ከጥቂት ሰዓታት በፊት ፣ ሰላማዊ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ፍቼ ያቀኑ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አሰተባባሪዎች በአገዛዙ ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፣ ከወዲሁ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠዉን የዜጎች መብት ለመርገጥ ኢሕአዴግ እየሰራ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነዉ። የፓርቲዉ አመራር አባላት በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት መግለጫ እንደሚሰጡም ለማወቅ ችለናል።
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጂንካ ሰላማዊ ሰልፎች በወላይታ ሶላማዊ ሰልፎችን፣ በአዲስ አበባና በወላይታ ሶዶ ደግሞ የተሳኩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማድረጉ ይታወቃል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/
No comments:
Post a Comment