው፡፡ የተፈፀመባቸው ነገር ግን እጅግ አሣፋሪ ነገር ነው፡፡ ኢትዮጵያን የሚያሣፍር ነው፡፡ ትናንት የተመሠረተች ሀገር አይደለችም፡፡ የብዙ ሺህ አመት ታሪክ ያላት ሀገር ናት፡፡ አንዱ ዜጋ በፈለገው አካባቢ መኖር አይችልም ብሎ ማፈናቀል…በእውነት በኢትዮጵያ ላይ ከዚህ የበለጠ ውርደት ያደረሰ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡
ሎሚ፡- ክሱ እነማንን ያጠቃልላል;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- በመጀመሪያ ደረጃ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ኃላፊዎች ይህንን ጉዳይ ሣያውቁ፣ እነዚህ ሰዎች ከቀያቸው ተባረሩ ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ባያውቁ እንኳን ማወቅ ነበረባቸው ተብሎ መክሰስ ይቻላል፡፡ ኃላፊነታቸው የነዚህን ሰዎች መብት ማስከበር ነው፡፡ ይሄ የክልሉ ብቻ ኃላፊነት አይደለም፡፡ የፌዴራል መንግስትም ኃላፊነት ነው፡፡ ስለዚህ በአንደኛ ደረጃ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ይሆናሉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የክልሉን አስተዳደሮች…ከፕሬዚዳንቱ አንስቶ ሌሎችንም ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
ሎሚ፡- እርስዎ በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት በፀረ ሽብር ሕጉ ዙሪያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት አድርገው ነበር፡፡ እርስዎ የፀረ ሽብር ሕጉን እንዴት ይመለከቱታል;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለኔ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም፡፡ ምናልባት ከውጭ የሚመጣ አሸባሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ድንበርን አጠናክሮ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ እኔ በበኩሌ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ አለ ብዬ አላምንም፡፡ እስከዛሬም ድረስ አልታየም፡፡ እንደኔ አስተሳሰብ አሸባሪነት እኮ የራሱ ትርጉም አለው፡፡ የፖለቲካ ዓላማ አድርጐ ተነስቶ ሕዝብን ለመበጥበጥ፣ ለማስረበሽ፣ የሕዝብን ሰላም ለማናጋት የሚደረግ ድርጊት ነው፡፡ የፖለቲካ ለውጥ እንዲመጣ ጫና ማድረግ፣ ጥያቄ ማቅረብ አሸባሪነት አይደለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሕጉ ራሱ አሣፋሪ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዚህ ዓይነት ሕግ አይሰራም፡፡ አንድ ሰው ፃፈ፣ተናገረ ተብሎ ወህኒ ቤት አይገባም፡፡ ብዙዎቹ በሽብርተኝነት የተከሰሱ ሰዎች ቦንብ አልወረወሩ፣ የመንግስት መዋቅር አላበላሹ፣ የመንግስት መዋቅር አላወደሙ፤ ለምን ተናገራችሁ፣ ፃፋችሁ በሚል ነው የታሰሩት፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠውን ነፃነትን ይገድባል፡፡ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ይገድባል፡፡ ይሄ ሕግ አንድ ሰው አሰበ ብሎ እንኳን የሚቀጣበት ሁኔታ አለ፡፡ አንድ ነገር ማሰቡን በምን ማረጋገጥ ይቻላል? ማረጋገጫ መንገድ የለም፡፡ ማንም የፈለገውን ነገር ማሰብ ይችላል፡፡ አንተ ከፈለክ እኔን ለመግደል ልታስብ ትችላለህ፡፡ ወንጀል ሰራህ ማለት ግን አይደለም፡፡ እኔን ለመግደል አስበህ እንደሆነ እንዴት አድርጌ ነው የማውቀው፡፡ እና በእውነት የፀረ ሽብር አዋጁ የሀገሪቱን የሕግ አካሄድ፣ የፍትህ አካሄድ የበለጠ ይጐዳል እንጂ የሚጠቅም አይደለም፡፡ የወንጀል ሕጉ ወንጀለኛን ለመቅጣት በቂ አንቀፆች አሉት፡፡ ይሄን አዋጅ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአብዛኛው ያወገዙት ነው፡፡ ይህ በእውነት ለኢትዮጵያ ጥሩ ስም አይደለም፡፡ የዚህ አይነት ህግ የውጭ ባለሀብቶች እዚህ ሀገር መጥተው እንዳይንቀሣቀሱ ይከለክላቸዋል፡፡ ይሄ ሕግ በጣም ፅንፈኛና አላስፈላጊ ሕግ ነው፡፡ አሸባሪነትን መከላከል ካስፈለገ በሀገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲያዊና የሕዝቡ መብት መከበር አለበት፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲ ካለ፣ ሕዝቡ የኔ መንግስት ነው ብሎ ካመነ ራሱ ሽብርተኝነትን ይከላከላል፡፡ ከሕዝቡ በላይ ማንም የለም፡፡
ሎሚ፡- ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማመልከት ነው የሚያስፈልገው፤ እንጂ መንግስት የመከልከልም ሆነ የመፍቀድ መብት የለውም ይላል-ሕጉ፡፡ ይሁን እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ ለሁለተኛ ዙር የጠራው ሰልፍ ታግዷል፤ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል?
ዶ/ር ያዕቆብ፡- ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል ተገቢ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም ቢሆን በወቅቱ ለሚመለከተው ክፍል አስታውቋል፡፡ በሀገሪቱ ሕግ ወይም በሕገ መንግስቱም ይሁን በሌላው አለም አቀፍ ሕግ ማስታወቅ እንጂ ማስፈቀድ አያስፈልግም፡፡ ይሄ ሰብአዊ መብት ነው፡፡ መብቴ ይከበር ብለህ አታስፈቅድም፤ ትጠቀምበታለህ እንጂ፡፡ መብት እንደተገሰሰ ታስታውቃለህ እንጂ መብቴ ይጠበቅልኝ ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በጊዜው አስታውቆ ነበር፡፡ መልስም የተሰጠው አልመሰለኝም፡፡ “ጉዳዩን በርግጥ በዝርዝር አላውቅም፡፡ አልነበርኩም፡፡” መልስ ተሰጠውም አልተሰጠውም በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ካላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ ይችላል ይላል ሕጉ፡፡ ከዛ ባለፈ ግን ቢሯቸው ድረስ ሄዶ መደብደብ፣ ማንገላታት፣ ሰላማዊ ሰልፍን መከልከል ቀጥታ ሕገ መንግስቱን ቃል በቃል የሚፃረር ድርጊት ነው፡፡ መንግስት ያላከበረውን ሕገ መንግስት ማን ሊያከብረው ይችላል? መጀመሪያ መንግስት አርዓያ መሆን አለበት፤ መንግስት ካመፀ በምን ልትከላካል ነው? ይሄ የመንግስት አመፅ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተዘጋጁ ሰዎችን መደብደብ ቢሯቸውን መበርበር አመፅ ነው፡፡ ይሄ በእውነት አሣፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ከዚህ አይነት ድርጊት መውጣት አለብን፡፡ ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመፃፍ፣ የመናገር መብት የትም ሀገር ያለ ነው፡፡ ቱርክ፣ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ ይደረጋል፡፡ ለምንድነው እኛ ሃገር ሰላማዊ ሰልፍ በዱላና በግድያ የሚስተናገደው? ከእንደዚህ አይነት ነገር መውጣት አለብን፡፡ እንደሌሎች ሕዝቦች ሁሉ መብቶቻችን እንዲከበሩልን እንፈልጋለን፡፡ ሰዎች ነን፤ እንደሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ዴሞክራሲ እንፈልጋለን፡፡ ፍትህ እንፈልጋለን፣ ቅር ሲለን የመንግስት ፖሊሲ ሣይስማማን ሲቀር ወጥተን በሰላማዊ መንገድ መቃወም እንፈልጋለን፡፡ ይሄን መከልከል አያስፈልግም፡፡
ሎሚ፡- መንግሰት “አክሪራነት” የሚለውን ቃል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ጋር የማያያዝ አዝማሚያ ታይቶበታል፡፡ ይሄ ለጉዳዩ መፍትሄ ሊሆን ይችላል ወይ;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- የማንኛውም ሕዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ካልሆነ በስተቀር በጉልበት ሊፈታ አይችልም፡፡ በመንግስት በኩልም ኃይል ተጠቅሞ የሕዝብን ጥያቄ ማዳከም አይቻልም፡፡ የሚሻለው ምንጊዜም ቢሆን ወደ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመራውን ውይይት መምረጥ ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች መንግስት በኃይማኖታችን ውስጥ ጣልቃ አይገባ ማለታቸው ትክክል ነው፡፡ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ይሄንን ነገር ማቆም አለበት፡፡ ዋናው ነገር ግን ኢትዮጵያ በኃይማኖት ተቻችሎ በመኖር በጣም ዝናን ያተረፈች ሀገር ነች፡፡ ይሄ አሁንም ሊቀጥል ይችላል፡፡ ግብፅ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ሙስሊሞች ብቻ ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች አስር ፐርሰንት ናቸው፡፡ ሶሪያ ሙስሊም ብቻ ነው ያለው፤ ሊቢያም እንደዛው፡፡ ኢትዮጵያ እኮ ከዚህ የተለየች ነች፡፡ እኔ አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ዘመድ የሌለው የለም፡፡ ስለዚህ ዘመዶቼ ናቸው፡፡ ታዲያ በኔ ላይ ነው የሽብር ተግባር የሚፈፅሙት; አያደርጉትም፡፡ አስታውሳለሁ፤ ከሆኑ የቅርብ ጓደኞቼ ጋር ስንጨዋወት ሙስሊም ዘመድ የሌለው ኢትዮጵያዊ የለም በሚለው ተማመንን፡፡ በሀገራችን የሙስሊም አሸባሪነት የሚያስፈራ ነገር አይደለም፡፡ መብታቸው እስከተከበረ ድረስ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡ ዋናው ነገር ተግባብቶ ከሙስሊሞቹ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ መብታችን ይከበር ብለው ጥያቄ ያቀረቡትን የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ሰዎችን ቃሊት ሄጄ አነጋግሪያቸዋለሁ፡፡ “እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሀገራቸውን የሚወዱ፣ ለሀገራቸው በጐ ነገር የሚመኙ፣ ሰላምና ዴሞክራሲን የሚመኙ ሰዎች ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚለዩበትን ሁኔታ አላየሁም፡፡
ሎሚ፡- ኢህአዴግ ላለፉት አንድ አመታት “የመለስ ራዕይ” በሚለው መርሁ ቀጥሏል፡፡ አንድ ፓርቲ በአንድ ሰው ወይም በሕይወት በሌለ የቀድሞ መሪው ሀገር መምራት ይችላል?
ዶ/ር ያዕቆብ፡- በእውነት በጣም የሚገርም ነው፡፡ ሰው ከሞተ በኋላ በሬሳው ይግዛን ብሎ ይሄን ያህል ማጋነን፣ ማቅ ለብሶ ማዘን ተገቢ አይደለም፡፡ በጣም ኋላቀርነት ነው፡፡ እኔ እንደማየው “ሰው ስራው ታሪኩ ነው” ታሪክ ደግሞ ለማንም አያዳላም፡፡ የአቶ መለስ ስራ ታሪኩ ነገ ከነገ ወዲህ ይወጣል፤ እንጂ ዛሬ የተሰሩ ነገሮች (ጥሩ ተሰርተውም ይሁን መጥፎ) ሊደመሰሱ አይችሉም፡፡ ብዙ የማይደመሰሱ ነገሮች አሉ፡፡ በ1997 ዓ.ም. በመንግስት አባባል እንኳን 200 ሰዎች ሞተዋል /ተገድለዋል/፡፡ በዚህ ዙሪያ ማነው ተጠያቂው? ተብሎ የተፈረደበት አመራር የለም፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ወደብ አልባ እንድትሆን ተደርጓል፡፡ ይሄን ሁሉ ታሪክ የሚፈርደው ነገር ነው፡፡ ዛሬ “ራዕይ፣ራዕይ” ስለተባለ እነኚህ ድርጊቶች ይሰረዛሉ ማለት አይደለም፡፡ በጐውም፣ መጥፎውም፣ ስህተቱም ተደብቆ አይቀርም፤ ይወጣል፡፡
ሎሚ፡- ሀገሪቱ ወዴት አቅጣጫ እየሄደች ይመስልዎታል?
ዶ/ር ያዕቆብ፡- የዚህች ሀገር የወደፊት መፃኢ ዕድል ሁሉንም የሚያሳስብ ነው፡፡ የብዙዎች ጭንቀትም ይሄ ነው፡፡ ሀገሪቱ በብሔረሰብ ተከፋፍላ በአንዳንድ አካባቢ ከፍተኛ ጥላቻ እየተፈጠረ ነው፡፡ ልንሸሸው የማንችለው ነገር ነው፡፡ ተረባርቦ ሀገሪቱን ማዳን ሕዝቡን ማዳን ያስፈልጋል፡፡ ጥላቻ ሲፈጠር እያየን ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ወደ መጥፎ አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል፡፡ ጥላቻው የለም ማለት፣ አውሎ ነፋስ ሲመጣ ሰጐን አንገቷን ቀበረች የሚሉት ተረት ዓይነት ቢጤ ነው የሚሆነው፡፡ ጥላቻ ስለመኖሩ ከጉራፋርዳና ከቤንሻንጉል የበለጠ ምን ማስረጃ ያስፈልጋል? ይሄ በፍጥነት እልባት ማግኘት አለበት፡፡ ምንም ጥርጥር የሌለውም፤ ሀገሪቱ በብሔር ተከፋፍላለች፡፡ ስም ባልጠቅስም፤ አሜሪካ በነበርኩበት ወቅት የአንድ ብሔር ቀን ብለው ሲያከብሩ ተመልክቻለሁ፡፡ ይህንን ስናይ ወዴት ነው የምንሄደው? የዚህች ሀገር መፃኢ ዕድልስ ምን ይሆን? በዚህ ዓይነት አካሔድ ሀገር እንደ ሀገር ሊቀጥል ይችላል ወይ? የሚል ስጋት አዘል ጥያቄ ማንሳታችን አይቀርም፡፡ ርግጥ ነው፤ የአንዱ ጐሣ መብት አይከበር አይባልም፡፡ ቋንቋው መከበር አለበት፤ በቋንቋው መናገር መቻል አለበት፤ ግን በጎሳው ኢትዮጵያዊነቱን ሊሰርዝ አይችልም፡፡ አሜሪካ ውስጥ “ኢትዮጵያዊነት በግድ ተጫነብኝ፤ እኔ የዚህ ጐሣ ተወላጅ ነኝ” ሲሉ የሚናገሩ አሉ፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል? የወደፊቷን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የሚጥል ነው፡፡
ሎሚ፡- በጥብቅና ሞያ በመስራት ላይ ይገኛሉ፤ አሁን ያለውን የፍ/ቤቶች አሰራር እንዴት ያጤኑታል? ቢሮክራሲያዊ አሠራሮችስ ምን ያህል ተንሰራፍተዋል?
ዶ/ር ያዕቆብ፡- ቢሮክራሲያዊ አሠራሩ በፍርድ ቤት ብቻ ሣይሆን በአጠቃላይ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ያለ እንከን ነው፡፡ በርግጥ ዳኞችም በጣም ስራ ይበዛባቸዋል፡፡ ብዙ ክርክሮችና ብዙ ጭቅጭቆች አሉ፡፡ ግን መንግስትን በሚመለከት ጉዳይ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ፍትህ አገኛለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ ምናልባት ሁለት ግለሰቦች ተካስሰው ፍትህ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ የመንግስት እጅ ያለበት ጉዳይ ከሆነ ግን ፍትህ አገኛለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ ሙስና መንሰራፋቱን መንግስት ራሱ ተቀብሎታል፡፡ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቷል፡፡ በፍ/ቤት ብቻ ሣይሆን ሀገሪቱንም የወረር ክስተት ነው፡፡ ሙስና እንደ ነቀዝ ኢትዮጵያን እያጠቃ ነው፡፡ ዛሬ ያለገንዘብ ጉዳይህን የሚያይልህ የለም፡፡
ሎሚ፡- ዶ/ር ያዕቆብ እስከመቼ ነው ከየትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ጋር የማይሰሩት? የፖለቲካ አቋማቸውስ ምንድነው;
ዶ/ር ያዕቆብ፡- አንድ ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ በፖለቲካ አመራሩ ወጣቶች መተካት አለባቸው፡፡ እኔ ያለሁበት ወይም የነበርኩበት ሁኔታ አክትሟል፤ ማለትም ጊዜው አልፏል፡፡ ሌሎች መረከብ አለባቸው፡፡ አሁን ያለው ትውልድ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት፡፡ እኛ እኮ የተቀረፅነው በማርኪስዝም ሌኒንዝም ነበር፡፡ ዛሬ ማርክሲዝም ሌኒንዝም የትም አይሰራም፡፡ ዛሬ ለዴሞክራሲ የተማሩ፣ ለፍትህ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶት በአመራር ደረጃ መተካት አለባቸው፡፡ ይሄ ደግሞ አማራጭ የሌለው እውነታ ነው፡፡ ብቻችንን ከ40 አመት በላይ ነው በፖለቲካ ውስጥ የቆየነው፡፡ አስታውሳለሁ፤ መሬት ላራሹ ብለን ሰልፍ የወጣነው የዛሬ 43 አመት ነው፡፡ በዛ ጊዜ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፕሬዚዳንት ነበርኩ፡፡ እስካሁን ድረስ አልተውኩትም፡፡ በአመራር ደረጃ ፖለቲካ በቂዬ ነው፡፡ ኃላፊነት ግን አለብኝ፤ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ይህቺ ሀገር ብዙ ብዙ ዕድል ሰጥታኛለች፡፡ መካስ አለብኝ፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ለዴሞክራሲና ለፍትህ በሚደረገው እንቅስቃሴ የምችለውን አደርጋለሁ፡፡ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ጥሩ ቅርበት አለን፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ቅርበት አለኝ፡፡ ከመኢአድም ጋር ቅርበት አለኝ፡፡ አንዳንዴም ሲጋብዙኝ ካለኝ ተሞክሮ በመነሣት ንግግር አደርጋለሁ፡፡ ትምህርት ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡ አመራሩ ግን በወጣቶች መተካት አለበት፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የምሆነው ፓርቲዎቹ ከተዋሃዱ ብቻ ነው፡፡ ይህን ካደረጉ የአባልነት ቅፅ ለመሙላት ዝግጁ ነኝ፡፡ በዚህ በተከፋፈለ ሁኔታ ግን መቀላቀል አልፈልግም፡፡ በኔ እምነት የተከፈለ ፓርቲ የትም ይደርሳል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ አባል የመሆን ፍላጐት የለኝም፡፡

Wednesday, September 25, 2013

ወታደራዊ መኮንኖች የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ አቀረቡ

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ /
 ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛውየመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል።
ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊመኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉትየጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁንተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱየደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ሰራዊቱ አሁን የሚያገኘው ደሞዝ ለኑሮው በቂነው” የሚል መልስ ከሰራዊቱ ዋና አዛዦችተሰጥቷል።  በተሰጠው መልስ የተበሳጩት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ስብሰባ ረግጠውወጥተው እንደነበር ታውቋል። ጄኔራሉን ለማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበርም የደረሰን መረጃያመለክታል። ጄኔራል ሰአረ ለሰራዊቱ ደሞዝ እንዲጨመር አቋም ከያዙት ከፍተኛ መኮንኖች መካከልአንዱ ናቸው።
ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ባለው ከጄኔራል በታች ማእረግ ባላቸው መኮንኖች ስብሰባም   የደሞዝ ጭማሪናየኑሮ ውድነት ዋና አጅንዳ ሆኖ ቀርቧል።
በምስራቅ አካባቢ ባለው እዝ አንዳንድ መኮንኖች ” እኛ ቤተሰቦቻችንን ምግብ አብልተን ለማኖርአልቻልንም፣ እናንተ በሙስና በዘረፋችሁት ገንዘብ ልጆቻችሁን ውጭ አገር ልካችሁ ታስተምራላችሁበሚል አለቆቻቸውን በድፍረት መተቸታቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።   መኮንኖች ያቀረቡትንጥያቄ የመደረክ መሪዎች ለመመለስ ሲቸገሩ ታይቷል።
መኮንኖቹ ስብሰባቸውን ሲጨርሱ ከተራ ወታደሮች ጋር የሚደረገው ስብሰባ ይቀጥላል ተብሎአል።
ከፍተኛ ቅሬታ እየተስተናገደበት ባለው ስብሰባ፣ ወታደሮቹ እንደ መኮንኖቹ ሁሉ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄሊያነሱ ይችላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ሻምበል የወለደውን ልጅ በእሳት ማቃጠሉ ታውቋል። በምስራቅ እዝየሚገኘው ሻምበል ፈቃዱ በዳዳ ከሳምንታት በፊት በልጁ ላይ ቤንዜን በማርከፍከፍ ያቃጠለው ሲሆን፣ልጁም ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ አባቱ ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል ተኝቷል። ሻምበል ፈቃዱ በልጁ ላይይህን አሰቃቂ እርምጃ ለምን እንደወሰደ አልታወቀም።