Monday, November 3, 2014

የመኢአድ አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው

Monday, November 3, 2014

የመኢአድ አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተንተርሶ በሚመስል መልኩ በምስራቅና ምእራብ ጎጃም አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ

በተመሳሳይ ዜና ደግሞ የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች “እኛ ሀገር እየመራን እናንተ ትቃወሙናላችሁ እናንተን እናጠፋቹሃለን” በማለት ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡ አመራሮቹ በድብደባው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል፡፡
አቶ ወኖ በዳሳ ራሳቸውን ስተው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም እስካሁን እንዳላገገሙ እና የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ ህክምና አግኝተው ከወጡ በኋላም በከተማው ደህንነቶች ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች ላይ ድብደባ እንዲደርስ መመሪያ የሰጡት የከተማው የፖሊስ አዛዥ በአቶ ወኖ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት ተደናግጠው በአምቡላንስ እንዲወሰዱ ካደረጉ በኋላ የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ “በአንድም ሚዲያ ስለሁኔታው እንዳይናገሩ” በሚል ክትትል እያስደረጉባቸው ያገኛል ሲል ፍኖተነጻነት ዘግቧል::

No comments:

Post a Comment