Monday, March 16, 2015

የኢትዮጵያ (የተደፈረው)ካንጋሮ ፍርድ ቤት ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራን በሌለበት ከሶ በሌለበት ጥፋተኛ አለ



የኢትዮጵያ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራን በሌለበት ከሶ በሌለበት ጥፋተኛ አለ
አዲስ አበባ፣ 07/07/07
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 20ኛው ወንጀል ችሎት ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ሃይለመድን አበራ ከተመሰረቱበት ሁለት ክሶች በአንዱ ጥፋተኛ ሲለው ሁለተኛውን ውድቅ አደረገ።
ተከሳሹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከግንቦት 2000 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በረዳት አውሮፕላን አብራሪነት ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር የክሱ መዝገቡ ያስረዳል።
ለካቲት 10 2006 አጥቢያ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ30 ሲሆን የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 702 የሆነውን ቦይንግ አውሮፕላን 202 ተሳፋሪዎችን ጭኖ በጣሊያናዊው ዋና አብራሪነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሮም ጉዞ ጀምሯል።
ዋናው አብራሪ ካፒቴን ወደ መፀዳጃ ቤት እንደወጡ ተከሳሹ የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል በውስጥ በኩል በመቆለፍ አውሮፕላኑን በቁጥጥሩ ስር ማደረጉ በክሱ ተጠቅሷል።
የበረራ ቡድኑ በሩን እንዲከፍት ሲጠይቁት አርፋቹህ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ በማስፈራራት የአውሮፕላኑን መዳረሻ ያለአግባብ በማስቀየር ወደ ሲውዘርላንድ ጀኔቫ እንዲያርፍ አድርጓል።
በዚህም የፌደራል አቃቤ ህግ ተከሳሹ በሌለበት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 20ኛ የወንጀል ችሎት በህገ ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን መያዝ ወይም ማገት ብሎም አውሮፕላኑን አየር ላይ ሁለት ጊዜ ከፍ ዝቅ በማድረግ የመንገደኞችን ምግብ ማቅረቢያ ቁሳቁሶች እንዲገለባበጡ አድርጓል የሚለውን በመጥቀስ በፈፀመው በህገ ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል በሚሉ ወንጀሎች ከሶታል።
ተከሳሹ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ቢደረግለትም ባለመገኘቱ በሌለበት የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰምቷል።
በመሆኑም ዛሬ ችሎቱ መዝገቡን መርምሮ በአንደኛው ክስ ጥፋተኛ ሲለው በሁለተኛው ክስ ቁሳቁስ ተገለባበጠ ከሚለው ውጭ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባለመኖሩ አቃቤ ህግ እንደ ክሱ አላስረዳም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል።
ተከሳሹ ጥፋተኛ በተባለበት በአንደኛው ክስ ቅጣት ለመጣል ለመጋቢት 11 ቀን 2007 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

No comments:

Post a Comment