ምስጋና ለኢትዬጲያ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የጸረ ሽብር ቡድን ግብረ ሃይል
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለምዶ በአሜሪካ ግቢ ራስ ስዩም ሆቴል አጠገብ ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭነት የሚጫንበት ቦታ አካባቢ በሚገኘው ራህመት ኤጀንሲ በር ላይ ኮድ 3 የታርጋ ቁጥር 73189 በሆነ አንድ |የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ጎማ ስር የአጅ ቦምብ ተገኘ ተባለላቹ፡፡፤
ይህን የእጅ ቦምብ የአዲስ አበባ ከተማ መደበኛ ፖሊሶች ቀደም ብለው በእጃቸው ይዘውት እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፤የእጅ ቦምቡን ጠዋት ይዘውት ከነበሩት ሁለት ፖሊሶች መካከል የአንዱ ፎቶ ከዚህ በታች ተያይዞ ቀርቧል|፡፡ሙስሊሙ የመረጃ ሰው ሆኗል፡፡አልሃምዱሊላህ
ይህ ቦምብ አፈንጂው እና ቦምባ አምካኞች ያደረጉት ትንቅንቅ አንድ ወንድም ያደረሰኝን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡የተቀረውን መረጃ በቦታው ከነበሩ እና ከኢቲቪ ማጣራት ትችላላችሁ
አንድ ግለሰብ ቦምብ ይዞ በመምጣት አንድ የጭነት መኪና ጎማ ስር ቦምቡን አስቀምጦ ዞር ይላል፡፤ በመቀጠልም ይህ ግለሰብ ከቆይታዎች ቡሃላ ተመልሶ በመምጣት እዛው አካባቢ ይቆማል፡፡ በመቀጠልም ፖሊስ ይህን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ያውለዋል፡፡ከዛ ፖሊስ ይህን ግለሰብ ሲፈትሸው ሌላም ቦምቦች በኪሱ ስር ያገኛሉ፡፡ ከዛ የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ይህን አሸባሪ ግለሰብ በህዝብ እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር አዋሉት፡፤ ከዛ የፈንጂ አምካኝ ግብረሃይል መጣና መኪናው ጎማ ስር የተቀመጠውን ቦምብ እንዳይፈነዳ በጥንቃቄ በማድረግ አክሸፈው፡፤ከዛ በቃ ድራማው በሚገርም ሁኔታ በመጠናቀቁ ቀረጻ ተካሂዶለታል፡፡በጥሞና ስላነበባችሁልኝ አመሰግናለው
ቆይ ትንሽ ልጨምርላችሁ ይህ አሸባሪ ግለሰብ እራሱ ያስቀመጠው ቦምብ ጋር በመምጣት መፍንዳት እና አለመፈንዳቱን የሚጠባበቀው ምንኛ አስገራሚ አሻባሪ ነው???? ቀጥሎም ለሌላ ተልኮ የሚሆን ቦምቦችን በኪሶ ሸክፎ ይዞ ነበር፡፤ይህንንም አደገኛ ሊፈጸም የነበረውን የሽብር ጥቃት በማስመለከት ለኢቲቪ ዜና የሚሆን ድራማ ይህ አሸባሪ ግለሰብ ከፌደራል ፖሊስ እና ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረ ሃይሉ ጋር በመሆን ሲከውን እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የዚህን ሙሉ ዜና ዝርዝር ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ ይጠብቁ:;
ከዚህ ቀደም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያም ተመሳሳይ ጠቀጣጣይ የሆኑ ሁለት ስሊንደሮች ተቀምጠው መገኘታቸው ኢቲቪ ዘግቦልን ነበር፡፡ደሞ ሌላ ቀን ምን አይነት ነገር መያዡን እንሰማ ይሆን???? ፡፡
ምናለ ኢትዬጲያ ሃገሬ ለአለም ሰላም ሁሌም በምታደርገው ጥረት የምትደነቅ በመሆኗ እንዲህ አይነት የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሏን ችሎታ ለሌሎች ሃገሮችም ልምዷን ብታካፍል እና ቦምቦች ሳይፈነዱባቸው ሁሌም ከነአሸባሪው በቁጥጥር ስር እንዲ ያውሉ ብትረዳቸው ?????
እኔስ ምንም አልልም ግን ብቻ ይሄ ድራማ እንዲ እያጃጃለን አንድ ቀን የምር አፈንድተውት እንዳይጨርሱን እሰጋለው!!!
ለማንኛውም ቦንቦቹ ሳይፈነዱ በቁጥጥር ስር ስለዋሉ አልሃምዱሊላህ በዚህኛው ድራማ ሂወታችንን አልቀጠፉብንም፡፡
አላህ የኢትዬጲያን ህዝብ
ለድራማ ተብሎ ከሚደረስ ጥቃት ይጠብቅልን!!!!
ድል ለኢትዬጲያ
No comments:
Post a Comment